የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የጋምቤላ ክልል፤ የደቡብ ሱዳን፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ የምዕራብ ወለጋ፤ የምስራቅ ወለጋ ፤ የሆሮ ጉድሩ እና የቄለም ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ የሰላምና የልማት አምባሳደር፤ የሃይማኖት ተቋማት ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የ2017 ዓ/ም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤

January 7, 2025

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ አምላክ አሜን!

“የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ.9፥6)

ክቡራትና ክቡራን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ በ7ቱም አህጉረ ስብከት በየደረጃው የምታገለግሉ ካህናት መምህራን፤ የሰበካ ጉባኤ አባላት፤ የሰ/ት/ቤት መዘምራን፤ ወጣቶች የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት፤መላው ህዝበ ክርስቲያን በመጀመሪያ እንኳን ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር በሰላምና በጤና ጠብቆ ለ2017ኛው ዓመት ለጌታችንና የመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ አደረሰን!

የሰላም አለቃ ማለት ሰላም የባሕርይ ገንዘቡ የሆነች ከማንም የማይፈልጋት ከእርሱ የምትመነጭና ለሚፍልጓት ሰዎች ሁሉ የሚሰጣት ሰላም የባሕርዩ መገለጫ የሆነ ማለት ነው።

የሰላም አለቃ የሆነውን ጌታ ከመከተልና እርሱን ከማምለክ የራቀች አለቅነቱን ያልተቀበለች፣ ግዛቱ ዘላለማዊ መሆኑን የዘላለም ንጉሥነቱን አላውቅም እንቢ ያለችው ይህች ዓለም የሰላም አለቃ ሆኖ የተወለደውን ፤ የሰላም ንጉሥ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፋ ለሞት ስለሰጠች ሰላም እርቋት ከቆዬ ዘመናት ተቆጥረዋል።

ዓለም ስለሰላም አብዝታ ብትጮህም የሰላምን ምንጭ ስላደረቀችውና ሰላም ከማይገኝበት ቦታ ስለምትፈልግ አልተሳካላትም።

የሰው ልጅ ሰላም እርቆት፤ ጨለማ ውጦት በነበረበት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም አለቃ ሆኖ ተወለደ ፤ ነብዬ ልዑል ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት ሰባት መቶ ዓመታት በፊት እንዲህ ብሎ ተናገረ ” ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል”።(ኢሳ.9፥6)

ይህን የሰላም አለቃ፤ ዓለም ጠልታ፤ በሀሰት ክስ እና ምስክር ለሞት አሳልፋ ስለሰጠችው፤ አሁን የዓመፅ ዋጋዋን እያገኘች የክህደት ፍሬዋን እየለቀመች ፤ሰላም እርቋት ትገኛለች።

ለእኛ የሰላም ልጆች የዘላለም ንጉሥ የሕዝቡ ሁሉ መድኀኒት የሆነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ የሰላም አለቃ ሆኖ ከተወለደልን 2017 ዓመት ሆኖልናል።

የተወለደው ሕፃን መደኀኒት ነው። አባት ነው። መካር ነው። ኃይልና ብርታት ነው። አምላክ ነው፣ ነጉሥ ነው፣የሰው ብርሃን ነው፣የሰው ሕይወት ነው፣መልካም እረኛ ነው፣ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ ነው።

የተወለደው ለእኛ ነው። ተሰጥቶናል ተወልዶልናል የሚለው የቅዱሳን ነቢያት አነጋገር የሚያስረዳን ለእኛ እንጂ ለራሱ ወይም ለመላእክት እንዳልተወልደ ነው።

እግዚአብሔር የሰጠን ሰላም ልጁ ነው። እርሱን ቀዳሜ ጸጋ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለው ቅዱስ ባስልዮስ፤ የሰጦታ ሁሉ መጀመሪያና መጫረሻ፤ ወድ ስጦታ፤ ክቡር ስጦታ፤ታላቅ ስጦታ ብሎ ከመቀበል ውጭ ሌላ ሰላም ከሌላ ሥፍራ አናገኝም።

በእውነት የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁላችንም ሰላሙን ፍቅሩንና አንድነቱን ስምምነቱን ይስጠን። አሜን!

ክቡራትና ክቡራን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ!
“””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””
ሰብአ ሰገል የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በማለት በኮከቡ እየተመሩ መጥተው ሰግደውለታል።
(ማቴ.2፥1)

ለእግዚአብሔር መንበርከክ፤ ለእግዚአብሔር መገዛት፤ ለሀገር ሰላም ያመጣል፤ ለሀገር ፍቅርን፤አንድነትን፤ ስምምነትን ያመጣል ፣ ከእርሱ የተገኘውን ሥልጣን ገንዘብ ማድረጊያ መንገዱም ይሄው ነው።

ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ( ሮሜ . 13 ፥ 1) ይላልና የዛሬዎቹ ባለሥልጣናትም የሚያስተዳድሩት ሕዝብ  እንዲመራላቸው፤ እንዲታዘዛቸው፤ እንዲያከብራቸው፤ ሥልጣን ለሰጣቸው የባሕርይ ንጉሥ መገዛት ይገባቸዋል፤ ይህን ካደረጉ የተወለደው ህፃን  የዘላለም አምላክ፤ የሰላም አለቃ ነውና ሰላሙን ያሳድርባቸዋል።

እኛም የሰላም ልጆች በልደቱ እረኞችና መላእክት አንድ ሆነው ” ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ” ብለው እንደዘመሩ የሰላም መዝሙር እየዘመርን፤ የተቸገሩትን እየረዳን፤ የተራቡትን በማብላትና በማጠጣት እንድናከብር አደራ እላለሁ።
ልዑል እግዚአብሔር ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሰላም ይስጥልን!
መልካም በዓለ ልደት ይሁንልን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ Link to: መልእክተ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ መልእክተ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top