የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግድያ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አወገዘ።

December 5, 2023

ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
******
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ በዛሬው እለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በምሥራቅ አርሲ አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የሞት አደጋ በተመለከተ ኅዳር 24 ቀን 2016ዓ.ም ከሀገረ ስብከቱ በስልክና በደብዳቤ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ውይይት ካደረገ በኋላ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሀገረ ስብከቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት ባደረሰው መረጃ በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶሌ ሚካኤል፣በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በሪፖርቱ አሳውቋል።

በተጨማሪም በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው ተለቅመው የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው ነተገለጸ ሲሆን በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ተገሌጿል።

ከሁለት ቀናት በፊትም በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን ከመገደላቸው በተጨማሪ የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት መቃጠሉ ታውቋል።በተያያዘም ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ሦስት ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸውንም ሀገረ ስብከቱ በላከው በሪፖርት ገልጿል።በማያያዝም በመንግሥት በኩል አጥፊዎች ላይ እርምጃ መወሰድ የተጀመረ መሆኑንም ሀገረ ስብከቱ ገልጿል።

አስተዳደር ጉባኤው በምሦራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጥቃትና ሞት በእጅጉ ማዘኑን ገልጾ በዚህ መልኩ በኦርቶዶክሳዊያን ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ጥቃትና ሞት አሳዛኝና ድርጊቱም በጽኑ የሚኮነንና የሚወገዝ ተግባር ነው በማለት አውግዞታል።

ይህን የመሰለ በጭካኔ የተሞላ ድርጊትም መቆም የሚችልበት፣ወገኖቻችን ሕገ መንግስታዊ ከለላን በማግኘት በሰላም መኖር የሚችሉበት መንገድ መፈጠር አለበት ያለው አስተዳደር ጉባኤው በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ጉዳዩ ከፍ ባለ ደረጃ መታየት የሚገባው መሆኑን በማመን ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ውሳኔ ማግኘት ይችል ዘንድ ለቋሚ ሲኖዶስ ግብዓት የሚሆን ምክረ ሐሳብን አቅርቧል።

አስተዳደር ጉባኤው በተለያዩ ቦታዎች የሚከሰቱ ችግሮችን ተከትሎ አህጉረ ስብከት ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ሪፖርት ባደረጉ ጊዜ ጉዳዩን በማየት ውሳኔ የሚያስተላልፍ መሆኑን ገልጾ ሪፖርት ባልተደረገበትና በሚዲያዎች የተነገሩ መልዕክቶችን ብቻ መነሻ በማድረግ ውሳኔ ማስተላለፍ በተቋም ደረጃ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ስለሆነ አህጉረ ስብከት ችግሮች በገጠሟቸው ጊዜ ሁሉ በፍጥነት ሪፖርት
መላክ ይገባቸዋል ብሏል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-12-05 12:04:292023-12-05 12:04:36በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግድያ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አወገዘ።
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤ Link to: በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤ በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን... Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት መፍትሔ ሊሰጥባቸው ይገባል ያላቸውን በ13 ነጥቦች የተዘረዘሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሀገረ ስብከቱ በኩል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ውሳኔ አስተላለፈ። Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት መፍትሔ ሊሰጥባቸው ይገባል ያላቸውን በ13 ነጥቦች የተዘረዘሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሀገረ ስብከቱ በኩል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ውሳኔ አስተላለፈ። የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top