ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የመልካም ምኞት መግለጫ መርሐ ግብር በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተከናወነ
ግንቦት 27ቀን 2017 ዓ/ ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
ግንቦት 27ቀን 2017 ዓ/ ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media
አዳማ ኢትዮጵያ
በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የኖርዲክና የግሪክ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመራው የ“ዝክረ ነዳያን ዘአበዊነ” የበጎ አድራጎት ድርጅት በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ለሚመራው ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርቱ ለምግብ የሚሆን ሰባት መቶ ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ እንደተናገሩት “ኮሌጁን ወደፊት ወደ ዩኒቨርሲቲ ከፍ ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው ብፁዕነታቸው ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን” አቅርበዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የኖርዲክና የግሪክ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም “ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ለኮሌጁ በርካታ ሥራ እየሠሩ ናቸው፡፡ የብፁዕነታቸው ድካም በጣም ትልቅ ነው፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጁ ከተለያየ ክፍለ ሀገር የመጡ ደቀ መዛሙርትን የሚማሩበት ታላቅ ቦታ ነው፡፡ ዝዋይ ቀደም ሲልም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ ጳጳሳት የተገኙበት ቦታ በመሆኑ እገዛ ሊደረግለት እንደሚገባ” አስረድተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው አክለውም ለመጀመሪያ ጊዜ በ“ዝክረ ነዳያን ዘአበዊነ” የበጎ አድራጎት ድርጅት ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው ወደፊትም በቀጣይነት ኮሌጁን እንደሚረዱ ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ በሥራ አመራር (Leadership) የትምህርት ዘርፉ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መልካም ፈቃድ በሥራ አመራር (Leadership) የትምህርት ዘርፉ እንዲያስተምር ባቋቋመው መሠረት ከመላው አህጉረ ስብከት የሚመጡ ደቀመዛሙርትን ከ፳፻፲፪ ዓ.ም ጀምሮ ሲያስተምርና ሲያስመርቅ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፤ከዚህም በተጨማሪ የአብነት ትምህርትም በስፋት የሚሰጥበት፣ የተለያዩ አጫጭር ሥልጠናዎች የሚሰጥበት ቦታ ነው፡፡
ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ ወያድኀኖሙ ለትሑታነ መንፈስ እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል፡፡” መዝ 33፤ 18
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ብሉይ የብሉይ ኪዳንን አስተምህሮ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በጃንደረባው አማካይነት ክርስትናን ከተቀበለች በኋላ የውስጥ እና የውጭ ችግሮች ቢኖሩም ዘመናትን በመሻገር ዶግማዋን እና ቀኖናዋን በመጠበቅ ለዛሬ ደርሳለች፡፡
