ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የዮርዳኖስ መንግሥት የቱሪዝም እና ጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስትር ክቡር ማክራም ሙስጣፋ አብዱልከሪምን በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተቀብለው አነጋግረዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት ፲፫/፳፻፲፮ ዓ/ም የዮርዳኖስ መንግሥት የቱሪዝምና የጥንታውያት ቅርሶች ሚንስትር ክቡር ማክራም ሙስጠፋ አብዱልከሪምን በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው “መነኩሴ “ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን ሀገረ ስብከቱ ገለጸ።
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን “መነኩሴ”በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ “መነኩሴ” መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።
ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም:- የካቲት 12 ቀን በታጣቂ ቡድኖች ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።
በኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምርህታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ደቀመዛሙርት ማዕርገ ዲቁና ተቀበሉ።
በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ መልካም ፈቃድ አሳሳቢነት የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩት አራት ደቀ መዛሙርት የዲቁና ሥልጣነ ክህነት በሰጡበት ወቅት ለአገልጋዮቹ በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ትምህርት አስተምረው በዓለም ዙሪያ ያለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቅንነትና በእውቀት እንዲያገለግሏትም አባታዊ መመሪያም አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የካቲት 11/06/2016 ዓ/ም ለሰባት ማኅበራት የዕውቅና ሰርተ ፍኬት ሰጠ።
የተሰጣቸው ሰርተፍኬት ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ይቆያል ተብሏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የካቲት ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሥራ ጉብኝት አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር እና ደቀመዛሙርትን በመጎብኘት አባታዊ ቡራኬ እና የሥራ መመሪያን አስተላልፈዋል፡፡
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
የካቲት ፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በትላንትናው እለት የብፁዕ አቡነ ፋኖኤል የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወላጅ እናት የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተከኝተው አሸኛኘት አደረጉላቸው።
የካቲት ፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዓመታዊ የሥልጠናና የውይይት መርሐ ግብሩን ጀመረ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በየዓመቱ የሚያካሂደውንና ወዘቅታዊና ዘላቂ የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ላይ በየዓመቱ የሚያደርገውን የሁለት ቀናት የሥልጠናና የውይይት መርሐ ግብር ዛሬ ጥር ፴ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም ጀመረ።