የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በተደረገው የአቀባበል ሥነሥርዓት ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት

June 3, 2025

‹‹ወዝንቱ ሕጉ ለቤት ዘዲበ ርእሰ ደብር
በተራራው ራስ ላይ ያለው የቤቱ ሕግና ሥርዓት ይህ ነው››
(ሕዝ.43+10)
‹‹አይድዖሙ ሥዕለ ዝንቱ ቤት ይዕቀቡ ኵሎ ሥዕሎ ወትእዛዞ ወይግበርዎ ወዝንቱ ሕጉ ለቤት ዘዲበ ርእሰ ደብር ሥርዓቱንና ሕጉን ይጠብቁና ያደርጉትም ዘንድ የዚህን ቤት ክብርና መልክ ንገራቸው›› በሚለው ቃል ክብሩ የተገለጠው፣የአገልግሎታችን መዳረሻ የሆነው የቤታችን ሕግና ሥርዓት በርቱዕ እምነት ማንነታችንን ቀርጾ፣ ከምግባረ ሃይማኖት ጋር አዋሕዶ ወደ እውነተኛ ወደባችን (ወደክርስቶስ) ለመድረስ የሚያበቃ ከውድቀት የምንጠበቅበት ሕገ ርትዕ መሆኑ የታመነነው፡፡

ከዓለም ሁሉ ከፍ ብሎ የከበረውና የተቀደሰው የእግዚአብሔር ቤት እውነተኛ መልክም የተጨነቁትን ማረጋጋት፣ ተሰፋ ላጡ ወገኖች ተሰፋ መሆን፣ በሕዝቡ መካከል መተማመንን ማስፈን፣ ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን ማወጅ ነው፡፡ የዚህን ቤት ትክክለኛ መልክ፣ መውጫውንና መግቢያውን፣ሥርዓቱንና ሕጉን ተረድተን በማስተዋል እንድንኖርበትም የቤቱ ባለቤት “ቅዱሰ ቅዱሳን” ብሎ ሰይሞታል፡፡ነገር ግን ‹‹እለ አልቦሙ ኀሊና ወልብ የዐቅቡ ግብሮሙ ወሥርቶሙ በዘተአዘዙ ናሁ ሌሊት ትዴግኖ ለመዓልት ፣ ወፀሐይ ይዴግኖ ለወርኀ በከመ ተአዘዘ። አእምሮ የሌላቸው ማሰብ የማይችሉ ግዑዛን ፍጥረታት ከእግዚአብሕር በታዘዙት መሰረት ግብራቸውንና ወሰናቸውን ይጠብቃሉ ፤ሌሊት ትእዛዙንና ሥራዋን ጠብቃ ቀንን ትከተለዋለች፡፡ ፀሐይም በታዘዘው መሰረት ጨረቃን ይከተለዋል፡፡ እያንዳንዳቸውም በሕግና በሥርዓት መኖር ተስኖት ሕግን ሲተላለፍ፣ ሥርዓትን ሲያፍርስ ይታያል፡፡መጽ ሲኖዶስ አንቀጽ 45 ገጽ 22)

በእኛም የአገልግሎት ዘመን የዚህ ቤት ሠሪና አስገኝ የሆነው አምላከ ምሕረት እግዚአብሔር በሚደንቀው የፍቅሩ ዝምታ ታግሶን ነው እንጂ ዓለሙን ሁሉ አቅፎ በሚይዝ ልባቸውና በሰፊ ትክሻቸው ሁሉን ተሸክመው፣ ሕይወታቸው የመላእክት ያህልሆኖላቸው ለደካሞቹ ሲተጉ በኖሩት፣የቤቱን ሕግና ሥርዓት በሚያውቁት አባቶቻችን መንፈሳዊ ተጋድሎ ተጠብቆ የኖረውን የቤቱን ጥንታዊ መልክ የሚለወጡ፣ ከምግባረ ሃይማኖት የሚያድጡ አንዳንድ ጉደለቶቻችን መታያት ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል፡፡

በመሆኑም የቤቱ መልክና ሥርዓት የተዋበ እጅግ ከፍ ያለ ስለሆነ እኛን በክብር ከፍ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት አቅቶን ከዓለም ሕግ፣ ከሥነ ፍጥረት ሥርዓት በታች አሳንሰን ካየነው የቤታችንን ውበት በራሳችን እናጣዋለን፡፡

