ልማት በቤተ ክርስቲያን
ልዮ ዕትም መጽሔት
ይህ ”ልማት በቤተክርስቲያን“ የተሰኘ ልዮ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ከትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠውን መግለጫ በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
. . . በመጨረሻም መላው በትግራይ ክልል የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲወገድና አንድነቷ ጸንቶ እንዲኖር በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ ስታግዙ እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም በክልሉ የተከሰተውን ቀኖናዊ ጥሰትና ሕገወጥ አደረጃጀት ቆሞ እናት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ጸንታ እንድትኖር እንደአሁን ቀደሙ በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን የኢፌዴሪ መንግስትም እንደአሁን ቀደሙ በሲኖዶሳዊ አንድነት ላይና በቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ የተጋረጠው ችግር ልዩ ትኩረት በመስተጠና የበኩሉን ሚና በመጫወት የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድንትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀት ጸንቶ እንዲኖር አገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በውጭ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያናትና የአገልጋዮችን ዝርዝር በአፋጣኝ እንዲልኩ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ሰጡ።
መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የቤተክርስቲያናችንን የመረጃ ሥርዓት ለማዘመን የሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ ፣መተንተኛና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ሥርዓትን በመፍጠር ወጥነት ያለው የመረጃ ፍሰት ለመዘረጋት በጥናት ላይ የተመሰረተ የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ሰበር ዜና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር አረፉ
ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ የሆኑት በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ ዶ/ር በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በባህርዳር ሀገረ ስብከት የሚከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፣ወደፊት በሚሰሩ የልማት ሥራዎች ዙሪያም የሥራ መመሪያ ሰጡ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚያዝ ፰ -፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ያስጀነመሯቸውን ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናትና ልዩልዩፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል ። በፕሮጀክቶቹ ዙሪናም ድጋፍና ክትትልም አድርገዋል፣ ከገዳማትና አድባራት አስተዳደር ክፍሎች ጋርም ውይይት አካሂደው የሥራ መመሪያና ወደፊት መአናወን በሚገባቸው ሥራዎች ዙሪያም አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መጋቢት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ ም በጀርመን ሙንስትር ከተማ በመገኘት ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሙንስተርና አካባቢ ጳጳስ ከኾኑት ዶክተር ፊልክስ ጌን ጋር ውይይት ውይይት ማድረጋቸውን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ምልአተ ጉባኤ እንዲካሄድ ጥሪ ተላለፈ
በህገ ወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በአምስት ቀናት ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላለፈ።
በምሥራቅ አውሮፖ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው ከተማ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የምሥራቅ ጎጃም፣ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ አገልግሎት ጀምሯል ።
የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ ግብር
የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ ግብር ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት የምምሪያ ኃላፊዎች የመንግስት ባለሥልጣናት፣የባቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተፈጸመ።
ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ የሕይወት ታሪክ
ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በወሎ ክፍለ ሀገር ሰገራት (ኩታበር ወደ ግሸን መሔጃ) ከወላጅ አባታቸው ከአለቃ ምሕረቱ ካሣ ከእናታቸወ ወ/ሮ አበቡ ወልደ ጻድቅ በየካቲት 16 ቀን 1916 ዓ.ም ተወለዱ። የፊደልና ንባብ ትምህርት የጀመሩት በእናታቸው ሀገር በቦሩ ሥላሴ ነው።
ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።
የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