የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር ባካሔደው የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ነዳያንን ከመገቡ በኋላ ቃለ በረከትና ቃለ ቡራኬ ሰጡ።

February 8, 2025

ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም
================
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዛሬ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ባዘጋጀው የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ነዳያንን በጋራ ከመገቡ በኋላ ቃለበረከት፣ቃለምዕዳንና ቃለቡራኬ ሰጥተዋል።

በዚሁ ጊዜም ማኅበሩ በተለይም በ2016ዓ.ም በጀት አመት ያከናወናቸውን መንፈሳዊ፣ማኅበራዊና ልማታዊ የሥራ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ በቪዲዮ የተቀነባበረ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን የማኅበሩ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መምህር ኤልያስ ሙላቱ በማኅበሩ የተከናወኑ ዋናዋና ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ አዳምጠዋል።

የማኅበሪ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ በመልዕክታቸው ቅዱስነታቸውና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች ማኅበሩ ባዘጋጀው የምገባ መርሐ ግብር ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል።

በመቀጠልም ቅዱስ አባታችን ቤተክርስቲያንን ለመምራት ወደዚህ የተቀደሰ ኃላፊነት ከመጡ ጀምሮ ፍጹም በሆነ ቅድስናና ንጽሕና፣ትህትናና ትዕግስተኝነት ያከናወኑት ሐዋርያዊ አገልግሎት በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ መሆኑን የሚያረጋግጠው በቤተክርስቲያናችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የገጠማት ፈተናዎችን ሁሉ በቅዱስታቸዎ ጽኑ ጸሎት ያለፈቻቸው መሆኑን ጠቁመው የቅዱስነታቸው ጽኑዕ አቋምም ቤተክርስቲያናችን በቀጣይ ይገጥማት የነበረው አደጋ በእጅጉ የቀነሰ መሆን የቻለው በቅዱስነታቸዎ አርቆ አሳቢነትና ትዕግስት መሆኑን እኛ የመንፈስ ቅዱስ ልጆችዎ የምናቀው ሃቅ በመሆኑ በቅዱስነትዎ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፍጹም ደስተኞች መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ።ብለዋል።

በመጨረሻም ማኅበራችን ከጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና ማግኘቱን ተከትሎ ከዚህ በኋላ የማኅበራችን ሥራዎችን በሙሉ በቅዱስነትዎ አመራር ሰጪነትና በጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራት ማደራጃ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ በኩል ተቋማዊ በሆነ መንገድ ብቻ ሥራችንን በመፈጸም የሚጠበቅብንን አገልግሎት በብቃት የምንወጣ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እወዳለሁ ብለዋል።

አያይዘውም ማኅበራችን ሕጋዊ ቅርጽ ኖሮት በቤተክርስ
ቲያናችን ሕግጋት መሰረት ሥራውን ማከናወን እንዲችል እና ሕጋዊ ፈቃድ እንዲያገኝ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ከፍተኛ አባታዊ ድጋፍ ላደረጉልን ለብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ያለኝን ከፍተኛ ክብር በቅዱስነትዎ ፊት ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።በማለት መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መምህር ኤልያስ ሙላቱ ማኅበሩ በተለይም በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በመንፈሳዊ፣ማኅበራዊና ልማታዊ ሥራዎች ያከናወናቸውን ዝርዝር ተግባራትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ዝርዝር ሪፓርት ያቀረቡ ሲሆን ማኅበሩ በበጀት ዓመቱ ብር 968,534,947,00 (ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ )ወጪ በማድረግ ስኬታማ ሥራን አከናውኗል ብለዋል።

በተያዘው መርሐ ግብር መሰረትም ቅዱስነታቸውና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በነዳያን ምገባ መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ድሆችን የሚረዳው ልጃችንን ሥራዎች ለማየት በመገኘታችን ደስተኞች ነን ድሆችን የሚያበላ፣የታመሙትን የሚረዳ፣የታረዙትን የሚያለብስ ንዑድ ክቡር ነው እግዘብሔር የሚወደው ትልቁ ነገርነው ይሔ ነውና ካሉ በኋላ እግዚአብሔር ለሰዎች ሀብት የሚሰጠው ሀብቱን ለድሆች እንዲያካፍል ነው።ልጃችን የሚያደርገው መልካም ሥራ እግዚአብሔር የሚያዘውንና የሚወደውን ነው መሔድም መብላትም ያቃታቸውን የሚንከባከበው ልጃችንን እግዚአብሔር ይጠብቅህ፣ሐብትን ንብረትህን ይባርክልህ በማለት መልዕክታቸውን ካጠቃለሉ በኋላ ቃለ በረከትና ቃለ ምዕዳን በመስጠት መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበራት ማደራጃ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን የማኅበራት ምዝገባ መስፈርቶችን በማሟላት ሕጋዊ ዕውቅናና ፈቃድ የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡ Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የአክትስ ቸርች ኦፍ ሱዲን የሥራ ኀላፊዎችን   በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የአክትስ ቸርች ኦፍ ሱዲን የሥራ ኀላፊዎችን   በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top