የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅርስ ጥበቃና ቤተመጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ/ቤት የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በዘመናዊ  መልክ  ተደራጅቶ የማስጎብኝቱን ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በውስጡም የንዋየ ቅድሳት እና  የተለያዩ  ታሪካዊ እና ኃይማኖታዊ መጻሕፍትና ድርሳናትን  በአንድ ላይ  በማሰናዳት  ለጎብኝዎች ፤ለጥናትና  ምርምር  ሥራዎች  እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች  እንዲውሉ  ተደረትገው ለጉብኝት ዝግጁ በመሆን አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል ፡፡ የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ሶስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም፡.-የቅርስ ጥበቃ -ቤተ-መጻሕፍት -ቤተ-መዘክር የሚሉት ናቸው፡፡

በቤተ መዘክሩ የታችኛው ወለል የተለያዩ መጻሕፍቶች፣   ሃይማኖታዊ ታሪካዊ  ሰነዶች ፤ የሚገኙ ሲሆኑ፡- በላይኛው  የቤተመዘክሩ ወለል ደግሞ የቅዱሳን ፓትርያርኮች የመገልገያ ንዋየ ቅድሳት  (የእጅ መሰቀል፤  የመጾር መሰቀል …ወዘተ.) ፎቶግራፎች በአግባቡ ተደራጅተው ለጎብኝዎች ዝግጁ ሆነው የተሰናዱ ናቸው፡፡ በ2014 ዓ/ም በጀት ዓመት በመምሪያው በእቅድ ተይዘው የተከናወኑትን እና ሳይከናወኑ የቀሩባቸውን ምክንያቶች (ችግሮች) አስመልክቶ  ዝርዝር የሥራ ሪፖርት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

፩.- በ2014 ዓም  የተሠሩ ሥራዎች

  1. ከባሕልና ቱሪዝም፣ ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲሁም አዲስ አበባ ቱሪዝም ቢሮ እና መሰል ተቋማት ጋር  በመቀናጀት ቅርስን አስመልክቶ  ለመምሪያው ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡
  2. በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አዲስ የታተመው የግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስ በቁጥር 20 የሚሆኑ ለቤተመጻሕፍት አገልግሎት በነጻ ለሙዚየሙና ለቤተመጻሕፍት አገልግሎት እንዲውል  ደብዳቤ ተጽፏል፡፡
  3. 25የሚደርሱ የወሎ ዮኒቨርስቲ የግዕዝ ዲፓርትመንት ተማሪዎች የብራና መጻሕፍትን በማየትና ወደፊት ለምርምርና ጥናት አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻህፍቶች እንዳሉ  እና አጠቃላይ ቤተመጻሕፍቱን በመጎብኝት ለቀሩት ማኅበረሰብ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ታሪክና ቅርስን የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሰሩና  ቃል ገብተዋል፡፡
  4. በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ላልይበላ አስተዳደሪ ቆሞስ አባ ጽጌ  እና   ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ፤  የዩኒስኮን አፍሪካ ዋና ጸሐፊ እና ተወክለው በመጡ የውጭ ሃገር ሰዎች ጋር በመገኛኝት የቅዱስ ላልይበላን ቅርስ ከጦርነቱ በኃላ ያለበትን ሁኔታና ወደፊት ስለሚጠገኑት አብያተ ክርስቲያናት የፕሮጀክት ሥራ  ውይይት ተደርጓል፡፡
  5. ሙዚየሙን የማስጎብኝትና ቤተመጻሕፍቱን (Library) ለተጠቃሚዎች ክፍት በማድረግ የተለመደውን የዘወትር አገልግሎቱን ለሁሉም ማኅበረሰብና በተገቢው መልኩ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
  6. ከመንግስት መ/ቤት ማለትም ከቤተመጻሕፍት ወመዘክር ጋር ወደፊት  በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding) ተዘጋጅቶ  ወደሥራ ለመግባት ዝግጁ  እንዲሆን ተደርጓል፡፡
  7. የብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና ብፁዐን አበው አባቶች (ሊቃነ ጳጳሳት) አረፍተ ዘመን ሲገታቸው መጻሕፍቶቻቸው የመባረኪያ የእጅ መስቀላቸውና የመሳሰሉት  ወደ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር  በሕጋዊ ደብዳቤ ገቢ እንዲሆን ተደረጓል ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መንፈሳዊ ፍርድ ቤት Link to: መንፈሳዊ ፍርድ ቤት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት Link to: የጥምቀት በዓል አከባበር  በአኃት አብየተ ክርስቲያናት፤ በምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያንና በምዕራቡ ዓለም  Link to: የጥምቀት በዓል አከባበር  በአኃት አብየተ ክርስቲያናት፤ በምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያንና በምዕራቡ ዓለም  የጥምቀት በዓል አከባበር  በአኃት አብየተ ክርስቲያናት፤...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top