ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የደምቢ ደሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራልን ቅዳሴ ቤት አከበሩ።
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር በዛሬው ዕለት በ27/07/2016 በደምቢ ዶሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራል በመገኘት የታደሰውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመባረክ፣ ቅዳሴ ቤቱን አክብረዋል።
የብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሐዋርያዊ ጉዞ
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት (26/07/2016) ሐዋርያዊና መንፈሳዊ ጉዞአቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ደምቢ ዶሎ በማድረግ ላይ እንዳሉ በዳሌ ሰዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጫሞ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በቁልቢና አካባቢው ልዩልዩ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ ውሳኔ ተለይተው ተላልፏል።
መጋቢት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
የጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የሐዋርያት አንድነት ኑሮ ማኅበር በማሰልጠኛ ማዕከሉ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ ።
የጽርሐጽዮን ዘተዋሕዶ የሐዋርያት አንድነት ኑሮ ማኅበር የሰባክያነ ወንጌልና የአብነት ትምህርት ማሠልጠኛ ለቤተክርስቲያን ዘቢብ ጧፍ ጥላ ሻማ ብቻ ሳይሆን ሰውንም እንስጥ በሚል መሪ ቃል የተቋቋመ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ከልዩ ልዩ አህጉረ ስብከቶች የተወጣጡ ሰልጣኞችን በየቋንቋቸው አሰልጥኖ አስመርቋል።
የመልአከ ፀሐይ መኰንን ደስታ ግብአተ መሬት ተፈጸመ።
ረጅሙን የሕይወት ዘመናቸውን ቤተክርስቲያንን በሀገር ውስጥና በሰሜን አሜሪካ በቅንነትና በትህና ሲያገለግሉ የኖሩት የመልአከ ፀሐይ መኰንን ደስታ ጸሎተ ፍትሐትና ሽኝት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በአሮጌው ቄራና በጠቅላይ ቤተክህነት በግንባታ ላይ የሚገኙትን ሕንጻዎች የሥራ አፈጻጸም ተዘዋውረው ተመለከቱ።
መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የምክክር ጉባኤ በጠቅላይ ቤተክህነት በመካሔድ ላይ ነው።
መጋቢት ፲ቀን፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ እንድትሆንና በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ተገቢው ክብርና እውቅና እንዲሰጣት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ጥረት እንዲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አሳሰበ።
መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም.
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው መግለጫ ሰጡ፣
ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፤ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡ ስንጾም መገዳደልን፣ መጣላትን፣ መለያየትን፣ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አለብን፤ ከክፉ ኅሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በምግባረ ሰናይ ሆስፒታል የሚከናወኑ የማስፋፊያ ሥራዎችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እንደገለጹት የሆስፒታሉን አገልግሎት ለማዘመንና ለማስፋፋት እየተከናወነ ያለው ሥራ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን ገልጸው የግንባታ ሥራው በታቀደለት ጊዜ ተከናውኖ ወደ ሥራ መግባት እንዲችል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።