ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

መጋቤ ምሥጢር ሲዘከሩ

የአንጋፋው ጋዜጠኛ መጋቤ ምሥጢር ወልደሩፋኤል ፈታሒ ሁለተኛ ዓመት የሙት ዓመት መታሰቢያ ዛሬ ጷጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ውሏል።

የኢሉ አባ ቦራ ሀገረ ስብከት ለቤተክርስቲያን መሪዎች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ!

ስልጠናው በሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግኑኝነት መምርያ ከመቱ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የስልጠናውን ሙሉ ወጭ የመቱ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን ሸፍኗል።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሰሜን አሜሪካ ሲያካሒዱ የቆዩትን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ጷጉሜን ፪ቀን፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም

ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል ከአህጉረ ስብከት የሚደርሱትን ወቅታዊ መረጃዎችና ዜናዎችን በማስተላለፍ የመረጃ ፍሰቱን የተቀላጠፈ ማድረግ ይቻል ዘንድ”ድምጸ ተዋሕዶ” የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ በመክፈት ወቅታዊ የአህጉረ ስብከት መረጃውችን ማሰራጨት ጀምሯል።

የቤተ ክርስቲያናችንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎትን ለማዘመን የሚያስችል የምክክር መድረክ በሰሜን አሜሪካ ተካሔደ።

ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
===================
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 12ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ዋለ።

ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት፣ ቃለ በረከትና ቡራኬ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል። መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ11.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡

ሐምሌ 243/2016 ዓ.ም

በዲላ ማረሚያ በቅዱስ ዮሐንስ ወሌደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን 47 ኢአማኒያን የሥላሴን ልጅነትን አገኙ።

ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (ዲላ)

በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ!

ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

ለውስጥ አገልግሎት

የኢሜይል አገልግሎት

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል