የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ።

May 25, 2024

ግንቦት ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ “ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች በሕዝብ ግንኙነት ምንነት፣ አሠራር፣ አደረጃጀትና በእርቶዶክሳዊ ማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ሥልጨና ተጠናቀቀ።

በዛሬው እለትም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለአሰልጣኞችና በስልጠናው ላይ ለተሳተፉ የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊዎች የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ከቅዱስነታቸው እጅ ተቀብለዋል።በዚሁ ጊዜም ቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ መልዕክት፣ ቃለ በረከትና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል።

በዚሁ ጊዜም የተዘጋጀው በለ ፲ ነጥብ የአቋም መግለጫ ተነቧል። የአቋም መንለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

‹‹አምላከ ሰማይ ይረድአነ ወንህነ አግብርቲሁ ንትነሣእ ወነሐንጽ ሎቱ፡፡››
‹‹የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፡፡››
ነህምያ 2፡20

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኃላፊ፤ ክቡራን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያና ድርጅቶች ኃላፊዎች፤ ክቡራን ሠልጣኞች፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔር ረድቶን የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እና የብፁዓን አባቶቻችን ጸሎት አግዞን ይህንን የቤተ ክርስቲያናችንን የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ከፍ ወዳለ ደረጃ ማድረስ የምንችልበትን የሥልጠና፣ የውይይትና የምክክር መርሐ-ግብራችንን አጠናቀን በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ለመባረክ በመብቃታችን ታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት የተሰማን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ በአግባቡ በመረዳትና ያሉባትን ፈተናዎች በጠንካራ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመወጣት በማሰብ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለእኛ በየአህጉረ ስብከቱ ላለን የሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊዎች ካዘጋጀውና ከ ግንቦት 15 – 17 ቀናት 2016 ዓ/ም ከተሰጠው የሥልጠና፣ የውይይትና የምክክር መርሐ-ግብር ዘርፈ ብዙ እውቀትን ገብይተናል፡፡

በሥልጠና መርሐ-ግብሩ ያገኘነውን ዕውቀት፣ ግንዛቤና ምክረ-ሐሳብ መነሻ በማድረግም እግዚአብሔር አምላካችን እንደሚረዳን በማመንና የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እና የብፁዓን አባቶቻችንን ጸሎት ተስፋ በማድረግ በሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ቤተ ክርስቲያን የምትፈልግብንንና ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊ ሥራ ለመሥራት መዘጋጀታችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ለሦስት ቀናት በቆየው የሥልጠና መርሐ-ግብር፡-
1.ኛ ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገራችን ያበረከተቻቸውን ወደር የለሽ አስተዋጽኦዎች ተረድተናል፡፡
2.ኛ ስለ ሕዝብ ግንኙነት ምንነት፣ ተልእኮ፣ የአፈጻጸም ስልትና የውጤታማነት ግምገማ ተምረናል።
3.ኛ ስለ ሕዝብ ግንኙነት ሙያዊ ስነ ምግባር እና የሕግ ተጠያቂነት ከፍተኛ ግንዛቤ አግኝተናል።
4.ኛ የቤተ ክርስቲያናችንን ልማትና ተግዳሮት በንቃት በመከታተል፤ የሚነሡትን አሉታዊ አመለካከቶች ወይም የተሳሳቱ ግንዛቤዎች በማጥራት በምእመናን እና በማኅበረሰቡ መካከል መተማመንና መከባበር እንዲኖር በትጋት መሥራት እንዳለብን ተረድተናል።
5.ኛ ከጠባቂነት በመውጣት በቆራጥነት፤ በበቂ ክህሎት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወደ ፊት ለማሻገር ጠንክረን መሥራት እንዳለብን ተገንዝበናል፡፡
ከእነዚህ ግንዛቤዎች በመነሣትም ቤተ ክርስቲያናችን በሕዝብ ግንኙነት መስክ ውጤታማ ትሆን ዘንድ የሚከተሉትን ጠቃሚ ተግባራት ለመፈጸም እኛ በሥልጠናው የተሳተፍን የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊዎች እግዚአብሔር አምላካችንን አጋዥ አድርገን በብፁዕ ወቅዱስ አባታችንና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፊት ቃል እንገባለን፡፡
6.ኛ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉን ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በእቅድ በመምራት፣ ፈንድ በማፈላለግ፣ የሚዲያ ሠራዊትን በስልጠና በማጠናከርና የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ ቃል እንገባለን፡፡
7.ኛ በአህጉረ ስብከት የሚከሰቱ ማናቸውንም አወንታዊ ዜናዎችና አሉታዊ ተግዳሮቶች ሳምንታዊ በሆነ መርሐ-ግብር ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በተከፈተልን የግንኙነት መስመር ለማስተላለፍ ቃል እንገባለን፡፡
8.ኛ የቤተ ክርስቲያናችንን ነባራዊ ሁኔታ በንቃት በመከታተልና ትክክለኛ መረጃዎችን በመስጠት፤ አሉታዊ አመለካከቶችን እና የተሳሳቱ ግንዛቤዎች የማጥራት ሥራን በትጋት ለመሥራት ቃል እንገባለን።
9.ኛ ቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ እሴቶቿን እንደ ጠበቀች፤ ከወቅታዊ ጉዳዮችና የመገናኛ መንገዶች ጋር በመላመድ በምታደርገው ጉዞ የሚገጥሟትን እንቅፋቶች በድል መሻገር እንድትችል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ቃል እንገባለን፡፡
10.ኛ ማኅበራዊ ሚዲያ የሌለን አህጉረ ስብከት የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ከፍተን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓቷን፣ ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን፣ ክብረ በዓላቶቿን፣ የአደባባይ በዓላቶቿን፣ የሀገረ ስብከታችንን የልማት፣ የስብከተ ወንጌልና አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ለምእመናንና ለቤተክርስቲያናችን ወዳጆች ተደራሽ ለማድረግ ቃል እንገባለን፡፡
ለዚህም የቅዱስ አባታችንና የብፁዓን አባቶቻችን ጸሎት ትርዳን፡፡

ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ/ም.
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “የአብነት ትምህርት ቤት ለቤተክርስቲያን መሠረት ነው” በሚል መሪ ቃል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የአብነት መምህራን ያዘጋጀው የምክክርና ሥልጠና ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ Link to: “የአብነት ትምህርት ቤት ለቤተክርስቲያን መሠረት ነው” በሚል መሪ ቃል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የአብነት መምህራን ያዘጋጀው የምክክርና ሥልጠና ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ “የአብነት ትምህርት ቤት ለቤተክርስቲያን መሠረት... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top