የቦታው ስም ቀራንዮ ነው
የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ላለፉት ፯ ዓመታት ግንባታቸው የተጓተቱ ሁለት ህንጻዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የሚያደርግ የውል ስምምነት ተፈረመ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ሥራውን ቀግንባር ቀደምነት የሚያስተባብሩና የሚመሩት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊዕ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የበጀትና ሒሳብ መምሪያ ዋና ኃላፊ ወ/ሮ ጽጌሬዳ ዓለሙ ተገኝተዋል።
“እኛ ካህናት አስታራቂዎች እንጂ ታራቂዎች መሆን አልነበረብንም፤ በጥሪአችን መሰረት የእውነት ካህናት በመሆን ለቤተክርስቲያን አንድነት መስራት ይኖርብናል፤”
በቅርቡ በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ነገ ላይ ሆነን ስናየው መጸጸታችን አይቀርም፤የዛሬ አመጣጣችሁ የመጨረሻ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።
አዲስ መረጃ
ከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር አስገብተዋል።
አዲስ መረጃ
የቀድሞው ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ በትላንትናው ዕለት ቤተክርስቲያን ያደረገችውን ጥሪ በመቀበል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተደረሰውን ስምምነት በመቀበል በዛሬው ዕለት ወደ እናት ቤተክርስቲያናቸው መመለሳቸውን የሚገልዕ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በማቅረብ በይፋ ተመልሰዋል።
“የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን” ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው ጥያቄ ነው”።
“የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን” ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው ጥያቄ ነው”። የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በዛሬ ዕለት የተካሔደውን በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በሕገ ወጥ መንገድ በተሾሙ የቀድሞ አባቶች መካከል የነበረውን ውይይት አስመልክተው መግለጫው የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ሲሆኑ ቅዱስ […]
ከትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠውን መግለጫ በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
. . . በመጨረሻም መላው በትግራይ ክልል የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲወገድና አንድነቷ ጸንቶ እንዲኖር በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ ስታግዙ እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም በክልሉ የተከሰተውን ቀኖናዊ ጥሰትና ሕገወጥ አደረጃጀት ቆሞ እናት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ጸንታ እንድትኖር እንደአሁን ቀደሙ በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን የኢፌዴሪ መንግስትም እንደአሁን ቀደሙ በሲኖዶሳዊ አንድነት ላይና በቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ የተጋረጠው ችግር ልዩ ትኩረት በመስተጠና የበኩሉን ሚና በመጫወት የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድንትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀት ጸንቶ እንዲኖር አገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በውጭ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያናትና የአገልጋዮችን ዝርዝር በአፋጣኝ እንዲልኩ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ሰጡ።
መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የቤተክርስቲያናችንን የመረጃ ሥርዓት ለማዘመን የሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ ፣መተንተኛና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ሥርዓትን በመፍጠር ወጥነት ያለው የመረጃ ፍሰት ለመዘረጋት በጥናት ላይ የተመሰረተ የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ሰበር ዜና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር አረፉ
ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ የሆኑት በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ ዶ/ር በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በባህርዳር ሀገረ ስብከት የሚከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፣ወደፊት በሚሰሩ የልማት ሥራዎች ዙሪያም የሥራ መመሪያ ሰጡ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚያዝ ፰ -፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ያስጀነመሯቸውን ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናትና ልዩልዩፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል ። በፕሮጀክቶቹ ዙሪናም ድጋፍና ክትትልም አድርገዋል፣ ከገዳማትና አድባራት አስተዳደር ክፍሎች ጋርም ውይይት አካሂደው የሥራ መመሪያና ወደፊት መአናወን በሚገባቸው ሥራዎች ዙሪያም አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መጋቢት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ ም በጀርመን ሙንስትር ከተማ በመገኘት ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሙንስተርና አካባቢ ጳጳስ ከኾኑት ዶክተር ፊልክስ ጌን ጋር ውይይት ውይይት ማድረጋቸውን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ገልጿል።