ለዚህም የክርስትና እምነት ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያሰጥ መንፈሳዊ ጉዞ በመሆኑ አባቶቻችን ሊቃውንት እና ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንድ ላይ በመሆን የሕዝቡ መንፈሳዊ ጉዞ ረዥም እንደሆነ በመገንዘብ እያንዳንዱ ሃይማኖታዊ ትሑፊት ለትውልዱ እንዲተላለፍ ለማድረግ ለቤተ ክርስቲያኒቷ በተሠራላት ሕግ መሠረት በየጊዜው የሚመሯትን አባቶች በመምረጥ ቤተ
ክርስቲያኒቷን እንዲመሩ የሚያደርጉ በመሆኑ በዚሁ መሠረት ባሳለፍነው የ2017 ዓ.ም የግንቦት ርክበ ካህናት ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቷን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንድንመራ አባቶች አደራ ሰጥተውናል፡፡
አደራው ግን እጅግ ከባድ እንደ መሆኑ መጠን አደራውን መወጣት እንድንችል የሁላችንም ኃላፊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከባድ እና ጥብቅ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለማገልገል የምናደርገው ጥረት በመንፈሳዊ መሠረት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያስፈልጋል ለዚሁም የአባቶቻችን ጸሎት እንደሚረዳን እናምናለን፡፡
አሁን በዚህ ዘመን ያለችቷ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሁኔታዋ እናመንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲሁም ሁለንተናዊ የልማት ጉዞዋ እጅግ ውስብስብ እንደመሆኑ መጠን ይህን ለመወጣት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው እኛም በትሑት ልብ ነህምያ የፈረሰችውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ ለመገንባት እኛ ልጆቹ ተነስተን እንሠራለን የሰማይ አባታችንም ያከናውንልናል በማለት የሥራው መጀመሪያ አደርጎ እንደተናገረው አሁንም ከዚህ ትምህርት በመውሰድ በጥልቅ እምነት በጸሎት በአስተዋይነት እና በቁርጠኝነት የሚቃወሙት እና እርሱ ቅጥሩን እንዳይሠራ የሚይፈልጉ ወገኖች ቢኖሩም እነርሱን ተሸግሮ የእግዚአብሔርን አጋዥነት ተስፋ በማድረግ የኢየሩሳሌምንቅጥር መልሶ እንደገነባ ሁሉ ዛሬም ያለብንን ችግር ፈትቶ ትውልዱ ከሚዘፈቅበት
ዓለማዊነት በማላቀቅ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለትውልድ ለማሻገር እኔም ሆንኩኝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደ ነህምያ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን
ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ነህምያ ከሁሉ በፊት ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ መንገዱን ለእግዚአብሔር በመስጠት ያሉ ችግሮችን በማጥናት የፈረሰውን ቅጥር በምሽት ዞሮ በማየት ቅጥሩ ለመፍረስ የቻለበትን ችግር ተረድቶ እንደገና እንዳይፈርስ ለማድረግ ለመገንባት እንደጀመረ ሁሉ ከእኛ ቀደም ብሎ በቦታው ላይ የነበሩት ኣባቶች ዘመናቸው በፈቀደላቸው መጠን እንደሠሩት እኛም ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት እንድትራመድ እንደ ቀድሞ ክብሯ እና ገናናነቷ እንዳትታይ ያደረጓትን ችግሮች በማጥናት እና በማየት በማቀድ መሥራት እንደሚገባን ይጠቁመናል፡፡