የልዩነት፣ የጠብ፣ የጭቅጭቅ ቤትም ካደረግነው በክብር ፈንታ ሐሳር፣ በከፍታ ፈንታ ውድቀት በራሳችን ላይ እንዳናመጣ የቤቱን ሥርዓትና ሕግ በጋራ ትብብር ወደነበረበት መመለስ ግድ ይለናል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሠራው፣ አባቶቻችን የደከሙበት
የቤታችን ጥንታዊ መልክ ሰላምና ፍቅር፣ስምምነትና አንድነት፣ቅንነትና አስተዋይነት ጽናትና ደግነት ነው:: እንዲህ ያለ መልክና ውበት ባለው ቤት ስንኖር ደግሞ የዓለም መልክ ሊታይብን አይገባምና መልካችን አምላካዊ፣ አለባበሳችን ሃይማኖታዊ፣አኗኗራችን ሰማያዊ መሆን ይኖርበታል፡፡

ከቤቱ መልክ ወጥተን እርስ በእርሳችን ከተለያየን ለማይጠገን ስብራት፣ለማይታረም ስሕተት የምንዳረግ እንሆናለንና አንድም ነገር ሳይጎድልብን በፍጹም ደስታ የሚያኖረንን ይህን ቤት በክብር እንጠብቀው፡፡ወደፊትም ከአለፈው ታሪካችን እየተማርን፣ በቤቱ ሕግና ሥርዓት፣ በጋራ ውይይት ስሕተቶቻችንን እያረምን ትውልዱ ከእውነትና ከታሪካዊ መረጃ የራቀ እንዳይሆን መሥራት የመሪነት ተግባራችን ነው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ክቡራንና ክቡራት ልጆቻችን!

“ከሁሉ በተቀደሰው፣ በዙሪያው ካሉት ሀሉ ከፍ ባለው” የእግዚአብሔር ቤት እንደየደረጃችን ለአገልግሎት ስንጠራ መዐርጉንና ሀብቱን፣ የመከበር ዕሴቱንና ዐስቡን ብቻ ሳይሆን የሥልጣኑ ምንጭ፣ የተልእኮው ሥምረት፣ የማዕረጉ ድምቀት ለሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቦታ አሠራር በሚያመች ሕይወት ካገለገልን አገልግሎታችን በፍቅር ይጸናል፡፡ የሚማርክ መዓዛ ቅድስና ያለው ሕይወት፣የሚዘከር ማንነት ይኖረናል።

በመሆኑም ‹‹ከመንፈስ ቅዱስ ተለይተን እኛ ለእግዚአብሔር እንግዶች ነንና››በእርሱ እየተመራን በተሠጠን የአገልግሎት ጊዜ እንቅፋቶችን ሁሉ በጋራ በማስወገድ ሐዋርያዊ መሠረት ያለውን አንድነታችንንና ሰላማችንን በማጽናት፣ በምድር ሆነን በሰማይ ሥርዓት እየኖርን ለሀገራችን እድገት፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት መስፋፋት ከልብ መሥራት ይገባናል ፡፡ (ቅዱስ አትናቴዎስ)

ሁላችሁም እንደምታስታውሱት እኔና ወንድሜ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከአሁን በፊት በዚሁ ቤት አብረን አገልግለናል፡፡ ሰውንና እግዚአብሔርን ለማገልገል ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠን የሦስቱ ዓመታት የአገልግሎት ዘመንም የልባችንን እልፍኝ ሰፋ አድርገን የሚጠበቅብንን ለመሥራት፣ የሁሉም ልጆቻችን አባቶች ሆነን ሁሉንም በእኩልነት ለማገልገል እንሠራለን ብለን እናምናለን፡፡
ለቤቱ ክብር በሚመጥን በመልካም ምግባር በተጌጠ ሕይወት በዚህ መንገድ መሥራትና ማስተዳደር ከቻልን ከየት ተነሥተን ወዴት እንደምንሄድ ስለምናውቅ የተቀበልነውን አደራ ለመወጣት የቤተ ክርስቲያናችንን እውነት ከሕዝባችን ጋር ሆነን ለዓለሙ ሁሉ
አሰምተን በመናገር ታሪካዊ ክብሯን መጠበቅና ማስጠበቅ እንደምንችል ምንም ጥርጥር
የለውም፡፡

