የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቤተክርስቲያን ለምታስገነባቸው ሕንጻዎች በልዩልዩ ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍ ላደረረጉ ባለሙያዎች የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ።

February 10, 2026

የካቲት ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቤተክርስቲያን ለምታስገነባወቸው ሕንጻዎች የጨረታ ኮሚቴ በመሆንና በልዩልዩ የሙያ ዘርፎች ድጋፍ ላደረጉ ባለሙያዎች የዕወቅናና የምስጋና መርሐ ግብር በተካሔደበት ጊዜ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ክቡራን ልጆቻችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ያደረገችላችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ
ላበረከታችሁት ሙያዊ አስተዋጽኦ ምስጋናችን ይድረሳችሁ ካሉ በኋላ ይህንን የቤተክርስቲያን ጥሪ ተቀብላችሁ ጊዜና እውቀታችሁን አስተባብራችሁ ፈተናውን ሁሉ በጽናት አልፋችሁ ሠራችሁን በውጤታማነት ስላከናወናችሁ ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ታመሰግናችኋለች ወደፊትም ጥሪዋን ተቀብላችሁ ተግባራዊ ምላሽ እንደምትሰጡ እምነታችን የጸና ነው
ብለዋል።

ባለሙያዎቹም ቤተክረስቲያን ላደረገችላቸው ምስጋናና ለሰጠቻቸው ዕውቅና በማመስገን የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በማንኛውም ጊዜ ቤተክርስቲያን በምታደርግላቸው ጥሪና ሙያዊ አገልግሎታቸውን በምትፈልግበት ጊዜ ሁሉ ድጋፋቸውን ያለ ስስት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ ቃል ገብተዋል።

ቤተክርስቲያን ሞሁራን ልጆቿን በማሳተፍ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ሁለንተናዊ የልማት ሠራዋን አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑም የማኅበራዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ በመርሐ ግብሩ ላይ ገልጸው ለባለሙያዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመቀጠልም ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ የጠቅላይ
ቤተክህነት ሕዝብ ግኔኙነት መሥሪያ ኃላፊና የቤ/ሕ/አ/ል/ድርጅት ዋና ሥራ አክኪያጅ በበኩላቸው ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በመንፈሳዊ፣ማኅበራዊና ልማታዊ የሥራ ዘርፎች እያስመዘገቡ ያለውን ውጤት አድንቀው የቤተክርስቲያን ልጆች የሆናችሁ ባለሙያዎች የምታደርጉት ሙያዊ ድጋፍ ለቤተክርስቲያን ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለው ምስጋና ይገባችኋል ካሉ በኋላ ለኸደፊትም ይኸው ትብብራችሁፐተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ለኮሚቴ አባላቱ ቤተክርስቲያን ያዘጋጀችላቸውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተቀብለው የመርሐግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
  • በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ ደብረ ፀሐይ ብዙኃን ማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባርኮ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። Link to: በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ ደብረ ፀሐይ ብዙኃን ማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባርኮ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ... Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የገንዘብ አስተዳደሩን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ወጋገን ባንክ አማራጭ መንገድ አቀረበ። Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የገንዘብ አስተዳደሩን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ወጋገን ባንክ አማራጭ መንገድ አቀረበ። የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top