መጋቢት 20ቀን2017ዓ.ም
*****
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተመርጦ ወደ ግሪክ አቴንስ ያቀናው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ በመፍታት የቤተ ክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነትን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ ማድረጉን ገልጿል።
የቅዱስ ሲኖዶሱ ልዑካን ቡድን ባለፉት ቀናት በግሪክ አቴንስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ በተናጠልና በጋራ በርካታ ውይይቶችን ማድረጉን ገልጾ በስተ መጨረሻ በስምምነት ተጠናቋል ብሏል።ይህ ሰላም እና አንድነት እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደረጉትን ከካህናት፣ ምዕመናንና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ላበረከቱት የተቀደሰ ተግባርም በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ምስጋናውን አቅርቧል።
በዚሁ የእርቅ፣የሰላምና ስምምነት ሂደት ላይ በግሪክ መንግሥት በኩል በተለይ የሃይማኖት ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ለሂደቱ መሳካት ላደረገውና ወደፊትም ከቤተክርስቲያኗ ጋር አብሮ ለመስራት እንሁም በማንኛውም መስክ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የገለጹት የልዑካን ቡድኑ አባላት በውይይቱ ወቅትም በአካል ተገናኝተው መሳተፋቸውን በማድነቅ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ። በአጠቃላይ ውይይቱንና ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ እንመለሳለን።