ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለማኅሌት አገልግሎት ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው የማኅሌተ ጽጌ መጽሐፍ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጎመ። ይህንን የአባ ጽጌ ድንግል ድርሰት የሆነው መጽሐፍ የተረጎሙት የፊንላንድ ሀገር ዜጋ የሆኑት እና ከሃምሳ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቆይታ ያደረጉት አቶ ኒሎ ሆንካነን ናቸው። ተርጓሚው መጽሐፉ ወደ ፊንላንድኛ ለመተርጎም ከ10 ዓመት በላይ ሲያጠኑ እንደቆዩና ዋና ምንጭ አድርገው የተጠቀሙት ደግሞ በ1919 ዓ.ም. በዶ/ር አዶልፍ ግሮህማን የተተረጎመውን የጀርመንኛ ቅጅ እንደሆነ ገልጸዋል።

የብፁዕ አቡነ ሰላማ ክቡር አስከረን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጓዘ።

በሀሌሉያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትላንትናው እለት ከዚህዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ክቡር አስከሬናቸው ወደበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸልተ ፍትሐት ሲደረግበት እንዲያድር እና በነገው እለት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አስፈላጊው ሥርዓት ከተፈጸመለት በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ እንዲፈጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጉዟል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ዕረፍትን በማስመልከት ያስተላለፉት አባታዊ የሐዘን መግለጫ

. . . ብፁዕነታቸው በዕረፍተ ሥጋ ከእኛ በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ቢሰማንም በሰማይ የሚጠብቃቸውን ክብር እያሰብን እንጽናናለን።

የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።

ዜና እረፍት – ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ጸሎተኛው፣ደጉ፣ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።

የ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከብሮ በመዋሉ ቅድስ ቤተክርስቲያን ምስጋናዋን ታቀርባለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሮ የሚውለው የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ መዋል ይቻል ዘንድ ፲፫ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማደራጀት ስኬታማ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ስታከናውን መሰንበቷ ይታወሳል።

የ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት በመከበር ላይ ነው።

የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት በመከበር ላይ ነው።በበዓሉ ሊይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣የከተማችን አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣አምባሳደሮች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ካህናት፣ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል።

የመስቀል ደመራ በዓል የአከባበር ሥነ ሥርዓት ዝግጅት ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ከምታከብራቸው የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱና በዓለም አቀፉ የትምህርት ሳይንስና ባህል ጅርጅት በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል ።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ ዶክተር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የ2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አስመልክቶ የሊቃውንት ወረብ ጥናት ልምምድን ጎበኙ።

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ከሚገኙ ገዳማትና አድባራት የተውጣጡ ብዛታቸው 800 የሚደርሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በ2016 ዓ.ም የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል በተለየ ድምቀት ለማክበር ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ግቢ በዓሉን የተመለከተ የወረብ ጥናት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ/ም በተደረገው የወረብ ጥናት መርሐ ግብር ወቅት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ለሠልጣኞቹ የማበረታቻ ሐሳብና ቡራኬ ሰጥተዋል።

ዓለም በሚቀማበት ወቅት ጊዜውን፣እውቀቱን፣ገንዘቡን ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ እንደእናንተ አይነት ልጆች ስላሉን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም የ6 ወራት የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል።

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

ለውስጥ አገልግሎት

የኢሜይል አገልግሎት

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል