የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በከሚሴ ሀገረ ስብከት የከሚሴ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመትን እና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን መታሰቢያ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

September 14, 2024

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም(በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል) መዝ 65:-11

መስከረም 1/2017 ዓ.ም
_______
የከሚሴ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና በሆነው በከሚሴ ከተማ ውስጥ ሁለት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ያሉ ሲሆን ሁለቱም በአንድ ሰበካ ጉባኤ የሚተዳደሩ ናቸው።
የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዚሁ እለት ሲከበር የመጀመሪያውን ከፍለ ጊዜ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የሀይቅ እስጢፋኖስ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መ/ር የሆኑት መ/ር አምደ ብርሀን የ2017 ዓመተ ምህረት በዓላትና አጽዋማት የባሕረ ሀሳብ ቀመር አውርደዋል።

በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ የአጥቢያዎች ወረዳ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል ክፍል ሃላፊ መ/ር ኤፍሬም መላኩ “ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም” ። መዝ 65:-11 የቅዱስ ዳዊትን የምስጋና ሃይለ ቃል መነሻ አድርገው እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ እለታትን ሳምንታትን ወርሀትንና ዐመታትን ሳያጎድል ሳይረሳ በየዓመቱ ለሰው ልጅ ይሰጣል/ያድላል በማለት ትመህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

በዚህ አዲስ ዓመት ሁላችንም የቆየ ቂምን ጥልን በመተው ንጹህ ሁነን ሥጋ ወደሙ ተቀብለን አዲስ ህይዎት ልንኖር ይገባልም ብለዋል። እኛ ኢትዮጵያውያን መስከረምን አዲስ ዓመት ብለን የምናከብረው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ :-መንግሰተ ሰማያት ቀርባለችና ንሥሐ ግቡ ጥርጊያውንም አሳምሩ እያለ ያስተማረበት ወር ሰለሆነ እና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምትረተ ርእሱን መታሰቢያ በማድረግ ነው ብለዋል ።

ከሁለተኛው የትምሀርት ክፍለ ጊዜ በመቀጠል ታቦተ ህጉ ሦስት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ከዞረ በኋላ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት: ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሳህል (ዐውደ ዓመትን ለመባረክ ለይቅርታና ለምህረት ማርያም ነይ የሚወለውን ወረብ አቅርበዋል)።
በመቀጠልም የደበሩ ሰንበት ትምህርት ቤት “ሰመዮ ብርሀነ በውስተ ጽልመት ለዘተወልደ እምብእሲት ተወልደ እምብእሲት : አእሚሮ ዮሐንስ እምከርሰ እሙ ሰገደ ወልደ መካን ለወልደ ድንግል
(ከሴት የተወለደው ብርሀንን በጨለማ ውስጥ ሾመው። የመካኒቱ ልጅ ዮሐንስ ለድንግል ልጅ አውቆ በእናቱ ማህጸን ውስጥ ሰገደ) የሚለውን ወረብ ካቀረቡ በኋላ የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ደጀን ተስፋዬ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አቅርበው በቃለ ምእዳን የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

መስከረም 1/2017 ዓ.ም
መረጃውን ያደረሰን ሀገረ ስብከቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳቸው መልእክት አስተላለፉ። Link to: ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳቸው መልእክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አዲስ... Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር አካሄደ። Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር አካሄደ። የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top