የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአሶሳ እንዚ መካነ ገነት መድኃኔአለም ካቴዴራል የህንፃ ግንባታ ኮሚቴ የመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት የማጠናቀቂያ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጠየቀ፤

November 18, 2023

ሀ/ስብከቱ የአሠሪ ኮሚቴውና የካቴዴራሉ ሰበካ ጉባኤ ያቀረበውን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ከመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን የመሩት የሀገረስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ዘካርያስ ፀጋ እንደገለጹት የህንፃ ግንባታውን ምርቃት በተመለከተ የካቴዴራሉ ሰበካ ጉባኤ እና የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ኃላፊነት ወስደው ዐብይ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ እንደሚገባ ገልጸው የመንበረ ጵጵስ ገዳማትና አድባራትን በመያዝ ካህናትን ሰብስቦ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸው ግንዛቤ

የተፈጠረላቸውን ካህናት በማሠማራት የማጠናቀቂያ የገቢ ማሰባሰብ ሥራ በመሥራት እስከ መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ/ም ሥራው ተጠናቆ በዘመነ ትንሣኤ ለማስመረቅ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀገረስብከቱ ዋና ፀሐፊ ሊቀልሳናት ትህትና አበበ በበኩላቸው የመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት አጥቢያ አቢያተክርስቲያናት የሰበካ ጉባኤ ካህናትና ምዕመናን በህንፃ ግንባታው ማስፈጸሚያ የገቢ አሰባሰብ ንቅናቄ ሥራ ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረው ይህም የቤተክርስቲያን አንድነት መገለጫ ነው ብለዋል። ምንግዜም ቢሆን የቤተክርስቲያን አንድነት በሥራ መገለጽ እንዳለበት በሰፊው ያብራሩት ዋና ፀሐፊው በየደረጃው ያለን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ፍቅርን እና አንድነትን በመያዝ የትብብርን መንፈስ ማዳበር አለብን ብለዋል።

የአሶሳ እንዚ መካነ ገነት መድኃኔአለም ካቴዴራል ዋና አስተዳዳሪ ሊቀ-አዕላፍ አባ ገ/መስቀል ምንዳ እንደተናገሩት አሁን ሥራውን አጠናቆ ለማስመረቅ አራት ሚልዮን ብር እንደ ሚያስፈልግ ገልጸው ብሩን ለማሰባሰብ የመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት የሚችሉትን ተከፋፍለው ቃል እንዲገቡ ካህናት ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ለማስቻል በሀ/ስብከቱ በኩል ጥሪ ተደርጎ ምክክር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስታውሰዋል።

የህንፃ ግንባታ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ ይሁን ጉዴታ እንደገለጹት ምዕመናን በዓይነት ድጋፍ እንዲያደርጉ በመድኃኔዓለም ስም ጠይቀው የሙሌት ሥራ ለመሥራት አሥር ቢያጆ ሀርድ ኮር ድንጋይ”፤ አምስት ቢያጆ አሸዋ፤ ሁለት መቶ ሃምሳ ኩንታል ስሚንቶ፤ የኳርቲዝ ቀለም በዋናነት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት አጥቢያ አቢያተክርስቲያናት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላትም የሚችሉትን ሁሉ ዴጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በቅርቡም የገቢ ማሰባሰብ ንቅናቄውን ለመጀመር ከካህናትና ከዲያቆናት ጋር ምክክር እንደሚደረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

ዘገባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
ኅዳር 08 ቀን 2016 ዓ/ም
አሶሳ፤

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-11-18 16:26:582023-11-18 16:26:58የአሶሳ እንዚ መካነ ገነት መድኃኔአለም ካቴዴራል የህንፃ ግንባታ ኮሚቴ የመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት የማጠናቀቂያ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጠየቀ፤
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ። Link to: ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ። ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት... Link to: የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት 42ኛው ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በይፋ ተጀመረ። Link to: የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት 42ኛው ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በይፋ ተጀመረ። የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት 42ኛው ጠቅላላ ሰበካ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top