እርግጥ በነህምያ ዘመን የነበሩት አንዳንድ ወገኖቹ የእርሱን ሃሳብ እና የእግዚአብሔርን መንገድ ባለመረዳት ቅጥሩን መልሶ መገንባት እንደማያስፈልግ በጦቢያ እና በጌሼም የሚመሩ ተቃዋሚዎች ተነስተው በማስፈራራት እና በማፌዝ ሴራ ቢያሴሩበትም እርሱ ግን እጅ ባለመስጠት እኛ ልጆቹ ተነስተን
እንሠራለን የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል በማለት በጸሎት በንቃት እንደተቋቋማቸው ሁሉ እኛም በዙሪያችን የሚፈጠሩትን ችግሮች ለእግዚአብሔር በመስጠት ቤተ ክርስቲያናችንን በቁርጠኝነት መንፈሳዊ አስተዳደራዊ እና ማኀበራዊ ጉዳዮቿ በአንዳንድ ቢታዎች ላይ የሚታዩ አስተዳደራዊ ክፍተቶችን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ አለመግባባቶችን ፣ የንብረት አያያዝ ችግሮችን ፣በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በማከም በሁሉም አቅጣጫ የሚገኙት ምዕመናን ልጆቻችን ከቤተ ክርስቲያናቸው ጋር ያላቸውን መዳከም ፣ በተለያዩ ምክንያቶች እኛ የበለጠ ባለመሥራ
ታችን ከቤተ ክርስቲያኒቷ የሚርቁ እንዳይኖሩ ፈተናዎችን ለማሻገር ተግተን ልንሠራ ይጠበቅብናል ፡፡
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን
ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ቤተ ክርስቲያን አሁን ያለችበት ዘመን 21 ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደሙ በዘልማድ ብቻ ልንጓዝ ስለማይቻል በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ ያለውንም በመቃኘት ዕቅድ በማውጣት መንፈሳዊ አስተዳደራዊ ማኀበራዊ ክፍተቶችንም በመለየት ተጨባጭ የመፍትሔ ዕቅዶችን
በማውጣት በጥናት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ልትሠጥ ይገባታል፡፡
ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዘመን በውስጥ ብቻ ሆነን ከምንሠራው በበለጠ ከውጭ ካሉትም ከተለያዩ አካላት ጋር ከመንግሥትም ጭምር በአስተዋይነት እና በጥበብ በመቅረብ ቤተ ክርስቲያኒቷ ተከብራ እንድትሻገር ካላደረግን የትውልድን ቅብብሎሽ ሊያደክምብን ይችላል፡፡ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ጎን ለጎን አገልግሎት ለምትሰጣቸውም ሕዝብ በመራራት ልትደርስላቸው ስለሚገባት የቤተ ክርስቲያኗን የውስጥ ሰላም በማጠንከር በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ መነጋገር እንዲችሉ የቤተ ክርስቲያን ድርሻዋ ከፍተኛ በመሆኑ እና ሊሠራ ስለሚገባ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
በመጨረሻም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ባሉን ቀጣይ ሐዋሪያዊ የአገልግሎት ዘመናት በውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የምትገኙ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት የሁላችን ድርሻ ትልቅ በመሆኑ ከፊትለፊታችን ያለውን የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ምላሽ ለመስጠት ሁላችሁም በተወከላችሁበት በተሰጣችሁ
ኃላፊነት ተግታችሁ እንድትሠሩ በአባታዊ ፍቅር አደራ እንላለን፡፡
ሰው በተሰጠው ኃላፊነት ላይ በትጋት በታማኝነት ፣ በቅንነት መሥራት የቤተ ክርስቲያኒቷን ሕልውና ከፍ ስለሚያደርግ በሥራ ቦታም ሆነ በግል ሕይወታችሁ ሰላምን እና መግባባትን ጠብቃችሁ እንድትሠሩ ግጭቶችን እና አለመግባባትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ወሳኝ እና ቤተ ክርሰቲያንም ከዚህ አትራፊ መሆንዋን ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
