የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በምሁር ኢየሱስ ገዳም የአዲሱን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቡራኬን ተከትሎ ሲከበር የነበረው በዓል ተጠናቀቀ

May 3, 2026

ሚያዚያ ፳፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ.ም
በታላቁ አባት በአቡነ ዜና ማርቆስ የተገደመው የምሁር ኢየሱስ ገዳም ሚያዚያ ፳፬ ቀን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፀሎተ ቡራኬ ታቦታቱ ከነበሩበት መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ወጥተው ወደ አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስታያን መግባታቸው ይታወሳል።በዓሉ በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ታቦታቱ ታጅበው ወጥተው በልዩ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዕለቱ የሕንጻ ሥራውን አስመልክቶ በገዳሙ አበመኔት በመምህር አባ ዘኢየሱስ ቀርቧል።
በሪፖርቱ መነሻም የምሁር ኢየሱስ ገዳም አንጋፋ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ምስረታውም ከ840 ዓ.ም በፊት በ13 ክ.ዘመን እንደተገደመ እና የገዳሙ መስራች ጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ 3 ጊዜ ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ወደ ገዳሙ ማድረጋቸው ተገልጧል።
በወቅቱ ሕዝቡ እግዚያብሔርን ከማምለክ ወደ ባዕድ አምልኮ ተሻግሮ የነበር ቢሆንም ጻድቁ ሕዝቡን አስተምረው ወደ እግዚአብሔር መመለሳቸው ተወስቷል።
ጻድቁ ለሁለተኛ ዙር ሲመጡም 156 አብያተ ክርስቲያናትን በአካባቢው ማሠራታቸውም ነው የተገለፀው።
ከገዳሙ ታሪክ ጋር ተያይዞም ጻድቁ በዘመናቸው የሠሩት ዘርፈ ብዙ ገድልና ታሪካቸው ታውሷል።
በዘመኑም ገዳሙ በኑቡረ ዕድ ይተዳደር እንደነበር እና እንደ አክሱምና ጎንደር የትምህርት ተቋም ሆኖ ለዘመናት የቆየ መሆኑም ተጠቅሷል።በዘመናት ሂደት በዋናነትም ከመሬት ላራሹ ጀምሮ ገዳሙ እንደተዳከመም ያነሱት የገዳሙ አበመኔት አባ ዘኢየሱስ ከ1988 ጀምሮም በድጋሚ ገዳሙ በብፁዕ አቡነ መልከ ጼድቅ ካልዐይ ጥረት ማንሰራራቱን ጠቅሰዋል።
ዛሬ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንም 17 ዓመት መፍጀቱ በሪፖርቱ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ሥራ የተጀመረው በብፁዕነታቸው በ2000 ሲሆን በ2002 ብፁዕነታቸው ማረፋቸው ተገልጿል።
በወቅቱ በወልቂጤ በአዲስ አበባ በሰበታ የጀመሯቸው ትምህርት ቤት እና የሕንጻ ሥራ የነበር በመሆኑ ከጀመሯቸው የልማት ሥራዎች ጋር ይህም የሕንጻ ሥራ ለፍጻሜ መብቃቱ ተገልጿል።
የሕንጻ ሥራውን አስመልክቶ የፈጀው የገንዘብ መጠን በሪፖርት ያልቀረበ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ አባ ዘኢየሱስ በምክንያትነት ያቀረቡት ከሕሊና ጀምሮ ብዙ መዋዕለ ነዋይ የፈሰሰበት በመሆኑ ገንዘብ አይተምነውም ነው ያሉት።
በተጨማሪም ለሕንጻ ሥራው ከሳንቲም ጀምሮ ከፍተኛውን ብር የሰጡ በእግዚአብሔር ፊት እኩል በመሆናቸው ለይቶ ማመስገን እንደማይቻል ነው በምክንያትነት የተጠቀሰው።
ከዚህም የተነሳ በሌሎች አብያተ ክርስቲያን እንደተለመደው የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ያልተከወነ ሲሆን ከዚያ ይልቅ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎተ ማርየም እንዲጸለይላቸው ተደርጓል።
በገዳሙ የበዓላትን ቀንን ጨምሮ የገንዘብ አሰባሰብ የማይደረግ መሆኑም ተገልጿል።
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በገዳሙ መነኮሳት እና መነኮሳይት የተሳለ ኢትዮጵያዊ መልክ ባላቸው ቅዱሳን ያጌጠ ሲሆን አንዳንዶቹም ማብራሪያ የሚሹ በመሆናቸው ወደፊቱ በመጽሔት ማብራሪያ እንደሚቀርብበት ተነግሯል።
በዕለቱም ብፁዓን አባቶች ትምህርተ ምዕዳን የሰጡ ሲሆን የብፁዕ አቡነ መልከ ጼድቅ ካልዓይ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ከብፁዓን አባቶች ጋር የነበራቸውም ቆይታ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ በትዝታ የዳሰሱበት ነበር።
ትላንት ሚያዚያ ፳፬ በነበረው መርሐ ግብርም ለብፁዕነታቸው የተሠራው መታሰቢያ ሀውልትና ቤተ መዘክር መመረቁ ይታወሳል።
በዕለቱ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ቅኔ የቀረበ ሲሆን በደብሩ ካህናትም ወረብ ቀርቧል።
በበዓሉ ላይ ከአዲስ አበባና ከወረዳው የመጡ በርካታ ምዕመናን ፣ የሙር አክሊል ወረዳ አስተዳዳር አቶ ብስራት ገብሩ እና ሌሎችም የመንግሥት ኃላፊዎች፣የእንድብር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ተገኝተዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ለካህናት የቅዳሴ አልባሳትም በስጦታ አበርክተዋል።
በመጨረሻም ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለገዳሙ አበመኔት ለመምህር አባ ዘኢየሱስ የሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኖ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።©E.o.t.c.tv.

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/003.jpg 427 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-03 08:26:462026-05-05 08:30:00በምሁር ኢየሱስ ገዳም የአዲሱን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቡራኬን ተከትሎ ሲከበር የነበረው በዓል ተጠናቀቀ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ታሪካዊው የምሁር ኢየሱስ ገዳም አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ Link to: ታሪካዊው የምሁር ኢየሱስ ገዳም አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ ታሪካዊው የምሁር ኢየሱስ ገዳም አዲሱ ሕንጻ ቤተ... Link to: EOTC TV | የሕንጻዎችና የቤቶች አስተዳደር ድርጅት ትንሣኤ Link to: EOTC TV | የሕንጻዎችና የቤቶች አስተዳደር ድርጅት ትንሣኤ EOTC TV | የሕንጻዎችና የቤቶች አስተዳደር ድርጅት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top