የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የአክትስ ቸርች ኦፍ ሱዲን የሥራ ኀላፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

February 8, 2025

የካቲት 1 ቀን 2017.ዓ.ም.
+ + +
ለበርካታ ዓመታት ከክርስቲያናዊ ተራድኦና ልማት ኮምሽን ጋር በመተባበር የአስቸኳይ የምግብና ምግብ ያልሆኑ ርዳታ በማቅረብ፣ የመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ዘርፈ ብዙ ቁሳቁሶችን በማገዝ ፣ ለአርሶ አደሮች የምርጥ ዘር በማቅረብ፣ በፕሮጀክት የታቀፉ የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚጨምሩ ሥራዎችን በማገዝ፣አቅመ ደካማ እናቶችን በከብት ርባታ ራሳቸውን እንዲደግፉ በመርዳት፣ በጤና ፣ በሕፃናት ምገባ እና በአቢያተክርስቲያናት አጸድ ልማት ዙሪያ በመሥራት እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ክንውኖችን ሲያከናውን የነበረው የሲውዲን ቤተክርስቲያን የልማት ክንፍ ኀላፊዎች ከጥር 29 ቀን 2017ዓ.ም እስከ የካቲት 1 ቀን 2017ዓ.ም. በኢትዮጵያ ቆይታ ለማድረግ የመጡ ሲሆን በቆይታቸው ማገባደጃ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ለማግኘት በልማት ኮምሽን የበላይ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል አማካኝነት ፕሮግራም እንዲያዝላቸው ተደርጎ ከቅዱስነታቸው ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮምሽን፣ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ድርጅት ሊቀ ጳጳስ
ኤሪክ ሌይሰን የአክትስ ቸርች ኦፍ ሲውዲን የግሎባል ዳይሬክተር
ካሪክ ሁግሰን የአክትስ ቸርች ኦፍ ሲውዲን የፖሊሲ አማካሪ
አቶ ብርሃኑ ይስማው የአክትስ ቸርች ኦፍ ሲውዲን በኢትዮጵያ ተወካይ
ኢንጂነር ይልቃል ሸፈራው የልማት ኮምሽን ኮምሽነር
መልአከ ሕይወት አባ ሐይለ ገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ እና ሌሎችም በኮምሽኑና በብፁዕ ወቅድስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ድርጅቱ ለዓመታት በሰበአዊ ርዳታ፣ በቤተክርስቲያን አጸድ ጥበቃ፣ በልማት እና በኢኮኖሚ፣ በጤና እና በሕፃናት ምገባ ላይ ያደርገው የነበረውን እግዛ እውቀና የሰጠና ከዚህ በኋላም በልዩ ልዩ ሥፍራ አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን ለማገዝ የሚያስቸል ነው ።

መርሐ ግብሩን የመሩት የኮምሽኑ ኮምሽነር ኢንጂነር ይልቃል ሽፈራው ሁሌ እንደምናደርገው በደብዳቤና በሪፖርት ከመገናኘት ባሻገር እንዲህ ገጽ በገጽ ተገናኝተን መነጋገሩ ለሥራችን ሠፊ መንገድ ይከፍታል ብለን እነዚህ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ይዘን መጥተናል። ከድርጅቱ ጋር የነበረን የሥራ ግንኙነት ከቅዱስነትዎ የተሰወረ ስላልሆነ እነዚህን የሥራ ኃላፊዎች እንዲባርኩልን በማለት ቅዱስነታቸውን ጋብዘዋል።

ቅዱስነታቸውም ንግግራቸውን ሲጀምሩ የሚፈናቀል፣ የሚሰደድ፣ የሚራብና የሚጠማ እንዲሁም በመድኃኒት እጦት የሚሰቃይ ሰው ባለበት ዘመን እጁን ለእርዳታ የሚዘረጋ ሰው መኖሩ የእግዚአብሔር ቸርነቱ እንዳልተለየን ትልቅ ማሳያ ነው። በርግጥም እናንተ የቸርነት ሰዎች ወደ ሀገራችን በመምጣት በልዩ ልዩ ዘርፍ ስለምትረዱን እናመሰግናለን። ያኔ በሰላም በምንንኖርበት ዘመን ከጎናችን እንደነበራችሁ ሁሉ አሁንም ግማሹ በጦርነት፣ ሌላው በኑሮ ውድነት እየተሰደደ ባለበት ዘመን ከጎናችን በመሆናችሁ የዘመናት ታማኝ አጋዦቻችን መሆናችሁን ተገንዝበናል። በመሆኑም ስለምታደርጉልን ማንኛውም ትብር ሁሉ በጣም እናመሰግናለን። የሰው ልጅ ሰውነቱ የሚለካው ለወንድሙ በሚያደርገው እገዛ ነው። ዓለማችን ካልተረዳዳች ልትቀጥል አትችልም። ይህ ገብቷችሁ መረዳዳትን ሥራችሁ አድርጋችሁ ከእኛም ጋር ስለምትሠሩ በጣም እናመሰግናለን ብለዋል።

የቅዱስነታቸውን የምስጋና ቃል የሰሙት ሚስተር ኤሪክ ስለተደረገልን አቀባበል እናመሰግናለን ከዚህ በፊት እናደርገው እንደነበረው እርሱን እንቀጥላለን። ይህ ዘመን ክርስቲያኖች አንድነት ፈጥረው እንዲንቀሳቀሱ ያስገደደ ዘመን ነውና እኛም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጋር ተባብረንና አንድነት ፈጥረን እየሠራን በመሆኑ ደስታችን ወደር የለውም ብለዋል።

በመጨረሻም ይህንን ሥራ በሲውዲን እያንቀሳቀሱ ላሉ ኀላፊዎች በክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮምሽን የተዘጋጀ ስጦታ በቅዱስነታቸው ተበርክቶ የውይይቱ ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር ባካሔደው የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ነዳያንን ከመገቡ በኋላ ቃለ በረከትና ቃለ ቡራኬ ሰጡ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር ባካሔደው የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ነዳያንን ከመገቡ በኋላ ቃለ በረከትና ቃለ ቡራኬ ሰጡ። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በእስራኤል ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በእስራኤል ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top