እግዚአብሔር ለልበ ቅኖች ቅርብ እንደመሆኑ መጠን ልባችንን ቅን በማድረግ ሕዝባችንን እና ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በቅዱስ ሲኖዶስ የተጣለብንን አደራ መወጣት እንድንችል ከቅዱስ አባታችን መመሪያ በየጊዜው በመቀበል የምንሠራ ሲሆን ጸሎታቸውም ይርዳን እያልን በቤተ ክርስቲያንውስጥ ከአንድ ማዕድ እየተቋደስን በሃሰብ ልዩነቶች ውስጥ የሚገኙትን
በማቅረብ በሀገሪቷ ውስጥም በየቦታው በፖለቲካ ምክንያት የሚታዩትን አለመግባባት ተቀርፎ ሰላም እንዲመጣ ድርሻችንን በመወጣት ሕዝቡ ሰላማዊ አየር እንዲተነፍስ እንድናደርግ አምላከ ቅዱሳን እንዲረዳን በመጸለይ በሰላም በኢኮኖሚያዊ ማኀበራዊ የልማት ሥራዎች ከመንግሥት ጋርም ሆነ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የቤተ ክርስቲያናችንን ዋና ተልዕኮ እና መብት በማስጠበቅ አብረን ለመሥራት ዝግጁ መሆናችንን እየገለጽን ፡፡
በዚህ በ2017 ዓ.ም የግንቦት ርክበ ካህናት ከእኔ ጋር የቤተ ክርስቲያኑን መንጋ እንድትጠብቁ የተሠየማችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የተሸማችሁነትን ምልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡
የቅዱስነትዎ ጸሎት እና በረከት በሥራችን ስኬታማ እንድንሆን ይርዳን ፡፡
አመሰግናለሁ።
ግንቦት 25/09/2017 ዓ.ም
አባ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብምዕራብ
ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
‹‹ወዝንቱ ሕጉ ለቤት ዘዲበ ርእሰ ደብር
በተራራው ራስ ላይ ያለው የቤቱ ሕግና ሥርዓት ይህ ነው››
(ሕዝ.43+10)
‹‹አይድዖሙ ሥዕለ ዝንቱ ቤት ይዕቀቡ ኵሎ ሥዕሎ ወትእዛዞ ወይግበርዎ ወዝንቱ ሕጉ ለቤት ዘዲበ ርእሰ ደብር ሥርዓቱንና ሕጉን ይጠብቁና ያደርጉትም ዘንድ የዚህን ቤት ክብርና መልክ ንገራቸው›› በሚለው ቃል ክብሩ የተገለጠው፣የአገልግሎታችን መዳረሻ የሆነው የቤታችን ሕግና ሥርዓት በርቱዕ እምነት ማንነታችንን ቀርጾ፣ ከምግባረ ሃይማኖት ጋር አዋሕዶ ወደ እውነተኛ ወደባችን (ወደክርስቶስ) ለመድረስ የሚያበቃ ከውድቀት የምንጠበቅበት ሕገ ርትዕ መሆኑ የታመነነው፡፡
ከዓለም ሁሉ ከፍ ብሎ የከበረውና የተቀደሰው የእግዚአብሔር ቤት እውነተኛ መልክም የተጨነቁትን ማረጋጋት፣ ተሰፋ ላጡ ወገኖች ተሰፋ መሆን፣ በሕዝቡ መካከል መተማመንን ማስፈን፣ ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን ማወጅ ነው፡፡ የዚህን ቤት ትክክለኛ መልክ፣ መውጫውንና መግቢያውን፣ሥርዓቱንና ሕጉን ተረድተን በማስተዋል እንድንኖርበትም የቤቱ ባለቤት “ቅዱሰ ቅዱሳን” ብሎ ሰይሞታል፡፡ነገር ግን ‹‹እለ አልቦሙ ኀሊና ወልብ የዐቅቡ ግብሮሙ ወሥርቶሙ በዘተአዘዙ ናሁ ሌሊት ትዴግኖ ለመዓልት ፣ ወፀሐይ ይዴግኖ ለወርኀ በከመ ተአዘዘ። አእምሮ የሌላቸው ማሰብ የማይችሉ ግዑዛን ፍጥረታት ከእግዚአብሕር በታዘዙት መሰረት ግብራቸውንና ወሰናቸውን ይጠብቃሉ ፤ሌሊት ትእዛዙንና ሥራዋን ጠብቃ ቀንን ትከተለዋለች፡፡ ፀሐይም በታዘዘው መሰረት ጨረቃን ይከተለዋል፡፡ እያንዳንዳቸውም በሕግና በሥርዓት መኖር ተስኖት ሕግን ሲተላለፍ፣ ሥርዓትን ሲያፍርስ ይታያል፡፡መጽ ሲኖዶስ አንቀጽ 45 ገጽ 22)
በእኛም የአገልግሎት ዘመን የዚህ ቤት ሠሪና አስገኝ የሆነው አምላከ ምሕረት እግዚአብሔር በሚደንቀው የፍቅሩ ዝምታ ታግሶን ነው እንጂ ዓለሙን ሁሉ አቅፎ በሚይዝ ልባቸውና በሰፊ ትክሻቸው ሁሉን ተሸክመው፣ ሕይወታቸው የመላእክት ያህልሆኖላቸው ለደካሞቹ ሲተጉ በኖሩት፣የቤቱን ሕግና ሥርዓት በሚያውቁት አባቶቻችን መንፈሳዊ ተጋድሎ ተጠብቆ የኖረውን የቤቱን ጥንታዊ መልክ የሚለወጡ፣ ከምግባረ ሃይማኖት የሚያድጡ አንዳንድ ጉደለቶቻችን መታያት ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል፡፡
