የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በ ፳፻፲፭ ዓ/ም አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

September 6, 2023

ጳጉሜን ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በ፳፻፲፭ ዓ/ም የሥራ ዓመት በነበረው የሥራና የአገልግሎት አፈጻጸም ዙሪያ አጠቃላይ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አሥኪያጁ በብፁዕ አቡነ አብርሃም መሪነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ሠፊ ውይይት አደረጉ።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ባደረጉት የመግቢያ ንግግር “ስለ እግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት በጀመረው ሥራ ሁሉ፥ በሕጉና በትእዛዙም፥ አምላኩን ለመፈለግ በፍጹም ልቡ አደረገው፥ ተከናወነለትም።” 2 ዜና 31÷21

“እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ የሚሄድበትም መንገድ ተከናወነለት፤” 2 ነገሥት 18÷7 የሚሉትን የቅዱሳት መጻሕፍት መልእክቶች መነሻ በማድረግ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች የተሠማሩት ሥራ ላይ ብቻ ሳይሆን አገልግሎትም በመሆኑ ተከናውኖልናል ወይ ብለው መጠየቅ እንዳለባቸውና ክንውን የሚገኘውም ሥራን በታቀደው መሠረት በአግባቡ በማከናወንና እግዚአብሔርን አጥብቆ በጸሎት ደጅ በመጥናት መሆኑን አበክረው ገልጸዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አክለውም እያጠናቀቅን ባለው ዓመት በተያዘው ዕቅድ መሠረት የተፈጸመው ሥራዎች ያሉትን ያህል ያልተፈጸሙ ብዙ ሥራዎች በመኖራቸው የሥራ አፈጻጸም ላይ ጠንካራ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው በመግለጽ መመሪያ ተሰጥተዋል።
በስብሰባው ላይ “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” ኤፌ. 5÷16 የሚለውን የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት መነሻ በማድረግ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል። ጽሑፍ አቅራቢው መ/ሰ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶ/ር) የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ ይህን ከዕለት ዕለት እየከፋ የመጣውን ዘመን ለመዋጀት አስፈላጊው ነገር ጥበብ፣ ጥንቃቄ፣ ጸሎት፣ በምስጋና፣ ለሌሎች ብርሃን በመሆን፣ ባለመጨነቅና በመታመን መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዋቢ በማድረግ አስረድተዋል።
በመቀጠልም ለቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ የመነሻ ሀሳብ ያመነጩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒው ዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዘመንን እንዴ መዋጀት እንደሚገባ አባታዊ መንፈሳዊ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ለቀጣዩ ዓመት ሥራቸውን በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት ለመሥራት ለእግዚአብሔር ቃል መግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ኃላፊው አፈ መምህር አባ ገብረሥላሴ በዓመቱ ቤተክርስቲያን የምትመራባቸውን ሕግጋት ለማሻሻልና በዓመቱ የገጠማትን ፈታኝ ወቅት እንድታልፍ የሠራቸውን ሥራዎች የሚያስገነዝብ ገለጻ አድርገዋል። አክለውም በዓመቱ ከቀረቡ የክስ አቤቱታዎች መካከል የሁለቱ ግለሰቦች ምርመራ ተጠናቆ ለአቃቤ ሕግ የቀረበ ሲሆን የአንዱ ደግሞ በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በስብሰባው በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ መሪነት የጉባኤው ተሳታፊዎች በሰጡት የተቆርቋሪነት ሀሳብ የጠቅላይ ጽ/ቤቱን መንፈሳዊ ዕቅድ ዳር ለማድረግ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የሚቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
በጉባኤው የእህታማቾች ዘማርያን ሕብረት መዘምራን የእንቁጣጣሽ ዝማሬ በማቅረብ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተቀብለዋል።

Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ በተባለው ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥያቄ አቀረበች። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ በተባለው ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥያቄ አቀረበች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን... Link to: ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕስራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት Link to: ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕስራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top