የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 14ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።

August 16, 2026
ነሐሴ 10ቀን 2018 ዓ.ም
የአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚደንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም ምክር ቤት የክብር ፕሬዚደንት አሥራ አራተኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከሐምሌ 5 ቀን 1986ዓ.ም. ጀምሮ ለ20 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በርእሰ አበውነት ሲመሩ ከቆዩ በኋላ በ76 ዓመት ዕድሜያቸው ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ሐሙስ ከንጋቱ 11 ስዓት ላይ በደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል የሕክምና ርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር የመደበላቸውን ጊዜ በታማኝነትና ይህ ቀረው በማይባል ስኬት አጠናቀው ከዚህዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል፡፡
ቅዱስነታቸው በጾመ ማርያም የመጀመሪያውን ሳምንት ሱባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቀድሰው በማቊረብና በማስተማር መሰንበታቸውና የመጀመሪያው ሳምንት ሱባኤ በተጠናቀቀበት ወቅት፦ “አባቶች ሱባኤው ተጠናቋል” በማለት በወቅቱ አብረዋቸው ለነበሩ ብፁዓን አባቶች መግለጻቸውና አባቶችም፦ “ቅዱስ አባታችን ገና እኮ ሳምንት ይቀራል” ሲሏቸው “የእኔን አጠናቅቄአለሁ”ማለታቸውን ብፁዓን አባቶች ያስታውሳሉ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በ1928 ዓ.ም. በትግራይ ክፍለ ሀገር በአድዋ አውራጃ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአቅራቢያቸው በሚገኘው የአባ ገሪማ ገዳም መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በመጀመር በዚሁ ገዳም ከዲቁና እስከ ምንኩስና መዓርግ የደረሱ ሲሆን፤ በመቀጠል የቤተ ክርስቲያንን ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጨርሰዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊው ዕውታቸው ጣምራ ችሎታ የነበራቸው ለመንበረ ማርቆስ የተገቡ ዓለም አቀፋዊ የጥበብ ሰው እንደነበሩ፡፡ የውጭ ምሁራን ሳይቀሩ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ታላላቅ ምሁራን ውስጥ አንዱ የሆኑና በኢትዮጵያ አርእስተ አበው (ፓትርያርኮች) ታሪክ ውስጥ ወደር ያልተገኘላቸው ብቸኛው ፓትርያርክ ናቸው” በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተውላቸው ነበር።
ስም ወደ ሥራ ይመራል እንዲሉ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመናገር ተሰጥዖ የነበራቸው፥ በወንጌል ስብከታቸው የብዙኃኑን ልቡና የዳሰሱና አጥንትን የሚያለመልም አንደበት የነበራቸው የወንጌል ገበሬ ነበሩ፡፡ ቅዱስነታቸው በፓትርያርክነት ዘመናቸው ያስመዘገቡት አስደናቂ ታሪክ ሁሉ በተጋድሎና በፍጹም የእምነት ጽናታቸው መሥዋዕትን ከፍለው የሠሩት እንጂ ነገሮች ሁሉ ቀና ሆነው የአልጋ በአልጋ የሆነ ውጤት የተመዘገበበት አልነበረም፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ለሀገር ሰላምና ዕድገት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ መልኩ በሀገራዊ ፍቅር በሰላምና በፍቅርበጋራ እንዲሠሩና ሀገራቸውን እንዲገነቡ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂነታቸው አማካኝነት ከፍተኛ ጥረትን አድርገዋል፤ ተጨባጭ ውጤትም አስመዝግበዋል፡፡ በተቋሙ ውስጥም በሁሉም የሃይማኖት አባቶች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያተረፉ አባትም ነበሩ፡፡
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000068.jpeg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-16 11:48:292026-08-16 11:51:34የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 14ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።
Search Search

Recent Posts

  • የደብረ ታቦር በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
  • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በባሕታዊ አባ ተስፋ ማርያም ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ኅዘን በመግለጽ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የብፁዕነታቸው አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል::
  • ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 14ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።
  • ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ Link to: ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ Link to: ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ። Link to: ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ። ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top