በመሆኑም የቤቱ መልክና ሥርዓት የተዋበ እጅግ ከፍ ያለ ስለሆነ እኛን በክብር ከፍ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት አቅቶን ከዓለም ሕግ፣ ከሥነ ፍጥረት ሥርዓት በታች አሳንሰን ካየነው የቤታችንን ውበት በራሳችን እናጣዋለን፡፡
የልዩነት፣ የጠብ፣ የጭቅጭቅ ቤትም ካደረግነው በክብር ፈንታ ሐሳር፣ በከፍታ ፈንታ ውድቀት በራሳችን ላይ እንዳናመጣ የቤቱን ሥርዓትና ሕግ በጋራ ትብብር ወደነበረበት መመለስ ግድ ይለናል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሠራው፣ አባቶቻችን የደከሙበት
የቤታችን ጥንታዊ መልክ ሰላምና ፍቅር፣ስምምነትና አንድነት፣ቅንነትና አስተዋይነት ጽናትና ደግነት ነው:: እንዲህ ያለ መልክና ውበት ባለው ቤት ስንኖር ደግሞ የዓለም መልክ ሊታይብን አይገባምና መልካችን አምላካዊ፣ አለባበሳችን ሃይማኖታዊ፣አኗኗራችን ሰማያዊ መሆን ይኖርበታል፡፡
ከቤቱ መልክ ወጥተን እርስ በእርሳችን ከተለያየን ለማይጠገን ስብራት፣ለማይታረም ስሕተት የምንዳረግ እንሆናለንና አንድም ነገር ሳይጎድልብን በፍጹም ደስታ የሚያኖረንን ይህን ቤት በክብር እንጠብቀው፡፡ወደፊትም ከአለፈው ታሪካችን እየተማርን፣ በቤቱ ሕግና ሥርዓት፣ በጋራ ውይይት ስሕተቶቻችንን እያረምን ትውልዱ ከእውነትና ከታሪካዊ መረጃ የራቀ እንዳይሆን መሥራት የመሪነት ተግባራችን ነው፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ክቡራንና ክቡራት ልጆቻችን!
“ከሁሉ በተቀደሰው፣ በዙሪያው ካሉት ሀሉ ከፍ ባለው” የእግዚአብሔር ቤት እንደየደረጃችን ለአገልግሎት ስንጠራ መዐርጉንና ሀብቱን፣ የመከበር ዕሴቱንና ዐስቡን ብቻ ሳይሆን የሥልጣኑ ምንጭ፣ የተልእኮው ሥምረት፣ የማዕረጉ ድምቀት ለሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቦታ አሠራር በሚያመች ሕይወት ካገለገልን አገልግሎታችን በፍቅር ይጸናል፡፡ የሚማርክ መዓዛ ቅድስና ያለው ሕይወት፣የሚዘከር ማንነት ይኖረናል።
በመሆኑም ‹‹ከመንፈስ ቅዱስ ተለይተን እኛ ለእግዚአብሔር እንግዶች ነንና››በእርሱ እየተመራን በተሠጠን የአገልግሎት ጊዜ እንቅፋቶችን ሁሉ በጋራ በማስወገድ ሐዋርያዊ መሠረት ያለውን አንድነታችንንና ሰላማችንን በማጽናት፣ በምድር ሆነን በሰማይ ሥርዓት እየኖርን ለሀገራችን እድገት፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት መስፋፋት ከልብ መሥራት ይገባናል ፡፡ (ቅዱስ አትናቴዎስ)
ሁላችሁም እንደምታስታውሱት እኔና ወንድሜ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከአሁን በፊት በዚሁ ቤት አብረን አገልግለናል፡፡ ሰውንና እግዚአብሔርን ለማገልገል ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠን የሦስቱ ዓመታት የአገልግሎት ዘመንም የልባችንን እልፍኝ ሰፋ አድርገን የሚጠበቅብንን ለመሥራት፣ የሁሉም ልጆቻችን አባቶች ሆነን ሁሉንም በእኩልነት ለማገልገል እንሠራለን ብለን እናምናለን፡፡
ለቤቱ ክብር በሚመጥን በመልካም ምግባር በተጌጠ ሕይወት በዚህ መንገድ መሥራትና ማስተዳደር ከቻልን ከየት ተነሥተን ወዴት እንደምንሄድ ስለምናውቅ የተቀበልነውን አደራ ለመወጣት የቤተ ክርስቲያናችንን እውነት ከሕዝባችን ጋር ሆነን ለዓለሙ ሁሉ
አሰምተን በመናገር ታሪካዊ ክብሯን መጠበቅና ማስጠበቅ እንደምንችል ምንም ጥርጥር
የለውም፡፡
