የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሐዋርያዊ አገልግሎት መዳረሻቸው እስራኤል ገብተዋል።

December 11, 2023

ታኅሣሥ ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
++++++++++++++

ብፁዕ  አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፥ የባህር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ በእስራኤል ቴልአቪቭ ቤንጎርዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ  አቡነ ዕንባቆም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስና የገዳማቱ  አበው መነኮሳት ደማቅ አቀባባል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕነታቸው በዚህ ሐዋርያዊ ጉዟቸው በቅድስት ሀገር  ኢየሩሳሌም ገዳማት በመገኘት የገዳማቱን የሥራ እንቅስቃሴ የሚጎበኙ ሲሆን ገዳማቱ አንድነታቸው ተጠብቆ  የሚያካሒዱት አገልግሎት ሁሉ ሰላምና ፍቅር የነገሠበት ሆኖ የበለጠ ተጠናክሮ መበጠል የሚችልበትን መንገድ መሰረት ያደረገ ምክክር  እንደሚያደርጉ ታወቋል።

የገዳሙን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የበለጠ ለማስፋፋትና ለማጠናከርም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ዻዻስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሚሰጡት አባታዊ መመሪያ እና ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጋር በሚኖሩ የጋራ ሥራዎች ዙሪያም ጥልቅ ውይይት በማድረግ የገዳሙ ሰላምና አንድነት፣ የማኅበረ መነኮሳቱ ኅብረት ተጠብቆ አገልግሎቱ እንዲቀጥል ማድረግ የሚያስችል አስተዳደራዊ መመሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ለአምስት ቀናት  በእስራኤል በሚኖራቸው  የአምስት ቀናት ሐዋርያዊ አገልግሎት ቆይታ  ከእስራኤል የሃይማኖትና የቱሪዝም ሚኒስትሮችና በእስራኤል ከሚገኙ የአይሁድ እምነት መሪዎች ( ራብአዮች) ጋር  በመገናኘት በልዩ ልዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ታውቋል።

ፎቶ EOTC TV

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በሲነርጂ ሀበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው የሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፊልም ጽሑፍ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ታዘዘ። Link to: በሲነርጂ ሀበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው የሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፊልም ጽሑፍ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ታዘዘ። በሲነርጂ ሀበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በመዘጋጀት... Link to: በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ Link to: በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top