‹‹ቢቻላችሁ ከሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ›› ተብሎ እንደተጻፈው የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና፣መንፈሳዊ ተልእኳዋንና ክብሯን በጠበቀ መልኩ ከመንግሥትና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት ጉዳት ስለሌለው ከሁሉም ጋር መልካም ግንኙት በመፍጠር የቀደሙትን ባለውለታዎች ሳንረሳ ለሠሩት ሥራ ዕውቅና በመስጠት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በማስፈጸም ሀገራችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ከፍታ
የሚያወጣ፣በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት ምእመናንና ለሌሎቹም የሚጠቅም ሥራ በመሥራት ለተሻለ ውጤት እንበቃለን፡፡

ነገር ግን የማገዝ አቅም የሌለው ሰው ያማል፣የማረም አቅም የሌለው ይሳደባል የመደገፍ አቅም የሌለው ሰው ይጠልፋል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም አብሮ ይወድቃል፡፡ እንደሚሉት ምሁራን አብሮ ላለመውደቅ ከመጠላለፍና ከመተማማት ይልቅ መተባበር በመካከላችን እንዲኖር ሁላችሁም በጸሎትና በሐሳብ እንድታግዙን አበትእግሥት በሆኑት ቅዱስ አባታችን ፊት አደራ እንላለን ፡፡ (ሮሜ 12፡18)

ያለ ትብብር ምንም ነገር ማድረግ አይቻልም እና የቤቱ ጥንታዊ መልክ አንዱ ያንዱ ምልዐት መሆኑን ተረድተን ‹‹ከወራጁ ከፍ ያለ ማድጋ አይሞላም ዝቅ ያለ ማሰሮ ግን
ይሞላል›› እንደሚባለው በጎውን ምክር ለመምከር
ራሳችን ዝቅ በማድረግ ከቅዱስ አባታችን፣ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እየተቀበልን በሞቱ የዳነውን በደሙ የከበረውን ሕዝበ ክርስቲያን መጠበቅና በአግባቡ ማገልገል ይኖርብናል።

የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን ከማግኘት ጀምሮ ከንዑሳን መዐርጋት እስከ ዐበይት መዐርጋት የደረስነው አባቶችና በውስጥም በውጪም ያላችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ራስን ለቤተ ክርስቲያን ቀኖና ማስገዛት፣ከሐዋርያዊ መንበር የሚወስነውን ውሳኔ የሚሰጠውን መመሪያ አክብሮ መቀበል ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት እንጂ ባርነት አይደለምና እርስ በእርሳችን መነቃቀፉን ትተን ሰላማችን በማጽናት አንድ እንሁን፡፡ የቤቱ መልክ ሰላም፣ፍቅርና አንድነት ነውና ለክፉ ሳይሆን ለበጎ እንፈላለግ።

በመጨረሻም ባልተገባ ሥዕለ ሕሊና የሚያየን ዓለም በመካከላቸው እንደ ገነት በተተከለች ቤተ ክርስቲያን እየኖሩ ‹‹እፎ ኮኑ ለሙስና…እንዴት ለጥፋት ሆኑ›› እንዳይለን ክፉኛ ከሚጎዱ የእርሰ በእርስ ልዩነቶች የሚጠብቀን የጋራ የሆነ የትኩረት አቅጣጫ እንዲኖረንና ነባሩን የቤታችንን መልክ እግዚአብሔር በሰጠን በቤቱ ሕግ ማስቀጠል እንድንችል ለሁሉም ውሉደ ቤተ ክርስቲያን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ (መዝ.73፥18)
አግልግሎታችን ሰማያዊና ምድራዊ መግቦት ስለሆነ መጪውን ዘመን ከሩቅ ተመልክተን ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሚሆን በጎ ሥራ የምንሠራበት በአንድ ልብ ሆነን ለተጠራንበት መንፈሳዊ ተልእኮ የምንተጋበት ጊዜ ያድርግልን የቅዱስ አባታችን ቡራኬ ይድረሰን አሜን ፡፡

‹‹ወስብሐት ለእግዚአብሔር››

ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
አባ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና
የራያ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/abune-dioskoros-cover.jpg 406 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2025-06-03 09:18:322025-06-03 09:18:32ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በተደረገው የአቀባበል ሥነሥርዓት ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ መቋጨቱን ገለጸ። Link to: ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ መቋጨቱን ገለጸ። ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን... Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top