ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
“ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደረሰባት የውስጥ ፈተና ሀዘኗ ከባድ ነው።” ብፁዕ አቡነ አብርሃም
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ይህን የገለጹት በዛሬው ዕለት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ የተፈጸመውን “የጳጳስ ሹመት” አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ
መግለጫውን የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።
በበረዶዋማ ፊንላንድ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጥምቀት በዓልን በድምቀት አከበሩ።
የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፣ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሰሱ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኘበት በድምቀት ተከሯል።
የጋምቤላ የጥምቀት በዓል አከባበር
የጋምቤላ የጥምቀት በዓል አከባበር ዛሬም ቀጥሏል እስከ ሰኞ ጥር 15 ይቀጥላል።
የ ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ መዋልን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየ ዓመቱ ጥር፲ ና ፲፩ቀን የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ዘንድሮም በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት ተከብረው ውለዋል።
ፎቶ ሪፖርታዥ፦ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር
ፎቶ ሪፖርታዥ፦ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የከተራ በዓል አከባበር
የከተራ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በጃን ሜዳ በታላቅ ድምቀት ተከበረ
የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የከተራ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት በታላቅ ሥነሥርዓት ተከብሮ ውሏል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስብከተወንጌል እምርታ ለቤተክርስቲያን ከፍታ፣የቤተክርስቲያንን መዋቅር ጠብቆ ማገልል፣የኮረና ቫይረስና ተዛማቾ በሽታዎችን መከላከልን በተመለከተ፣በሽታን መከላከል ከሃይማኖት አስተምህሮ አንጻር በሚሉና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዩች ዙሪያ ከጥቅምት ፲፬ -፲፭ ሸን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ/ም በጠቅላይ ቤተክህነቴ ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ለጠቅላይ ቤተክሄነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ለአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።