ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደ.መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል መርሐ ግብር የተሳካ እንዲሆን ላደረገው አስተዋጽጾ ምጋና ተቸረ።

የቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም መመለስን አስመልክቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለቅዱስነታቸው ክብር በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀው መርሐ ግብር የተሳካና ውጤታማ መሆን ይችል ዘንድ የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታና የደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ሊቃውንትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለመርሐ ግብሩ የሚመጥኑ ልዩልዩ ያሬዳዊ ዜማዎችን በማቅረብ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አድርገዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የአሜሪካ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰሜን አሜሪካ ሲያደርጉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ ወንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።

ከነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።

የቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተሞች ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የ፳፻ ፲ወ፭ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አደረገ፤ በሥራ አፈጻጸም ውጤት ያስመዘገቡ አድባራትን ሸለመ።

ዛሬ በቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ በተደረገ የ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የአዲሱ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ በክፍላተ ከተማው ሥር የሚሚገኙ አድባራትና ገዳማት በተለይም ውጤታማ የሥራ ክንውን ላደረጉት የሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላና የደቡብ ሱዳን፣ የቤኒሻንጉል አሶሳ፣ቄለም ወለጋ ቤጊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጋምቤላ ሀገረስብከት መጃንግ ዞን መንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች ለሐዋርያዊ አገልግሎት በመጓዝ ሦስት አዳዲስ የተሰሩ አብያተክርስቲያናትን በመባረክ ቅዳሴ ቤታቸውን አክብረዋል።

በኒው ዮርክና አካባቢው የሚገኙ የአሀት ኦርቶዶክሳዊት (Oriental) ቤተክርስቲያን ብፁዓን አበው፣ ካህናትና ምእመናን በጋራ ለጸሎተ ቅዳሴ ተሰባሰቡ።

የአሀት ኦርቶዶክሳውያን አብያተክርስቲያናት ብፁዓን አባቶች ጉባኤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የጋራ የጸሎተ ቅዳሴ አገልግሎት መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም በዌስት ኦሬንጅ ኒውጀርሲ በሚገኘው ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከናውነዋል።

ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለማኅሌት አገልግሎት ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው የማኅሌተ ጽጌ መጽሐፍ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጎመ። ይህንን የአባ ጽጌ ድንግል ድርሰት የሆነው መጽሐፍ የተረጎሙት የፊንላንድ ሀገር ዜጋ የሆኑት እና ከሃምሳ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቆይታ ያደረጉት አቶ ኒሎ ሆንካነን ናቸው። ተርጓሚው መጽሐፉ ወደ ፊንላንድኛ ለመተርጎም ከ10 ዓመት በላይ ሲያጠኑ እንደቆዩና ዋና ምንጭ አድርገው የተጠቀሙት ደግሞ በ1919 ዓ.ም. በዶ/ር አዶልፍ ግሮህማን የተተረጎመውን የጀርመንኛ ቅጅ እንደሆነ ገልጸዋል።

የብፁዕ አቡነ ሰላማ ክቡር አስከረን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጓዘ።

በሀሌሉያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትላንትናው እለት ከዚህዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ክቡር አስከሬናቸው ወደበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸልተ ፍትሐት ሲደረግበት እንዲያድር እና በነገው እለት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አስፈላጊው ሥርዓት ከተፈጸመለት በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ እንዲፈጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጉዟል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ዕረፍትን በማስመልከት ያስተላለፉት አባታዊ የሐዘን መግለጫ

. . . ብፁዕነታቸው በዕረፍተ ሥጋ ከእኛ በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ቢሰማንም በሰማይ የሚጠብቃቸውን ክብር እያሰብን እንጽናናለን።

የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

ለውስጥ አገልግሎት

የኢሜይል አገልግሎት

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል