የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

August 15, 2026
ነሐሴ ፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
መልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው መመደባቸውን ተከትሎ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ሰላም ዶክተር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሐላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ከህነት ሥራ አስኪያጆች፤ የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ አደራሽ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲመደቡ፤ ፍትሐዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት፤ ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት ፍትሕና ርትዕ እንዲያሰፍኑ መሆኑን ተገልጻል።
በአቀባበሉ ሥነ ሥርዓት የተገኙት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ፣ ቀደም ሲል ፈተና ያለፉት መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ወደ ሀገረ ስብከቱ በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመደቡ በሥራና በአሠራር ስር ነቀል የሆነ ለውጥ እንዲያመጡ ተብሎ መሆኑን ተናግረዋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለም፤ በቤተ ክርስቲያን አባቶች የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት፤ ብቻቸውን ሳይሆን በጋራ መሥራት ሲቻል መሆኑን በመግለጽ በክብር እንደገቡ በክብር እንዲወጡ በጸሎት አግዙኝ ብለዋል።
በአቀባበሉ መርሐ ግብር፤ ቅኔ በሊቃውንት፣ የእንኳን ደኅና መጡ እና የመልካም ሥራ ምስክርነት በሀገረ ስብከቱ እና በክፍለ ከተማው ሠራተኞች የቀረበ ሲሆን አገባባቸው ብቻ ሳይሆን አወጣጣቸውም በመልካም እንዲሆን ተመኝተዋል።
መልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርግስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ን በስብከተ ወንጌል ።
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ የደብረ ሰላም ቦሌ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል፣ የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን እና የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተ ክርስቲያን ዋና ፀሐፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፤
የቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እና የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ያገለገሉ አባት ናቸው።
በቀጣይ ከሱባኤ በኋላ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎችና የሥራ ሐላፊዎች እንዲሁም ከሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር የሥራ ትውውቅ መርