የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዓን አባቶች በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ሕሙማንን ጎበኙ

April 8, 2026

መጋቢት 30/7/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ኦስፒታል በመገኘት በእመም ላይ ያሉ ሕሙማንን ጎብኝተው ማዕድ አጋሩ፣የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፋ አደረጉ።
ጉብኝቱ የተካሄደው የትንሳኤ በዓል መንፈሳዊ ትርጉምን በተግባር ለማሳየት ሲሆን፣ በበዓሉ ወቅት በሕክምና ላይ ያሉ ወገኖች እንዳይረሱ እና ከማህበረሰቡ ጋር እንደተገናኙ እንዲሰማቸው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት ሕሙማኑን በማበረታታት፣ የህክምና ባለሙያዎችን ማመስገንና መንፈሳዊ ድጋፍ ማድረግ የቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባሯ መሆኑን ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው የታመመውን መጠየቅና የታረዘውን ማልበስ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ መሆኑን ገልጸው፣ ሕሙማኑ ፈጣን ፈውስ እንዲያገኙ እግዚአብሔርን በጸሎት ጠይቀዋል። የእንኳን አደረሳችሁ መልህክታቸውንም አስተላልፈዋል።ዶክተር ራኤል የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አመሰራረት እና የሚሰጡትን አገልግሎቶች በመግለጽ፣ “አባቶቻችን በተጣበበ ሰዓት በዚህ ስፍራ መገኘታቸው ለታካሚዎቻችን ተስፋ ሲሆን ለእኛ ደግሞ ታላቅ ማበረታቻ ነው” ብለዋል።
በዚሁ ጊዜ ለበዓል መዋያ የሚሆን 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር እና የተለያዩ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍና ከማድረጋቸውም በላይ ለሕሙማኑ ማዕድ አጋርተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ከብፁዓን አባቶች ጋር ዶክተር አካለ ወልድ ተሰማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ፣መጋቤ ካህናት አባ ሃብተጊዮርጊስ አስራት የገዳማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም መላከ ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ የሦስቱ ክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተገኝተዋል።
የጥቁር አንበሳ ኦስፒታል አስተዳደር በተደረገው ጉብኝትና ድጋፍ ከፍተኛ ደስታ እንዳላቸው ገልጸው፣ ይህ ዓይነት ማህበራዊና መንፈሳዊ ድጋፍ ለሕሙማን ትልቅ ኃይል እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
በመጨረሻምብፁዓን አባቶች እና የመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን በሕመምላይ የሚገኙትን ታማምዎችን ተዘዋውረው በመጠየቅና ለሁሉም ፀሎት በማድረግ ጉብኝቱ ፍጻሜውን አግኝቶአል ።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0029.jpg 480 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-04-08 10:13:522026-05-05 10:15:21ብፁዓን አባቶች በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ሕሙማንን ጎበኙ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የጌታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት በዓል በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በከታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡ Link to: የጌታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት በዓል በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በከታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት... Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ በልማት ምክንያት ለተነሱ ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ በልማት ምክንያት ለተነሱ ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top