የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ለብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በከምባታ ሐላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከት በዱራሜ መንበረ ጵጵስና አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

July 20, 2024

ሐምሌ ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””
ዱራሜ
**
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የከንባታ፣ሐላባ፣ጠንባሮ፣
ዳውሮና ኮንታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በከምባታ ሐላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከት በዱራሜ ከተማ በሚገኘው  መንበረ ጵጵስና አ/ተ/ሃይል ማኖት ቤተክርስቲያን ሐምሌ ፲፫ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዐ ዓ/ም ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻ ወ፮ ዓ.ም ባደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፀዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የከምባታ ሐላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በዛሬው እለት ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተጉዘዋል። ይህንን ተከትሎም በዱራሜ ከተማ መንበረ ጵጵስና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ሥነሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሰሜን አሜሪካ የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ሊ/ት እስክንድር ገብረክርስቶስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሕውብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ፣የሀገረ ስብከቱ የየክክሉ ኃላፊዎች፣ ተገኝተዋል።

በዚሁ የአቀባበል ሥነሥርዓት ላይ ቃለ ቡራኬ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በከምባትኛ ቋንቋ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ብፁዓን አባቶች ይሄንን ደግ ህዝብ      ለማየት ስላበቃችሁ እድለኞች ናችሁ።እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ሀገረ ስብከቱን በሁለንተናዊ ልማት ተቀዳሚ ለማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተባበር እንደሚሰሩ በመግለጽና ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና በማቅረብ አባታዊ መልዕኮታቸውን  አጠቃለዋል።

በበዓሉ ላይ በብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን በሊቃውንተ ቤተከርስቲያንና በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል፤ሊቃውንትም ልዩለዩ ቅንያትን አቅርበዋል።በአቀባበል ሥነሥርዓቱ ላይ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሀሆኑ ምዕመናንና ወጣቶች ከከተማው ወጥተው በመኪና፣በባጃጅና በሞተር ብስክሌት በማጀብ ደማቅና በአይነቱ ልዩ የሆነ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ Link to: ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም... Link to: የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የአቀባበል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በከንባታ ሐላባና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት በዱራሜ መንበረ ጵጵስና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከናወነ። Link to: የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የአቀባበል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በከንባታ ሐላባና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት በዱራሜ መንበረ ጵጵስና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከናወነ። የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የአቀባበል ማጠቃለያ መርሐ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top