ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

“ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ” በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉብኝትና ቡራኬ ተጠናቀቀ።

ሚያዚያ ፲፬ቀን፳፻፲ወ፮ ዓ/ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አዘጋጅነት ‹‹ኦርቶዶክሳዊ ብዙኃን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን›› በሚል መሪ ቃል በተደረገው የሥልጠና፣ ውይይትና የምክክር መርሐ-ግብር በተሳተፍን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የቀረበ የአቋም መግለጫ፤

ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ/ም

ኦርቶዶክሳውያን ብዙኃን መገናኛ ተቋማትና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሐሰተኛ ወሬ ባለመቀበል እና ባለማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን ሊውጡ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አሳሰቡ።

“ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በጣስ መልኩ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን እና ሥርዓተ አምልኮ በዲጂታል ሚዲያ የሚያስተላልፉ አገልጋዮች እና ሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከድርጊታቸው መቆጠብ ይገባቸዋል” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ኦርቶዶክሳውያን ብዙኀን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የኢ.ኦ.ተ.ቤ. ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ “ኦሮቶዶክሳዊያን ብዙኀን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን” በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለት የሥልጠና፣ የምክክርና የውይይት መድረክ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሂዷል።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል  የደምቢ ደሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራልን ቅዳሴ ቤት አከበሩ።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል  የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር  በዛሬው ዕለት በ27/07/2016 በደምቢ ዶሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራል በመገኘት የታደሰውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመባረክ፣ ቅዳሴ ቤቱን አክብረዋል።

የብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሐዋርያዊ ጉዞ

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት (26/07/2016) ሐዋርያዊና መንፈሳዊ ጉዞአቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ደምቢ ዶሎ በማድረግ ላይ እንዳሉ በዳሌ ሰዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጫሞ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በቁልቢና አካባቢው ልዩልዩ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ ውሳኔ ተለይተው ተላልፏል።

መጋቢት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም

የጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የሐዋርያት አንድነት ኑሮ ማኅበር  በማሰልጠኛ ማዕከሉ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ ።

የጽርሐጽዮን ዘተዋሕዶ የሐዋርያት አንድነት ኑሮ ማኅበር የሰባክያነ ወንጌልና የአብነት ትምህርት ማሠልጠኛ  ለቤተክርስቲያን  ዘቢብ ጧፍ   ጥላ  ሻማ ብቻ ሳይሆን ሰውንም እንስጥ በሚል  መሪ ቃል የተቋቋመ ማሰልጠኛ ማዕከል  እንደመሆኑ መጠን ከልዩ ልዩ አህጉረ ስብከቶች የተወጣጡ ሰልጣኞችን  በየቋንቋቸው አሰልጥኖ አስመርቋል።

የመልአከ ፀሐይ መኰንን ደስታ ግብአተ መሬት ተፈጸመ።

ረጅሙን የሕይወት ዘመናቸውን ቤተክርስቲያንን በሀገር ውስጥና በሰሜን አሜሪካ በቅንነትና በትህና ሲያገለግሉ የኖሩት የመልአከ ፀሐይ መኰንን ደስታ ጸሎተ ፍትሐትና ሽኝት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በአሮጌው ቄራና በጠቅላይ ቤተክህነት  በግንባታ ላይ የሚገኙትን ሕንጻዎች የሥራ አፈጻጸም ተዘዋውረው ተመለከቱ።

መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

ለውስጥ አገልግሎት

የኢሜይል አገልግሎት

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል