የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በዶምቢዶሎ ሎና በቄለም ወለጋ ልዩልዩ የልማት ሥራዎችን አከናወኑ ለችግረኛ ተማሪዎችም የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አየረጉ።

September 22, 2023

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላ፣የአስሳ፣የቄለም ወለጋና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደምቢዶሎ ከተማ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ አገልግሎት በደምቢዶሎ ከተማ ቀበሌ03 በአርባ ቀናት ተሰርቶ የተጠናቀቀውን የቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን መስከረም 6ቀን 2016ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱን ማክበራቸውን የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ገልጿል።አያይዞም በሀገረ ስብከቱ ከማገኙ 13ወረዴዎች መካከል የቅዱስ ሲኖዶስን መዋቅር በመተው በኦሮሚያ ሲኖዶስ ስር እንገለገላለን በማለት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ተነጥለው የሰነበቱ ሊቃነ ካህናት በድርጊታቸው በመጸጸት አንድ ፓትርያርክ ፣አንድ ሲኖዶስ፣አንድ መንበር፣አንዲት ቤተክርስቲያን በማለት ወደ እናት ቤተክርስቲያን ተመልሰዋል ብሏል።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል መስከረም 10 ቀን 2016ዓ.ም የከተማዋ ከንቲባና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው በተገኙበት አዲሱ የትምህርት ዘመንን መጀመር በማስመልከት ወላጅ አልባና ረዳት ለሌላቸው እጓለማውታ ልጆች ሃያ ካርቶን ደብተርና እስኪርቢቶ በመግዛት ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጸው ዘገባው የከተማ አስተዳደሩ ለሀገረ ስብከቱ ባበረከተው ሃያ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ለመትከልና መዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት ለመክፈት ብፁዕነታቸውና የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በተያያዘ ዜና በደንቢዶሎና በቄለም ወለጋ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት የሚገኙ ካህናት፣ የምዕመናን ተወካዮች፣የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ባደረጉት ስብሰባ የቤተክርስቲያንን አንድነትና ህልውና በማጽናት ለሰላምና ለአንድነት በጋራ እንደሚቆሙ ገልጸው ፓትርያርካችን አቡነ ማትያስ ጳጳሳችንም አቡነ ሩፋኤል ናቸው።ከአሁን በፊት ከሲኖዶስ እውቅና ውጪ የተሾሙትን አንቀበልም።የሚል የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይታቸውን ማጠናቀቃቸውን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ገልጿል።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በከተማው ቀበሌ 04 አካባቢ ለሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት መገልገያ የሚሆን ሕንጻ በአራት ሚሊየን ብር መግዛቱን የገለጸው የሀገረ ስብከቱ ዘገባ ሕንጻውን በቅዱስ ፓትርያርኩ በቅርቡ ለማስመረቅ ሀገረ ርብከቱ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።

ብፁዕነታቸው ባለፉት ሁለት ወራት በሀገረ ስብከቱ ሲያካሒዱ የቆዩትን ሐዋርያዊ አገልግሎት ከመስከረም 15 ቀን ጀምሮ በማጠናቀቅም በጋምቤላና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በመቀጠል በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚያቀኑ ይሆናል ሲል የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ጨምሮ ገልጿል።

Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥሪ ተላለፈ። Link to: የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥሪ ተላለፈ። የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥሪ ተ... Link to: በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ወታደሮች ከተዘረፉ የብራና መጻሕፍትና ልዩ ልዩ ንዋየ ቅድሳት መካከል እንደሆነ የሚገመት አንድ ጽላት እና የተለያዩ ቅርሶች በበጐ አድራጊዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የርክክብ ሥነ ሥርዓት በታላቋ ብሪታንያ ለንደን ከተማ ተከናወነ። Link to: በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ወታደሮች ከተዘረፉ የብራና መጻሕፍትና ልዩ ልዩ ንዋየ ቅድሳት መካከል እንደሆነ የሚገመት አንድ ጽላት እና የተለያዩ ቅርሶች በበጐ አድራጊዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የርክክብ ሥነ ሥርዓት በታላቋ ብሪታንያ ለንደን ከተማ ተከናወነ። በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ወታደሮች ከተዘረፉ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top