የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

መንፈሳዊ ፍርድ ቤት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀገር አቀፍ ደረጃ በብሔራዊ ሃይማኖት በነበረችበት በቀድሞው ዘመነ መንግስት ቤተክርስቲያኒቴ ያሏትን መንፈሳዊ እሴቶች ፣ ባህሎችና አስተምህሮዎች በወቅቱ በነበረው ሥርዓተ መንግሥት መዋቅራዊ አደረጃጀት ውስጥ ማስረጽ ችላ ነበረ፡፡

ለአብነትም ያህል የቤተክርስቲያኒቱ ሕግ የሆነው ፍትሐ ነገሥት የሀገሪቱ የበላይ ህግ ሆኖ ከማገልገሉም በተጨማሪ በወቅቱ በመንግሥታዊ ,ፍርድቤቶች በዳኝነት ተመድበው ፍትሕ ና ርትዕ ይሰጡ የነበሩት የቤተክርስቲያኒቱ የፍትሐ ነገሥት መምሕራንና ሊቃውንት እንደነበሩ በልዩ ልዩ የታሪክ ድርሳናት ተመዝግበው ይገኛሉ፡፡

ለአብነትም ያህል ለ900 ዓ.ም በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያው የመንግስት ፍርድ ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የአፈር ዳኛ ፣የአከል ዳኛ፣ሻለቃ ፍርድ ቤት፣ አፈ ንጉስና ንጉሰ ነገሥት፣ዙፋን ችሎት በማለት አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት በተሠራበት ወቅት መዋቅራዊ አደረጃጀትን በመሥራትና በእያንዳንዱ የዳኝነት መዋቅር ውስጥ የቤተክርስቲያኒቱ የፍትሐ ነገሥት መምህራን ተመድበው በመሥራት ዛሬ አደገ ተመነደገ ተብሎ የሚነገርለትን የፍትሕ ሥርዓት ከዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከጽንሰቱ እስከ ውለደቱ ብሎመ እስከ እድገቱ በቤተክርስቲያኒቱ እንቁ ሊቃውንት ልጆች አማካኝነት እሰከ ዓለም ፍጻሜ ሲዘክረው የሚኖር አኩሪ ታሪክ የሠራች እናት ቤተክርስቲያን መሆኗን እንኳንስ እኛ ልጆቿ  ይቅርና የማያምኑትን እንኳን ሳይቀሩ ሀገረ መንግሥት ምሥረታ በማጽናት እራሷ ሀገር የሆነች እናት ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ዘወትር በየአደባባዩ በኩራት ሲመሰክሩላት ይገኛል፡፡

የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ታሪካዊ ዳር

ፍርድ ቤቶች የሰውን ልጅ መብት ለማስከበሪያ ዜጎች መብቶቻቸውን በተጣሱባቸውና ባልተከበሩባቸው ወቅት ይህን የመብት ጥሰት ከሀገሪቱ ሕጎች ድንጋጌ አንጻር መርምረውና ተመልክተው ፍትሕና ርትዕ ለመስጠት መሆናቸው አጠያያቂ አይደለም ፡፡

ከላይ የተገለጸው የመንግሥታዊ የዳኝነት ሥርዓት መዋቅራዊ አደረጃጀት እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግሥታዊ የዳኝነት ሥርዓት ሊሸፈኑ የማይችሉትን የዳኝነት ዓይነቶችን ደግሞ መንፈሳዊ ነክ የሆኑትን በመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ባህል ነክ የሆኑትን ጉዳዮች ደግሞ እንደየአካባቢው ወግና ሥርዓት በባህላዊ የዳኝነት ሥርኣት እንዲታዩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት አሁን የምንያቸው በየደረጃው ያሉት መንፈሳዊ ፍርድቤቶች ሊቋቋሙና ሊመሰረቱ ችለዋል፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ አሁን ላለነው ትውልድ ተላልፈው ዛሬም ድረስ ፍትሕ ና ርትዕ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ይህንንም መሠረት አድርጎ በአሁኑ ሠዓት የሀገሪቱ የበላይ ሕግ በሕገ መንግስቱ እውቅና የተሠጣቸው መሆኑና የመቋቋሚያ አዋጅ ጥያቄ ሲቀርብም በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ የሕዝብ እንደራሴ ምክርቤቶች በመቋቋሚያ አዋጅ እንዲቋቋሙ የማድረግ ሐላፊነት ያለባቸውን ስለመሆኑ ለሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78/5/ ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቾች ሕገ መንግስታዊ ዕውቅና ያላቸው ቢሆንም የኤፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስከ አሁን ድረስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች የማቋቋሚያ አዋጅ ባለመፍቀዱ ለዘመናት በርካታ ፍትሕና ርትዕ ሲሰጥባቸው የቆዩ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶቻችን ጥርስ የሌለው አንበሣ ሆነው እነኳንስ በመንግሥታዊ አስፈጻሚ አካላት ዘንድ ይቅርና በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ በየደረጃው ያሉ አስፈጻሚ አካላት ዘንድ በማስፈጸም አስቸጋሪ መንፈሳዊ ፍርድቤቶቻችን በመኖርና ያለመኖር ሥጋት ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም ይህ ለመንፈሳዊ ፍርድቤት ተግዳሮት የሆነውን የማቋቋሚያ አዋጅ በኤ.ፌ.ድ.ሪ.የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማጽደቅ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት ረቂቅ አዋጁን አዘጋጅተን እንድናቀርብ በምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ በተሰጠው አመራር መሠረት የአዋጁን ረቂቅ በብቁ የሕግ በላሙያዎች ተዘጋጅቶ ለቅዴስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ በአጀንዳነት ተይዞ ይገኛል በመቀጠል በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር ሪፖርት በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ገዳማት አስተዳደር መምሪያ Link to: ገዳማት አስተዳደር መምሪያ ገዳማት አስተዳደር መምሪያ Link to: ቅርስ ጥበቃና ቤተመጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ Link to: ቅርስ ጥበቃና ቤተመጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ቅርስ ጥበቃና ቤተመጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top