የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“የአብነት ትምህርት ቤት ለቤተክርስቲያን መሠረት ነው” በሚል መሪ ቃል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የአብነት መምህራን ያዘጋጀው የምክክርና ሥልጠና ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

May 24, 2024

ዘጋቢ መ/ር ጌታቸው በቀለ
(© EOTC TV ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም አዲስ አበባ)

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ከግንቦት ፲፭-፲፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ለኹለት ቀናት ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በመክፈቻ መርኸ ግብር ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመላው ኢትዮጵያ የቤተክርስቲያን ጥሪ ተቀብለው በምክክር ጉባኤው ላይ ለተገኙት ሊቃውንት “እንኳን ደህና መጣችሁ” በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አክለውም “ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከጥንት ጀምሮ ጠብቀው ያቆዩት አባቶቻችን ሊቃውንት ቅዱስ ሲኖዶስ ባልተቋቋመበት ጊዜ ሁሉ፤ ቤተክርስቲያኗን የሚመሩ የሚጠብቁ ሊቃውንቱ ነበሩ፡፡ ለዚህች ቤተክርስቲያን ጥብቅናቸው የሚያስደስት ነበር” ብለዋል፡፡ ዛሬም “ቅድስት ቤተክርስቲያንን መጠበቅና ማስጠበቅ የእናንተ የሊቃውንቱ ድርሻ ነው” ያሉት ብፁዕነታቸው በጉባኤው ቆይታችሁ ምሁራኑም በሚያቀርቡት ጥናት መሠረት ተወያይታችሁ የምታቀርቡት ምክረ ሐሳብ ለቅዱስ ሲኖዶስ ግብአት እንደሚኾን እንጠብቃለን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መልአከ መዊዕ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ኃላፊ እንደተናገሩት “የአብነት ትምህርት ቤት ለቤተክርስቲያን መሠረት ነው በሚል ቃል ከመላው ኢትዮጵያ ከመጡ መምህራን ጋር ምክክር፣ ውይይት በማድረግ፤ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ክፍተት በመዳሰስ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን በተጠናና በተረዳ ነገር እንዲረዱ እናደርጋለን” ብለዋል፡፡ መልአከ መዊዕ አያይዘውም እነዚህ ሊቃውንት ቤተክርስቲያን ስላለችበት ሁኔታ በመንፈሳዊም ሆነ በማኅበራዊ ጉዳይ በመወያየት ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚደግፍ ምክር ሐሳብ ያቀርባሉ፡፡ በየዓመቱ ግንቦት ወር ላይ ከርክበ ካህናት በፊት፤ ሊቃውንቱ እየተሰበሰቡ እንዲመክሩ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ የመምሪያው ዋና ዓላማም ሊቃውንቱ ቤተክህነቱን እንዲያውቁት፤ ቤተክህነቱም ትውልድ እያፈሩ ያሉትን ሊቃውንቱን እንዲያውቃቸው፣ እንዲረዳቸው፣ እንዲደርስላቸው ማድረግ መኾኑን ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በኹተኛው የጉባኤው በማጠናቀቂያው ዕለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት “ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ትውልድ እያፈራችሁ፣ እያስተማራችሁ የቤተክርስቲያን ትምህርት ከትውልድ ወደ ትውልድ እያስተላለፋችሁ ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን ያላችሁ ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነትና ጥበቃ ቤተክርስቲያን ምንጊዜም በእናንተ ነው የምትጠበቀው፡፡ ቤተክርስቲያን ቁማ ያለችው በሊቃውንቷ አስተማሪነት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ እየጠነከረ እንዲሄድ ጸሎታችን ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ጥሪ ተቀብላችሁ ጉባኤ ማካሄዳችሁ ታሪካዊ ጉባኤ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ጉባኤም መቀጠል አለበት” ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ጉባኤ ቤት ለአላቸው የአብነት መምህራን የምስክር ሰርተፊኬት ሰጥተው ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠና በመካሔድ ላይ ነው ። Link to: “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠና በመካሔድ ላይ ነው ። “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት... Link to: “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ። Link to: “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ። “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top