የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን በተመለከተ በትግራይ ተፈናቃዮች የተደረገው መሰረተ ቢስ ውንጀላ ፍፁም ከእውነት የራቀ ነው።

July 11, 2023

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ አሥመራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር የተገናኙት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኤርትራና በኢትዩጵያ ስምምነት በተደሰተበት ማግስት የተፈጠረውን ሰላምና ዕርቅ እውቅና ለመስጠት በተደረገ ሥነሥርዓት ላይ ለመገኘት የአማራ ክልል ልዑክ በመሆን መጓዛቸው በቀጥታም ህነ በተዘዋዋሪ ከትግራይ ጦርነት ጋር ግንኙነት የለውም።

ብፁዕነታቸው ወደ አሥመራ በተጓዙበት ወቅት በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የትግራይ ክልል የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በሐዋሳ በተደረገ ስብሰባ ላይ ዶ/ር አቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስቴር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲፈጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያደረጉትን ጥረት በማሞገስ እውቅና በሰጡ ማግስት ብፁዕነታቸው አሥመራ መገኘታቸው በምን መመዘኛ ወንጀል ሊሆን ቻለ?የአክሱም ሐውልትን በስጦታ ማበርከትስ ከኢትዮጵያዊነት መገለጫዎቻችን ቅርሶች አንዱን ከማበርከት የዘለለ ሌላ ትርጉም እንደምን ሊሰጠው ይችላል?

ይልቅኑ ከጦርነቱ አስቀድሞ ችግር እንዳይፈጠርና ጦርነት እንዳይቀሰቀስ በብፁዕነታቸው አሳሳቢነት በአማራና በትግራይ ክልላዊ መንግስታት በኩል የሰላምና የአንድነት ውይይት እንዲካሔድ የተደረገው ጥረትና በትግራይና በፌደራል መንግስት መካከል ጦርነት አንዳይቀሰቀስ ለማድረግ ብፁዕነታቸው ያቀረቡት ሀሳብ በራሳቸው በትግራይ ክልል አባቶች እምቢተኝነትና ፌዝ የተሞላበት ትችት ሳይሳካ መቅረቱን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚያውቁት ሀቅ ነው።

ብፁዕነታቸው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሥራአስኪያጅ ከመሆናቸው በፊት ጦርነቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ የትግራይ ሊቃውንትና ተወላጆች የደረሰባቸውን የሥራ መፈናቀል በተመለከተ የቋሚ ሲኖዶስ አባል በነበሩበት ጊዜ ሊቃውንቱና የትግራይ ተወላጆች ወደ ሥራና ደመወዛቸው እንዲመለሱ ከፍተኛውን ዋጋ የከፈሉና ውሳኔው እንዲወሰን ያደረጉት ታሪካዊ ተጋድሎ ለምን ተረሳ?ከዚሁ ጋር ተያይዞ በወቅታዊ ሁኔታ የሚታሰሩ የትግራይ ተወላጆችን በመከላከል፣የታሰሩትን በመጠየቅና በማስፈታት ለፈጸሙት ተጋድሎስ እውቅና መንፈግስ ምን ይሉታል?

ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑ በኋላም በቋሚ ሲኖዶስ ደረጃ አስቀድመው የወሰኗቸው ውሳኔዎች በተሟላ ደረጃ እንዲፈጸሙ ለማድረግ ካደረጉት ጥረት በተጨማሪ በችግሩ ምክንያት ያለደመወዝና ያለሥራ የተቀመጡ የክልሉ ተወላጆችና ሊቃውንት በአሰሰቸኳይ ሥራ እንዲሰጣቸውና ደመወዛቸው ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ እንዲከፈላቸው በማድረግ እያደረጉት ያለው ተጋድሎ በትግራይ በኩል ጆሮ ዳባ ልበስ ቢባልም በአዲስ አበባ የሚገኙ የክልሉ ተዘላጆች የሚመሰክሩት ሀቅ ነው።

አሁንም በትግራይ አባቶችና በኢትዮጵያ እርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መካከል ያለው ችግር ቀኖና ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ፣ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ እንዲጠይቅና የስምምነት አመቻች ኮሚቴውም ሥራው የተሳካና ውጤታማ በሆነ መልኩ ማከናወን እንዲችል በማድረጉ ረገድ በሚገባ ኃላፈነታቸውን ፍጹም ተቋማዊ በሆነ መልኩ በመወጣት ላይ ያሉ ጠንካራ አባት ናቸው።

ይህን ሁሉ ተቋማዊ ተጋድሎ በቅንነትና በኃላፊነት መንፈስ የሚፈጽሙ አባትን ባልተገባ መንገድ መውቀስና መወንጀል ታዲያ ምን ይሉታል?ዛሬ በትግራይ የተደረገውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጉዞን ተከትሎ ተፈናቃይ ወገኖችን በመወከል በተላለፈው መልዕክት ላይ የተገለጸውም በምንም መመዘኛ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን የማይወክል፣ስብዕናቸውን የማይገልጽና የማይመለከታቸው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-07-11 05:05:232023-07-11 05:05:23ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን በተመለከተ በትግራይ ተፈናቃዮች የተደረገው መሰረተ ቢስ ውንጀላ ፍፁም ከእውነት የራቀ ነው።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ቅዱስነታቸው በትግራይ የሚገኙ አባቶች ችግሩን በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ Link to: ቅዱስነታቸው በትግራይ የሚገኙ አባቶች ችግሩን በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ ቅዱስነታቸው በትግራይ የሚገኙ አባቶች ችግሩን... Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ተጠራ Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ተጠራ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ተጠራ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top