የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“የማይኾን ጸጸት እንዳንጸጸት በሰዓቱ እና በጊዜው ንስሐ እንግባ” ብጹዕ አቡነ አብርሃም ፤

May 4, 2024

ባሕር ዳር-ኢትዮጵያ

ሚያዚያ ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም ሀገረ ሰብክት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ አብርሃም የስቅለት በዓልን ምክንያት በማድረግ ትምህርት እና አባታዊ ምክር ሰጥተዋል፡፡

ብጹእነታቸው እግዚአብሔር የተናቁትን ከፍ ያደርጋል፤ የተረሱትን ያስታውሳል ብለዋል፡፡ በሰው ዘንድ ነውረኛ የተባሉትን ከነውር አንጽቶ እና ቀድሶ ልጁ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡ ጌታውን የሸጠው ይሁዳ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለታላቅ ነገር መርጦት ሳለ ጌታውን አሳልፎ ሰጥቷል ያሉት ብጽዑነታቸው ንስሐ፣ መጸጸት፣ በድያለሁ፣ አጥፍቻለሁ ብሎ በሰዓቱ እና በጊዜው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ንስሐ ሰዓቱ ካለፈ፣ ጊዜው ከባከነ፣ በሩ ከተዘጋ ለምንም አይጠቅምም ነው ያሉት፡፡ የይሁዳ ጸጸት ከተዘጋና ሁሉንም ነገር ካከተመ በኋላ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ የማይኾን ጸጸት እንዳንጸጸት በሰዓቱ እና በጊዜው ንስሃ እንግባ ነው ያሉት፡፡ ይሁዳ ልቡ የነበረው ከገንዘብ ጋር ነበርና ሲያንገላቱት፣ ሲያዳፉት፣ መከራዎች ሲበዙበት ተጸጸተ፤ ጌታውን ያሸጠውን ገንዘቡንም በተነ፤ የዓለም ነገር ሁሉ ከንቱ እንደኾነ ተመለከተ፤ ጸጸቱ ግን የማይጠቅም፣ ንስሃውም ውኃ የማያነሳ ነበር ይላሉ፡፡

ከፍ ከፍ ያደረገውን አሳልፎ ሰጠው፣ ስጋዊ ምኞቱ ለክብር ሳያበቃው ቀረ፣ ንጹሕ ደም ያስፈሰስኩ፣ ጻድቅ ሰው ያስገደልኩ ነኝ አለ፣ ጸጸቱ ግን ጊዜ ካለፈ በኋላ ነበር፡፡ ራሳቸውን የማያድኑ፣ ለራሳቸው ማየት የተሳናቸው፣ የሚናገሩትን የማይሠሩ፣ የማያደርጉ ብዙዎችን በማያውቁት አሳሳቷቸው፤ እናም በጌታቸው ላይ፤ በመድኃኒታቸው ላይ ሆ! ብለው ተነሱ፡፡ ንጹህ የኾነውን ገደሉ፡፡ ዛሬም እንደዚያ ዘመን ኾነናል፤ ሆ! ብሎ የሚነሳው በዝቷል፤ ሕዝብን የሚያደናግረው ብዙ ነው ብለዋል፡፡

ብጽዕነታቸው በይሁዳ አሳልፎ ሰጭነት፣ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ጩኸት እና በሕዝቡ ተባባሪነት የማይገረፍ ተገረፈ፣ የማይንገላታ ተንገላታ፣ የማይሰቃይ ተሰቃየ፣ የማይሞትም እነኾ ሞተ፣ እርሱ ግን በሞቱ ሞትን ያጠፋ ዘንድ ነው፡፡ የሌላው ሞት ግን ትርጉም የለውም፤ ተናበን በሃይማኖት ጸንተን እምንናገረውን አውቀን እንድንኖር ከይሁዳ እንማራለን ነው ያሉት፡፡

ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ መኾን ግን ሐጥያት ነው ብለዋል፡፡ እህትና ወንድም፣ እናትና አባትን አጎሳቁሎ ገንዘብ መውሰድ ለምንም አይጠቅም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያጣላል ነው ያሉት፡፡

ትናንት በክርስቶስ ላይ በሀሰት እንደመሰከሩበት ሁሉ ዛሬም ክርስቶስን በሚመስሉ ላይ በሃሰት የሚመሰክሩ፣ አሳልፈው የሚሰጡ ሞልተዋል፡፡ በሃሰት ወንጀል መፈጸም፣ በሃሰት መመስከር ክርስቶስን ከሸጠው ይሁዳ ጋር አለመለየት ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ ለእኛ ድኅነት ነው፣ ለእኛ ክብር ነው፣ ለእኛ ልጅነት ነው፣ ለኛ ነጻነት ነው፣ አባቶቻችን የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቋት ኖረዋል፤ በዚህች እለት የሚጠቅም ጸጸት የተጸጹት ድነዋል፤ የሚገባ ጸጸት የተጸጸተ ገነት ገብቷል፤ የመንግሥቱ ወራሽ እንዲኾን የሚገባውን ጸጸት እንጸጸት፣ በሰዓቱ ንስሃ እንግባ ነው ያሉት፡፡

በሰዓቱ ንስሃ ከገባን እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎበኘናል፤ ሰላሙንም ያበዛልናል፤ ሰላም ትልቅ ዋጋ አለው፤ ንስሃ ለመግባት ሰላማዊ መኾን ያስፈልጋል፤ ንስሃ ለመግባት የፍቅር ሰው መኾን ያስፈልጋል፤ ንስሃ ለመግባት ከክፉ ነገር መራቅ ያስፈልጋል፤ ንስሃ ለመግባት ንጹሕ ልብ ያስፈልጋል፤ ቂም በቀል የቋጠረ ልብ ይዞ ንስሃ መግባት አይቻልም፤ ከእግዚአብሔርም ጋር መገናኘት አይቻልም ብለዋል፡፡ እውነት ስንናገር፣ በእውነት ስንኖር፣ ለወገን ስንራራ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይኾናል፤ ሰላሙንም ያበዛልናል ይላሉ፡፡

በዓሉን ስናከብር ከማንኛውም ወገን ጋር በመጠያየቅ፣ በመከባበር፣ በመንከባከብ ይሁን፣ የጋራ ሀገር አለን፣ የጋራ ሀገራችን ላይ የጋራ የኾነ ሕዝብ ኾነን በሰላም ከየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ጋር አብሮ መኖርን ገንዘብ እናደርግ ብለዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ ሰይጣን በእምነትም ሊያዋጋን ይፈልጋል፤ ግራ ሊያጋባን ይፈልጋል፤ በእምነትም ጥላቻ ፈጥሮ እርስ በእርስ እንድንጠፋፋም ለማድረግ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡ በፍቅር፣ በሰላም ስንኖር የጋራ ኖሮ እንኖራለን፣ የጋራ ሀገራችንን ከፍ ከፍ ማድረግ እንችላለን ነው ያሉት ብጹዕነታቸው፡፡

©አሚኮ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/abune-abrham300.jpg 300 300 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-05-04 08:58:432024-05-04 08:58:43“የማይኾን ጸጸት እንዳንጸጸት በሰዓቱ እና በጊዜው ንስሐ እንግባ” ብጹዕ አቡነ አብርሃም ፤
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የ”ገብረ ሰላመ” በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ። Link to: የ”ገብረ ሰላመ” በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ። የ”ገብረ ሰላመ” በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ... Link to: ቅዱስ ፓትርያርኩ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮንመድኀኔዓለም ካቴድራል የተመሰረተበትን ፳፭ኛ ዓመት በዓል አከበሩ። Link to: ቅዱስ ፓትርያርኩ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮንመድኀኔዓለም ካቴድራል የተመሰረተበትን ፳፭ኛ ዓመት በዓል አከበሩ። ቅዱስ ፓትርያርኩ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top