የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከብረ
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ምየምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ እጅግ ባማረ በድምቀት ተከብረ በበዓሉም ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የማይጨው አላማጣ እና ራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እና ማኅበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው የሥራ ኃላፊዎች ፣ አበው መነኮሳት ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል ።
በዕለቱም በሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የ76 ኛ ዓመት የቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓል በማስተባበር እንዲሁም ልዩ አስተዋፅኦ ላደረጉ የገዳሙ ባለሟሎች የሰርተፍኬት ስጦታ ተበርክቶላቸው በጸሎት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ።©ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
ሚዲያ