የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ እንድትሆንና በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ተገቢው ክብርና እውቅና እንዲሰጣት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ጥረት እንዲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አሳሰበ።

March 12, 2024

መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም.
“””””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ
=============

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብሔራዊ ምክክር መድረኩ ተሳታፊ እንድትሆንና በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥም ተገቢው እውቅና ተሰጥቷት ለአድዋ ድል ያበረከተችውን አስተዋጽኦ የሚያመለክት መታሰቢያ እንዲደረግላት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በዛሬው እለት ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው አሳሰበ።

ጉባኤው ቅድስት ቤተክርስቲያን ትምህርት ሚኒስቴር በሌለበት ትምህርት ሚኒስቴር ሆና ብራና ፍቃ ቀለም በጥብጣ በማስተማር ሀገሩንና ቤተ ክርስቲያንን የሚወድና በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ በመፍጠር ያበረከተችው አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ ገብቶ በሃገራዊ ምክክር መድረክ ልትሳተፍ ይገባል ብሏል።

በተያያዘ ዜና ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን በአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጄክት ውስጥ በጦርነቱ ድል የነበራትን ከፍተኛ ሚና በሚገልጽ መልኩ ታሪኳ አለመቀመጡ ያሳዘነው መሆኑን የገለጸው ጉባኤው የአድዋ ድል ከብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ትሩፋቱ ባሻገር ሃይማኖታዊ ትሩፋቱ መነገር የሚገባው ታላቅ ድል መሆኑን በመግለጽ በአድዋ ድል ትልቅ ድርሻ ያላት ታላቂቱ ቤተ ክርስቲያን ለድሉ መታሰቢያ በተገነባው ሙዚየም ውስጥ አለመዘከሯ ስህተት ስለሆነ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዋን በማቅረብ በሙዚየሙ ውስጥ ተገቢና ትክክለኛ ቦታዋን እንድታገኝ መደረግ እንዳለበት አሳስቧል።

በሌላ በኩል ቤተ እምነቷ እየተቃጠለ፣ አገልጋይ ካህናትና ምዕመናን እየሞቱና እየተሰደዱባት የምትገኘው ቤተ ክርስቲያናች ለሚገጥሟት ችግሮች መፍትሔ እንዳታበጅና በሀገራዊ ምክክር መድረኩ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳይኖራት መደረጉ ተገቢ ስላልሆነ ሁለንተናዊ አቅሟን አጠናክራ በየደረጃው በሚደረጉ ሀገራዊ የምክክር መድረኮች ላይ መሳተፍ እንድትችል ከሚመለከተው አካል ጋር ውይይት እንዲደረግ በመወሰን የአስተዳደር ጉባኤው ውሳኔ በመሸኛ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲላክና በቋሚ ሲኖዶስ በሚደረሰው የውሳኔ ሀሳብ መሠረትም ተግባራዊ እንዲሆን ወስኖ የዕለቱን ስብሰባ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጸሎት አጠናቋል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው መግለጫ ሰጡ፣ Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው መግለጫ ሰጡ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ... Link to: የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የምክክር ጉባኤ በጠቅላይ ቤተክህነት በመካሔድ ላይ ነው። Link to: የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የምክክር ጉባኤ በጠቅላይ ቤተክህነት በመካሔድ ላይ ነው። የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top