የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ቤተክርስቲያን የተፈተነችበት ሥርዓቷን እና ልጆችዋን ያጣችበት ጊዜ ስለሆነ ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም እንዲመጣ የጷጉሜን ፮ቀናት ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ።” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

September 4, 2023

ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የጷጉሜን ፮ ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲኖር አወጀ።

ዛሬ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በተሰጠው መግለጫ መሰረት የጷጉሜን ወር ፮ ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ መታወጁን ነው የገለጹት።

በመግለጫውም ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾም እና በጸሎት እንዲያሳልፉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ 13ተኛ ወር በሆነችው ወርሐ ጷጉሜ እለተ ምጽዓትን የምናስብበት ፤ ሠማይ የሚከፈትበት ፤ ጸሎት የሚሰማበት ሚስጥራዊ የሆነች ወር ነችና የበደሉንን ይቅር ብለን በንጹሕ ልቦና የቻልን ጾመን ያልቻልን በጸሎት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት እና የምንለምንበት ወር ሊሆን ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያን በዓላት ሲደርሱ ከሥርዓቷ እና ከአስተምሮዋ ውጪ በ ሆነ መልኩ የተለያዩ አካላት የዳንኪራ ጥሪ በማዘጋጀት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አግባብነት የሌለው መሆኑን እና ምዕመናንም ከዚህ እንቅስቃሴ እራሳቸውን ሊያርቁ ይገባል ነው ያሉት።

የማትደፈረዋን እና የማትነካዋን ቤተክርስቲያን የሚነኩ ሰዎች በዝተዋል ፤ ቀጣዩ ዓመትም ኢትዮጵያውያን በሰላም በፍቅር የምንኖርበት የሚራቡ የሚፈናቀሉ የሚያዝኑ ሰዎች እንዳይኖሩ ሁሉም ምዕመን ጠዋት ኪዳን ከሰዓት በሠርክ ጸሎት በየአብያተ ክርስቲያን በመሄድ ያልቻለም በየቤቱ ሊጸልይ ይገባል ብለዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-09-04 14:59:092023-09-04 14:59:09“ቤተክርስቲያን የተፈተነችበት ሥርዓቷን እና ልጆችዋን ያጣችበት ጊዜ ስለሆነ ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም እንዲመጣ የጷጉሜን ፮ቀናት ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ።” ብፁዕ አቡነ አብርሃም
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው። Link to: ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው። ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ ለመጠየቅ... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ በተባለው ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥያቄ አቀረበች። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ በተባለው ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥያቄ አቀረበች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top