ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የምክክር ጉባኤ በጠቅላይ ቤተክህነት በመካሔድ ላይ ነው።
መጋቢት ፲ቀን፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ እንድትሆንና በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ተገቢው ክብርና እውቅና እንዲሰጣት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ጥረት እንዲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አሳሰበ።
መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም.
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው መግለጫ ሰጡ፣
ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፤ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡ ስንጾም መገዳደልን፣ መጣላትን፣ መለያየትን፣ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አለብን፤ ከክፉ ኅሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በምግባረ ሰናይ ሆስፒታል የሚከናወኑ የማስፋፊያ ሥራዎችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እንደገለጹት የሆስፒታሉን አገልግሎት ለማዘመንና ለማስፋፋት እየተከናወነ ያለው ሥራ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን ገልጸው የግንባታ ሥራው በታቀደለት ጊዜ ተከናውኖ ወደ ሥራ መግባት እንዲችል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በባህርዳር ሀገረ ስብከት ለአንድ ሺህ አምስት መቶ አገልጋዮች ክህነት ሰጡ።
የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በህንድ ማላንካራ ሲሪያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተከበረውን የቅዱስ ቶማስ 1950ኛ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓል በማስመልከት ቃለ በረከት አስተላለፉ፡፡
ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት በህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ድምቀት የተከበረውን የሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓል በማስመለከት በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ከብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማር ቶማ ማቴዎስ ሦስተኛ የህንድ ማላንካራ ሲሪያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የክብር ጥሪ ተደርጎላቸው የነበረ ቢሆንም ቅዱስነታቸው በአካል ለመገኘት አስቀድሞ በተያዘ መርሐ ግብር ምክንያት ስላልቻሉ በቋሚ ሲኖዶስ በተወከሉ ልዑካን አማካኝነት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ/ም የሚጀመረውን ጾመ ነነዌ በማስመልከት አባታዊ ቃለ በረከት አስተላለፉ፡፡
በመረሻም ታላቅ ሀገር ይዘን፣ ምድሩ ሳይጠበን አመል እያጋፋን ነውና ጾማችን፣ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ለሀገር ደኅንነት፣ ለሕዝብ ድኅነት እንዲያመጣልን እግዚአብሔር ይቅር ብሎን ዘመኑን በምሕረት ያሻግረን ዘንድ በታላቅ ንስሐ፣ በጸሎትና በአስተብቍዖት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ አባታዊ መልእክታችንን በመሐሪው አምላክ ስም እናስተላልፋለን።
በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
የካቲት ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተመራ ውይይት ተካሄደ፡፡
የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
በ81 ዓመታቸው በድንገተኛ የመኪና አደጋ ያረፉት የሊቁ የመምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው የበዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ።
የካቲት ፲፪ ቀን ፲ወ፮ ዓ.ም