የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት፣ ቃለ በረከትና ቡራኬ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል። መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

August 6, 2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ!

በማሕፀነ ማርያም በፈጸመው እውነተኛ ተዋሕዶ የሰው ልጅን ከኃሣር ወደ ክብር የመለሰ እግዚአብሔር አምላካችን፣ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት ጾመ ቅድስት ማርያም በደኅና አደረሰን አደረሳችሁ!፤

‹‹ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ጸጋ፣ ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፡- ምልእተ ጸጋ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በእግዚአብሔ ዘንድ ሞገስን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ›› (ሉቃ. 1÷28-30″)
የክብር አምላክ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ከወደቀበት ዐዘቅተ ኵነኔ የሚያድንበት ዕድል እንዳዘጋጀ በብሉይ ኪዳን በስፋት ገልፆል፤ የማዳን ስራውም ከሰው ወገን ከሆነች ቅድስት ድንግል በሚወለደው መሲሕ እንደሚፈጸም አስረድቶአል፤ የማዳን ቀኑ በደረሰ ጊዜም መልእክቱን በፊቱ በሚቆመው በቅዱስ ገብርኤል በኩል ልኮአል፤ ቅዱስ ገብርኤልም የተነገረውን መልእክት ለድንግል ማርያም አድርሶአል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ለድንግል ማርያም እንዲነግር ከታዘዘባቸው መካከል ‹‹ጸጋን የተመላሽ ደስተኛይቱ ሆይ÷በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ›› የሚል አስደናቂ መልእክት ይገኝበታል፡፡

የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን!

ከእግዚአብሔር መንጭቶ በቅዱስ ገብርኤል በኩል ለድንግል ማርያም የተነገረ ይህ መልእክት፣ የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከመግለጽ ባሻገር ለሰው ልጆች ሁሉ ያለው ፋይዳ በእጅጉ የላቀ ነው፤

‹‹ጸጋ›› የሚለው ቃል እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ ያልተወሰነ፣ ገደብና ቅድመ ሁኔታ የሌለው ስጦታን ሲያመለክት ‹‹ሞገስ›› የሚለው ቃል ደግሞ ተወዳጅነትን ተደማጭነትን ተሰሚነትን የሚያመለክት የክብርና የባለሟልነት መግለጫ ቃል ነው፡፡

እነዚህ ቃላት ከእግዚአብሔር ዘንድ በቅዱስ ገብርኤል በኩል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተነግረዋል፤ የእግዚአብሔር ቃል የማይለወጥ ነውና ቃላቶቹ ለድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ሆነው የተሰጡ ናቸው፤ የተሰጡበትም ምክንያት ሰውን ለማዳን ስራ እንዲውሉ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡

ምክንያቱም የእግዚአብሔር የማይናወጥ ፈቃድ ሰውን ማዳን ነውና፤ በመሆኑም ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት በዚህ ገደብ የሌለው ቃል ኪዳኗ ሰውን ልትታደግ በቅታለች፤ይህም በቃና ዘገሊላ ባደረገችው ምልጃ በጭንቀት የተዋጡትን ሠርገኞች እንዴት እንደታደገች በቅዱስ ወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፤ቅድስት ድንግል ማርያም ቀድሞውኑም ከፍ ያለ ሞገስ ተሰጥቶአታልና የሠርጉ አሳላፊዎችን ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› በማለት ስታዝዝ እናያለን፤ ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ አስደናቂ የትድግና ስጦታ ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

የድንግል ማርያም የጸጋ ስጦታ በብሥራተ ገብርኤል ተገልጾ፣ በቃና ዘገሊላ ተተግብሮ በዕለተ ስቅለት ‹‹እነሆ ልጅሽ፣ እነኋት እናትህ›› በሚል መለኮታዊ ማኅተም የታተመ ነው፤ ይህ ቃል እሷ እናታችን መሆኗን፤ እኛም ልጆችዋ መሆናችንን ያረጋገጠ ማኅተመ ቃል ኪዳን ነው፤ የቃል ኪዳኑ ይዘት እሷ በአማላጅነቷ እንደ ልጅ ልትንከባከበን እኛም እንደ እናት ልናከብራትና ልንማፀናት የሚገባን መሆኑን ያሳያል፤ የእናትነትና የልጅነት ማረጋገጫ የሆነ ይህንን የቃል ኪዳን ማኅተም ሊሰርዝም ሆነ ሊፍቅ ሊደመስስም የሚችል ኃይል የለም፡፡

ይህ ጸጋና ሞገስ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም የሚቀጥል እንጂ የሚገደብ አይደለም፤ ሞት፣ ቦታና ዘመንም አይወስኑትም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በሞት በቦታና በዘመን አይገደብምና ነው፤ ‹‹ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል›› ተብሎ የተገለጸውም ለዚህ ነው፤ (መዝ. )111÷5)
መንፈስ ቅዱስም በእሷ አንደበት ‹‹እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ ይሉኛል›› በማለት የተናገረው ይህንን ለማስረዳት እንደሆነ ማስተዋል ያሻል፡፡

በእግዚአብሔር ተሰጥቶ፣ በቃል ኪዳን ታትሞ፣ በቅዱስ ገብርኤል ተብራርቶ፣ በጌታችን ተረጋግጦና በሐዋርያት በኩል የተላለፈልን፣ ሰውን ማዳን ግቡ የሆነ የድንግል ማርያም ምልጃ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ በሁሉ ያለች፣ አንዲትና ቅድስት ኦርቶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ሺሕ ዓመታት ያህል አምና እና ተቀብላ ስትጠቀምበት ኖራለች፤ አሁንም በዚሁ ትቀጥላለች፡፡

በኦርቶዶክሱ ዓለም ዛሬ የሚጀመረው የጾመ ማርያም ሱባዔም የዚሁ ጭብጥ ማሳያ ነው፤ ዋናው መልእክቱም ድንግል ማርያም በተሰጣት ጸጋና ሞገስ በጸሎቷ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ይቅርታን የምታሰጠን ስለሆነች እሷን በመማፀን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ የሚል ሆኖ ይመሰጠራል፡፡

የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!

ጾም ፈቃደ ሥጋን በማድከምና ፈቃደ ነፍስን በማጎልበት ምሕረተ እግዚአብሔር መሻታችንን የምናሳይበት መንፈሳዊ ማመልከቻ ነው፤ ጾም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፤ ቀደምት አበው በጾም ምክንያት ከጥፋት ድነዋል፤ የለመኑትንም አግኝተዋል፤ ምስጢርም ተገልጾላቸዋል፤ ዲያብሎስም ድል አድርገውበታል፡፡

እኛም ዛሬ ጾምን ስንጾም በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ብሎም በዓለም ዙሪያ ሁሉ ስጋትን እየጫረ ያለው የጥፋት እንቅስቃሴ እግዚአብሔር እንዲያስቆምልን ከልብ በመጸለይ ሊሆን ይገባል፤ ይህንንም ስናደርግ በጸሎት ብቻ ሳይሆን ንስሐ በመግባትና ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል እንደዚሁም የሰላም የፍቅርና የዕርቅ ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም ሊሆን ይገባል፡፡

ችግሮችንና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በምክክር ለመፍታት የሚደረገው ጥረትም በእጅጉ ሊደገፍ ይገባል፤ ግጭትና ጦርነት ከሚያጠፋን በቀር ሊያተርፍልን የሚችል አንዳች ጥቅም የለም፡፡

በመሆኑም በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ ያላችሁ ልጆቻችን እባካችሁ ለሰላም ለውይይትና ለሰው ልጆች መብት መከበር ቅድሚያ ስጡ፤ ግድያ፣ ዕገታ፣ አብያተ ሃይማኖትን መዳፈር፣ ዘረፋና ቅሚያ፣ የሴት ልጅን መድፈርና ሰውን ማንገላታት አቁሙ፤
እነዚህ ድርጊቶች ሰብአዊነትን ዝቅ የሚያደርጉ፣ እግዚብሔርን የሚያስቆጡ፣ በታሪክም የሚያሳፍሩ ናቸው፤ እነዚህን ሳናርም የምንጾመው ጾም ትርጉም ስለሌለው ንስሐ ገብተን ከእንደዚህ ያለው ድርጊ ርቀን ጾሙን መጾም ይገባል፤ ይህን ስናደርግ ጾማችን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ይኖረዋል፡፡

በመጨረሻም
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በተለይም በጾመ ማርያም ሱባዔ በንስሐና በጸሎት የሚያሳልፉ ሕዝበ ክርስቲያን ስለ ሃይማኖት መጠበቅ፣ ስለሀገር ሰላምና አንድነት፣ እንደዚሁም ስለሕዝቦች ደኅንነትና ጤንነት አጥብቀው እንዲጸልዩ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
መልካም የሱባዔ ወቅት ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.
ዋሽንግተን ዲሲ – ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/photo_2024-08-06_11-18-58-cover.jpg 433 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-08-06 11:33:002024-08-06 11:33:00ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት፣ ቃለ በረከትና ቡራኬ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል። መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ11.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡ Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ11.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን... Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 12ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ዋለ። Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 12ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ዋለ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 12ኛ ዓመት የእረፍታቸው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top