የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቀ ።

June 29, 2025

ሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ ተዘጋጅቶ የሚተላለፉ ማንኛቸውም ትምህርቶች ፣ መዝሙራት ፣ ቪዲዮዎች ፣ ቃለ መጠይቆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖናን የጠበቁ መሆናቸው ሙሉ የአርትኦት / ኦዲቶርያል ስራዎች/ ከገዳማችንና ከሰንበት ትምህት ቤታችን በተመደቡ አባቶች እና መምህራን አማካኝነት ሲረጋገጥ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በዚህ መሠረት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፣ ትምህርቶችን እና መዝሙራትን በማቅረብ ምዕመናን ወደ ንስሀና ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀርቡ ለማድረግ ፣ የቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊ ቦታዎች ማስተዋወቅ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና መምህራንን የህይወት ተሞክሮ ለትውልዱ በማስተዋወቅ አሰረ ፍኖታቸውን እንዲከተሉ ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የጻድቃን ሰማዕታት ተጋድሎ እና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጸጋ ለማስተዋወቅ ብቻ እንዲተላለፉ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን ፣የቤተክርስትያንን ስርዓቶች ለትዉልዱ ለማስተዋወቅ፣ ትዉልዱ ምንነታቸዉን ተረድቶ እንዲጠቀምባቸዉ እና እንዲጠብቃቸው ፣መስማት ለተሳናቸዉ የቤተክርስትያኒቱ ልጆች በቋንቋቸዉ ተከታታይ ትምህርቶችን እንዲማሩ ለማድረግ፤ የቤተክርስትያናችንን፤ የገዳማችንን እና የሰንበት ት/ቤታችንን መንፈሳዊ እና የልማት ስራዎችን ለምዕመና ይሀንን ለትዉልዱ እና ለቤተክርስትያን ጠቃሚነቱ የታመነበትን (ዘመናዊ ስቱዱዮ ) ገንብተን ስራ ለማስጀመር፣ ለዚሀ የምረቃ ቀን እንድንበቃ ለረዳን ለመድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ይሁን በማለት ብፁዕነታቸውን እና የገዳሙን አስተዳደር ጽ/ቤት አመስግነዋል ።

በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የቅድስት ሥላሴ መንፋሳዊ ዩንቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የኢትዮ ሶማሊያ ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ መልዓከ ምህረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የጋዳሙ ዋና አስተዳዳሪ፣ የገዳሙ የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የተምሮ ማስተማር ሥራ እልስፈጻሚዎች በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል ።

በመቀጠል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ይህ ዘመናዊ ስቱዱዮ መልካም ነገር የሚሰራበት የቤተ ክርስቲያንን ህግ ደንብ የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥ መሆን እንዳለበት ለቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ ጉዞዋ አስፈላጊ ስለሆን እናንተም መበርታት መጠንከር ፣ መጸለይ አለባችሁ እኛም ይህንን መልካም ነገር ማየታችን በጣም ደስ ብሎናል ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከ24 ዓመት በፊት በዚህ ገዳም አስተዳዳሪ በነበርኩበት ወቅት ተምሮ ማስተማር አንጋፋ እና ስመጥር የሆኑ የሀገር ባለውለታዎች የሚፈልቁበት ነው በሰንበት ትምህርት ቤት በማኅበራት እንዲሁም በዘመናዊ ትምህርት ቤት በመጀመር ምስካየ ኅዙናን ቀዳሚ ነው እና ብዙ መልካም ስራዎች ከዚህ በኃላም እንደሚሰሩ ተስፋ አለኝ ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል ።

©ምስካየኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከቤተክርስቲያናችን የኮሪደር ልማት ዐቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከቤተክርስቲያናችን የኮሪደር ልማት ዐቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከቤተክርስቲያናችን... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን “ሕገ_ቤተክርስቲያንና_ልማት” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የልማት ኮሚቴ አመራሮችና አባላት የተዘጋጀ ስልጠና ተካሄደ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን “ሕገ_ቤተክርስቲያንና_ልማት” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የልማት ኮሚቴ አመራሮችና አባላት የተዘጋጀ ስልጠና ተካሄደ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top