‹‹ቢቻላችሁ ከሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ›› ተብሎ እንደተጻፈው የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና፣መንፈሳዊ ተልእኳዋንና ክብሯን በጠበቀ መልኩ ከመንግሥትና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት ጉዳት ስለሌለው ከሁሉም ጋር መልካም ግንኙት በመፍጠር የቀደሙትን ባለውለታዎች ሳንረሳ ለሠሩት ሥራ ዕውቅና በመስጠት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በማስፈጸም ሀገራችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ከፍታ
የሚያወጣ፣በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት ምእመናንና ለሌሎቹም የሚጠቅም ሥራ በመሥራት ለተሻለ ውጤት እንበቃለን፡፡
ነገር ግን የማገዝ አቅም የሌለው ሰው ያማል፣የማረም አቅም የሌለው ይሳደባል የመደገፍ አቅም የሌለው ሰው ይጠልፋል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም አብሮ ይወድቃል፡፡ እንደሚሉት ምሁራን አብሮ ላለመውደቅ ከመጠላለፍና ከመተማማት ይልቅ መተባበር በመካከላችን እንዲኖር ሁላችሁም በጸሎትና በሐሳብ እንድታግዙን አበትእግሥት በሆኑት ቅዱስ አባታችን ፊት አደራ እንላለን ፡፡ (ሮሜ 12፡18)
ያለ ትብብር ምንም ነገር ማድረግ አይቻልም እና የቤቱ ጥንታዊ መልክ አንዱ ያንዱ ምልዐት መሆኑን ተረድተን ‹‹ከወራጁ ከፍ ያለ ማድጋ አይሞላም ዝቅ ያለ ማሰሮ ግን
ይሞላል›› እንደሚባለው በጎውን ምክር ለመምከር
ራሳችን ዝቅ በማድረግ ከቅዱስ አባታችን፣ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እየተቀበልን በሞቱ የዳነውን በደሙ የከበረውን ሕዝበ ክርስቲያን መጠበቅና በአግባቡ ማገልገል ይኖርብናል።
የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን ከማግኘት ጀምሮ ከንዑሳን መዐርጋት እስከ ዐበይት መዐርጋት የደረስነው አባቶችና በውስጥም በውጪም ያላችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ራስን ለቤተ ክርስቲያን ቀኖና ማስገዛት፣ከሐዋርያዊ መንበር የሚወስነውን ውሳኔ የሚሰጠውን መመሪያ አክብሮ መቀበል ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት እንጂ ባርነት አይደለምና እርስ በእርሳችን መነቃቀፉን ትተን ሰላማችን በማጽናት አንድ እንሁን፡፡ የቤቱ መልክ ሰላም፣ፍቅርና አንድነት ነውና ለክፉ ሳይሆን ለበጎ እንፈላለግ።
በመጨረሻም ባልተገባ ሥዕለ ሕሊና የሚያየን ዓለም በመካከላቸው እንደ ገነት በተተከለች ቤተ ክርስቲያን እየኖሩ ‹‹እፎ ኮኑ ለሙስና…እንዴት ለጥፋት ሆኑ›› እንዳይለን ክፉኛ ከሚጎዱ የእርሰ በእርስ ልዩነቶች የሚጠብቀን የጋራ የሆነ የትኩረት አቅጣጫ እንዲኖረንና ነባሩን የቤታችንን መልክ እግዚአብሔር በሰጠን በቤቱ ሕግ ማስቀጠል እንድንችል ለሁሉም ውሉደ ቤተ ክርስቲያን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ (መዝ.73፥18)
አግልግሎታችን ሰማያዊና ምድራዊ መግቦት ስለሆነ መጪውን ዘመን ከሩቅ ተመልክተን ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሚሆን በጎ ሥራ የምንሠራበት በአንድ ልብ ሆነን ለተጠራንበት መንፈሳዊ ተልእኮ የምንተጋበት ጊዜ ያድርግልን የቅዱስ አባታችን ቡራኬ ይድረሰን አሜን ፡፡
‹‹ወስብሐት ለእግዚአብሔር››
ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
አባ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና
የራያ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