የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅዱስ ሲኖዶስ በ፯ኛ ቀን ውሎው በአራት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ።

May 17, 2023

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ሰባተኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባካሄደው ውይይት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርቷን ለትውልዱ የታስተምርበት ተቋማት አንዱ መንፈሳዊ ኮሌጆች መሆነቸውን አውስቷል፡፡ እነዚህ ኮሌጆች ወጥ የሆነ ሕግ ሳይኖራቸው የቆየ ሲሆን በቅርቡም በሐዋሳ እና በወልቂጤ የተቋቋሙት ኮሌጆች ባቀረቡት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አድርጎ ለሁሉም መንፈሳዊ ኮሌጆች የሚያገለግል ወጥ የሚሆን ሕግ አዘጋጅቶ ማጽደቁን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡

በሌላ አጀንዳ በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጀርመን ገዳም እንዲኖራት ያቀረበው በጥናት የተደገፈ ሰነድ ጸድቋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ አማካኝነት በሰሜን አሜሪካ በካሊፎርኒያ የተመሠረተው የኆኅተ ሰማይ ገዳምን በተመለከተ ጉባኤው የተወያየ ሲሆን ; ብፁዕነታቸው ገዳሙ የተመሠረተበትን ሰነድ ለጥቅምት ጉባኤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት እንደሚያስረክቡ አስታውቀዋል፡፡

ጉባኤው የአእምሮ ንብረትን የተመለከተ ጉዳይም በስፋት ተወያይቷል። ይህ ኮሚቴ በርካታ ሥራዎችን ሲሠራ የነበረ መሆኑ ታውቆ አሁንም በተጠናከረ መንገድ እንዲሠራ በጀት እንዲያዝለት ተወስኗል፡፡ በሌላ አጀንዳ የምስጢራት መፈጸሚያ የሆነው የጸሎት መጽሐፍም እንዲታተም ተወስኗል፡፡

ጉባኤው የጡረተኞችን አበልን የተመለከተ ጉዳይም ላይ ተወያይቷል።
የጡረተኞችን አበልን የተመለከተ ተጠንቶ እንዲቀርብ በታዘዘው መሠረት ጥናቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በዕድሜያቸው በቤተክርስቲያን ሲያገለግሉ ቆይተው በአነስተኛ ደመወዝ ጡረታ የወጡ ማስተካከያ የሚደረግበት ውሳኔም ተለልፏል፡፡

የዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት ማኅበረ ደናግል አንድነት ገዳምን የተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የተወያየበት ጉዳይ ነው፡፡ ገዳሙ ከተመሠረተ ከአንድ ሺሕ ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ በዚህ ገዳም ላይ ተነሥቶ የነበረው ችግር በተመለከተ ቅዱስ ተወያይቶበት የውሳኔ ሐሳብ አሳልፏ፡፡ ውሳኔውም እናቶች በጥንት ገዳሙ ሲተዳደርበት በነበረው አሠራር መሠረት እንዲቀጥል ገዳማውያን እናቶች በጥያቄያቸውም መሠረት አምልኮአቸውን እንዲፈጽሙ ውሳኔ ተወስኗል፡፡

ይህም ሰፊ ውይይት ተደርጎበት የእናቶች ገዳም አሠራር መሠረት እናቶች በቆየው ትውፊት፣ በጥያቄያቸው መሠረትም አምልኮታቸውንን እንዲፈጽሙ በመወሰን የዕለቱ ስብሰባ ማጠናቀቁን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ አስታውቀዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከብረ
  • የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ የሰላምና የያብሮነት የጸሎት መርሐ ግብር ” ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን ” በሚል መሪ ቃል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሌሎች ሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት አደረገ
  • የአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል 1ኛ ዓመት የቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት ተከበረ
  • በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ
  • ደንበኛ ተኮር ስርዓት የወለደው የነዋሪዎች አንድነት ከድርጅቱ አልፎ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋርም እያስተሳሰረ መሆኑ ተገለጸ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ውሎን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጡ። Link to: የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ውሎን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጡ። የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው... Link to: የግንቦት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ ፲ ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። Link to: የግንቦት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ ፲ ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። የግንቦት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top