የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀስት – ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው”

September 27, 2024

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እጅግ የምንወዳችሁ እና የምናከብራችሁ በሀገረ ስብከታችን ፣ በመላው ዓለም የምትገኙ ክርስቶሳውያን ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንኳን ለ2017 ዓ.ም የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!
“ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀስት – ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው”
መዝ 59፥4
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ከዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ይህ የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል ነው። ደመራ የሚለው ቃል ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን የሚገልጸው ደግሞ መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣ መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ነው። ቅዱስ መስቀሉ የተገኘበት በዓልም ስለሆነም ደመራ እንጨቶች የሚደመሩበት የበዓለ መስቀል ዋዜማ ነው።

ይህን በዓል የምናከብርበት ምክንያት አይሁድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተለያዩ ገቢረ ተዓምራትን ሲያደርግ በመመልከታቸው በቅናት ተነሳስተው ቀብረውታል ቦታውንም የቆሻሻ መጣያ አድርገው ቆይተዋል። ኋላም የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት በሆነችው ንግሥት ኅሌኒ አማካኝነት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል ከተቀበረበት እንደወጣ ከመጽሐፈ ስንክሳራችን እንረዳለን።
መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን የመቀደሳችን ዓርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን፥ የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መንበር፥ ሲሆን አምላካችንን የምንመለከትበት መስታወት ነው።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “መስቀሉ ለወልድ ለነፍስየ ፀወና – የወልድ መስቀል የነፍሴ መጠጊያዋ ነው” ይላል። ይህ ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ መስቀሉ ስላደረገልን የማዳን ሥራ ሲያስረዳን ነው።
ለእኛ ለክርስቲያኖች ቅዱስ መስቀል ኃይላችን ፣ ቤዛችን ፣ ምልክታችን ፣ መጠጊያችን. . ነው። ስለዚህ ይህንን የቅዱስ መስቀል በዓል ስናከብር ታላቅ መንፈሳዊነት በተመላ መልኩ ሊሆን ይገባል። በቅዱስ መስቀሉ የተደረገልን ዕርቅ ፣ ሰላም ፣ ድኅነት ፣ ዕድገት… ነው። እኛም ይህንን በዓል ስናከብር አምላካችን ያደረገልንን ማዳን እያሰብን ፣ በአፋችን የሰላምን መዝሙር እየዘመርን ፣ ይቅር እየተባባልን ፣ የተቸገሩትን እየረዳን መልካም ነገሮችን በሙሉ በማድረግ በመንፈሳዊ ስርዓት ልናከብር ይገባል።

ወቅታትን ፣ ዓመታትን ፣ አዝማናትን እንደየስርዓቱ የሚያፈራርቅ ፥ ፍጥረታትን የሚመግብ የቸርነት እና የይቅርታ ባለቤት አዲሱን ዓመት የተባረከ ዘመን ያድርግን። ከቅዱስ መስቀሉ ረድዔት በረከት ያሳትፈን።

እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክልን
አባ ገሪማ
የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/photo_2024-09-27_15-04-50-cover.jpg 413 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-09-27 13:06:312024-09-27 13:06:31“ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀስት – ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው”
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ የመስቀል ደመራ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top