ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
ነሐሴ 11ቀን 2018 ዓ.ም አዲስአበባ -ኢትዮጵያብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአራት ሳይቶች ማለትም በአራት ኪሎ፣በፒያሳና በአሮጌው ቄራ አካባቢ የምታስገነባቸውን ግዙፍና ሁለ ገብ የሕንጻ የግንባታ ሥራዎች የሚገኙበትን አፈጻጸም ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ብፁዓን አባቶቹ በጉብኝታቸው ወቅት የግንባታ ሥራውን በሚያከናውኑ ባለሙያዎችና በጠቅላይ ቤተክህነት መሐንዲሶች ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በየሳይቶቹ ከተመዘገቡት ውጤቶች በመነሳት ቀሪ ሥራዎች በተቀላጠፈና ውጤታማ በሆነ መልኩ መከናወን እንዲችሉ አስፈላገው ክትትልና ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን በመግለጽ አመራር ሰጥተዋል።