የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።

August 25, 2026
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ከነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ አቀባበል ተደረገላቸው ።
በአቀባበሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ ኮንታ ከንባታና አላባ ጠንባሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መምሪያ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ልዩ ልዩ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች የክፍላተ ከተማ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል ።
መርሐ ግብሩ በጸሎተ ወንጌል ተጀመረ ሲሆን ለሥራ አስኪያጁ የሥራ ዘመን መመሪያ ይሆን ዘንድ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 20 ከቁጥር 26 ጀምሮ ተነቦ ለመርሐ ግብሩ ተስማሚ የሆነ ወረብ በቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ሊቃውንት መዘምራን
ቀርቧል ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ የሢመት ደብዴቤ ከተነበበ በኋላ የሀገረ ስብከቱ ክፍል ኃላፊዎች እና የክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ሊቃነ ካህናት በጉባኤው ፊት ቀርበው ትውውቅ ተደርጓል ። በሊቃውንትም ቅኔ ተበርክቷል ።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ስብከተ ወንጌልን፣ ሰበካ ጉባኤን ፣ሰንበት ትምህርት ቤትን በማደራጀትና በማስፋፋት ፣ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ልማትን እንዲያጠናክሩ ፣ ሕገ ቤተክርስቲያንን ጠብቀው የመልካም አስተዳደር ችግርና ሙስናን እንዲቀርፉ ኃላፊነት ተሰጥቶአቸዋል።
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ተ/ሃይማኖት ወልዱ ሰለ ሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያላቸውን የሥራ ክህሎት በመግለጽ ቤተ ክርስቲያንን አብረን እናሻግራት ማሻገር ባንችል ባለቤት ሆኖ የመሠረታት ክርስቶስ ያሻግራታል እኛ ሰጥመን እንዳንቀር ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል ምክራቸውን ለግሰዋል።
የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ተወካይ ክቡር መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በደብራችን ዘርፈ ብዙ ሰዋዊ እና የመሠረተ ልማት ተግባሮችን አከናውነዋል በማለት በዝርዝር የሠሯቸውን ሥራዎች አቅርበዋል።
መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነት እንደሚወጡ በሢመቱ ላይ የተነበበውን ዝርዝር መመሪያ በማንሳት አሁን ላይ ሀገረ ስብከቱን የተጋረጡበትን ተግዳሮቶች በጋራ እንቀርፋለን ብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሮሜ 3፣ 11 በመጥቀስ ወንጌል የሰውን ልጅ በኃጢአቱ እንደምትከስ በመጥቀስ ከውድቀታችን በንስሐ ልንመለስ ይገባል ብለዋል።
ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊነትና ታሪካዊ መሆኗን በመጥቀስ
” ተሿሚው ወንድምና ልጃችን ወደፊት በሚያከናውኗቸው ተግባራት ከብሔርና ከቡድን አሠራር ነጻ የሆነ መዋቅር ቤተክርስቲያንን ብቻ ማዕከል ያደረገ አድሏዊ ያልሆነና እውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ ሀሳብን በአሠራር በመዘርጋት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ልዕልና በማክበር የበላይ አካል መመሪያና ለሀገረ ስብከቱ የተሰጠውን ደንብ ጠብቀው በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር የፋይናንስና ንብረት አስተዳደሩን ግልጽ፣ ዘመናዊና ቁጥጥር የሚደረግበት በማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ፈጽመው እንደሚያጠፉ ትልቅ ተስፋና አደራ ጭምር ጥለንባቸዋል።”
ብለዋል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000073.jpeg 202 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-25 14:48:372026-08-25 14:48:37የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።
Search Search

Recent Posts

  • ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ወገን እናት እንጂ የቡድኖች መጠቀሚያ ልትሆን አይገባም ይበቃልን እንበል!” ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።
  • ከአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ ማሳሰቢያ
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለ272 አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።
  • የደብረ ታቦር በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ከአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ ማሳሰቢያ Link to: ከአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ ማሳሰቢያ ከአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ... Link to: ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ወገን እናት እንጂ የቡድኖች መጠቀሚያ ልትሆን አይገባም ይበቃልን እንበል!” ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ Link to: ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ወገን እናት እንጂ የቡድኖች መጠቀሚያ ልትሆን አይገባም ይበቃልን እንበል!” ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ወገን እናት እንጂ የቡድኖች...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top