የቦታው ስም ቀራንዮ ነው
የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
በኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ችግር ምክንያት የተደራጀው የሽምግልና ኮሚቴ እስከ አሁን የሰራቸውን ስራዎች ለዐቢይ ኮሚቴው ሪፖርት አደረጉ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተከሰተው የቀኖና፣የሃይማኖትና የአስተዳደር ጥሰትን ተከትሎ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር ምክንያት ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት የተደራጁት የሽምግልና ኮሚቴዎች (የሀገር ሽማግሌዎች) ችግሩ ከተፈጠረ ወዲህ በኮሚቴው የተሠሩ ሥራዎችን እና ወደፊት ሊሠሩ ስለሚገባቸው ጉዳዩች ለዐቢይ ኮሚቴ፣ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለመንበረ ፓትርያርክ እና ለቅዱስ ሲኖዶስጽሕፈት ቤትዛሬ የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም ሪፖርቱን አቅርቧል።
ቤተክርስቲያን ያወጀችውን አዋጅ ተከትሎ ሃይማኖታዊ ተልእኳቸውን በመፈጸማቸው ከሥራ የተባረሩ፣የታሰሩና የተንገላቱ ኦርቶዶክሳዊያን ሪፖርት እንዲያደርጉ የተላለፈ ጥሪ፤
የካቲት ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
መረጃ!
የካቲት 03 ቀን 2015 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ ካስተላለፈው ዕግድ መካከል የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ የአባ ሳዊሮስ፣ የአባ ኤዎስጣቴዎስና የአባ ዜና ማርቆስ ዕግድ ተነስቷል።
ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
ብፁአን አባቶች በአዋሽ ሰባት የታሰሩ ወጣቶችን ሊጎበኙ ነው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ወቅታዊ ችግር ምክንያት አዋሽ ሰባት በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ሁኔታ ለመመልከት ብፁአን አባቶች የሚመሩት ልዑክ በማረሚያ ቤቱ ጉብኝት እንደሚያደርግ ቤተክርስትያኗ ያቋቋመችው ጊዜያዊ የሕግ ኮሚቴ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።
ለኦርቶዶክሳውያን እና ለቤተክርስቲያን ክብር በመሟገታቸው ለእስር ተዳርገው የነበሩት ፓስተር ብንያም ሽታዬ ከእስር ተለቀቁ።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ ጥብቅና በመቆም ሉዓለዊነቷንና መብቷን ማስጠበቅ እንደሚገባ በመሟገታቸው ሁካታና ብጥብጥ ፈጥረዋል በሚል ወቀሳ ታስረው የነበሩት ፓስተር ብንያም ሽታዬ ዛሬ የካቲት ፲፯፤ ፳፻፲፭ በአምስት ሽህ ብር ዋስ ተለቀዋል፡፡ ለዚህም ውሳኔ መሳካት ከፍተኛ ርብርብ ያደረጉት ፴፫ የሚሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የሕግ ጥበቆች መሆናቸው ታውቋል፡፡
የዝዋይ ገዳም ኮሌጅ የተመሠረተው ለማን ነው ?
በመጋቤ ብሉይ ቆሞስ አባ አትናቴዎስ
የገዳሙ ርዕሰ መምህርና የኮሌጁ የቦርድ አባል
በውጪ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት መረጃዎችን ከማዕከል እንዲወስዱና በማዕከል እንዲያሰራጩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ አስተላለፉ።
የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎ ኦባሳንጆን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ዙሪያ አነጋገሩ።ቅዱስነታቸው ኦሊሴንጎ በሰላም ዙሪያ እያደረጉት ያለውን ጥረት በማድነቅ ምስጋና አቅርበውላቸዋል፤
ማኅበረ ቅዱሳንና ሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ያዘጋጁት የ2015 ዓ.ም የከፍተኛ ት/ተቋማት ገቢ ተማሪዎች ሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ።
ወደ ከፍተኛ ት/ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሚከታተሉባቸው ጊዜያት ኦርቶዶክሳዊነታቸውን በማጠንከር እና በመንፈሳዊነታቸው በመበርታት ተምስጋኝ መሆን እንደሚገባቸው ብፁእ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።”
አሥሩን ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመተግበር እነ አቡነ ሳዊሮስ ተስማሙ።ወቅታዊ መግለጫ
የካቲት ፲፩ቀን፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም