የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በወቅታዊ ጉዳይ በጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ከዓለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ጸሐፊ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ ጋር በወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ጉደይ ውይይት አደረጉ።

February 7, 2023

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በወቅታዊ ጉዳይ በጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ከዓለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ጸሐፊ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ ጋር በወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ጉደይ ውይይት አደረጉ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የመገናኛ ብዙኀን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ በሚገኘው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በመገኘት ከዋና ጸሐፊው ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ ጋር ውይይት አደረጉ። ብፁዕነታቸው ዋና ጸሐፊው በቅርቡ ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት በመመረጣችው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ስም የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል። ቤተ ክርስቲያናችን የምክር ቤቱ መስራችና ንቁ አባል በመሆን የበኩልዋን ሚና እየተወጣች መሆኑን አስታውሰው ይህ ግንኙነት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ወቅታዊ ሁኔታ ያብራሩላቸው ሲሆን የችግሩ ዋነኛ ምንጭ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና እና ሕግጋት የጣሱ ጥቂት አፈንጋጭ አካላት ድርጊታቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕልውና ላይ የሚያስከትለውን ታላቅ አደጋ በመገንዘብ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወገዙና የተለዩ ቢሆንም መንግስት የሕግ የበላይነትንና የሕዝብን ሰላም የመጠበቅ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ሃዘንና ጭንቀት ፈጥሯል። በዚህም ጳጳሳት እየተሳደዱ፣ ካህናተ እየታሰሩ፣ ምዕመናን እየተደበደቡ ይገኛሉ። እንዲህም ሆኖ ሕግ የጣሱት አካላት በንስሐና በይቅርታ ቢመለሱ ቤተ ክርስቲያን በሯን ክፍት አድርጋ እየጠበቀች ትገኛለች። ምክር ቤቱ ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ልዕልና፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለሰላምና ለፍትሕ አጋርነቱን እንዲገልጽ ብፁዕነታቸው ጠይቀዋል።

ዋና ጸሐፊው ለተደረገላችው ዝርዝር ማብራሪያ አመስግነው ይህች ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በወቅቱ የገጠማት ፈተና በእጅጉ አንደሚያሳስባቸውና ጉዳዩን በቅርበት መከታተላቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። በመጨረሻም በብጹዕነታቸው በኩል ለቅዱስ ፓትርያርካችን ሰላምታና መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ከብፁዕ አባታችን ጋር መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ሃይለ ጊዮርጊስ በስዊትዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የጄኔቫ አጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አመራር ተወካዮች በውይይቱ ተሳትፈዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ዋና ጸሀፊው በማግስቱ አጋርነታቸውን የሚያሳይ መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸው ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት የተመሰረተች፣ ሁልጊዜም ለአንድነትና ለሰላም የደም መስዋዕትነትም ጭምር ስትከፍል የኖረች ናት ብለዋል። አዲስ ሲኖዶስ ለመመስረት በሚደረገው ሙከራ ማዘናቸውን አክለው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠበቅ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠይቀዋል። የሚመለከታቸው የፖለቲካ ሃይላት ሁሉ ሕጋዊ ሰውነት ያላት ቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይዋን ባላት መንፈሳዊ ቀኖና እና ህግ ለመፍታት ብሎም የምዕመናኗን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝር መግለጫውን በዚህ ማስፈንጠሪያ ያንብቡ። https://www.oikoumene.org/news/wcc-expresses-solidarity-with-ethiopian-orthodox-tewahedo-church

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/photo_2023-02-07_16-05-38.jpg 768 1024 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-02-07 15:06:162023-02-07 15:06:16ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በወቅታዊ ጉዳይ በጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ከዓለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ጸሐፊ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ ጋር በወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ጉደይ ውይይት አደረጉ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ” በሚል ርዕስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም የመንግስት ኮምዩኒኬሽን የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ። Link to: “ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ” በሚል ርዕስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም የመንግስት ኮምዩኒኬሽን የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ። “ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ... Link to: To all diplomatic communities, Nation States, religious institutions, International Civic Societies (ICS), Non-Governmental Organizations (NGOs), and all International Communities (ICs) Link to: To all diplomatic communities, Nation States, religious institutions, International Civic Societies (ICS), Non-Governmental Organizations (NGOs), and all International Communities (ICs) To all diplomatic communities, Nation States, religious institutions, International...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top