ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የአቀባበል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በከንባታ ሐላባና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት በዱራሜ መንበረ ጵጵስና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከናወነ።
ዱራሜ
====
ሐምሌ ፲፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
ለብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በከምባታ ሐላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከት በዱራሜ መንበረ ጵጵስና አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
ሐምሌ ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””
ዱራሜ
ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ
ዓመታዊው የስብከተ ወንጌል ቀን በድምቀት እየተከበረ ነው።
ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም አዲስ አበባ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በአፋን ኦሮሞ የተተረጎሙ ሁለት መጽሐፍት ተመረቁ።
በዕለቱ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተክህነት ሊቃነ ካህናት ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተክርቲያን ፣የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት፣ የማኀበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል አባላትና ዘማርያን እንዲሁም በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።
የምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ከአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
ሰኔ ፯ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም አዲስ አበባ
ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር ቅዱስ ሲኖስ ያወጣውን የማኅበራት ምዝገባ መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠው።
ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
የገዳማት አበ ምኔቶች እና እመ ምኔቶች በቤ ተክርስቲያችን ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡
ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ
የኢኦቴቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የቀጥታ የሳተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭት ለመጀመር ባከናወነው ተግባር ለተሳተፉ አካላት የምስጋና ፕሮግራም እያካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ በችግር ሰዓት የቆመ ጣቢያ መሆኑን ጠቅሰው በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደብዳቤ መነሻነት ለተራዱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ሌሎች አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የ፳፻ ፲፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማጠቃለያ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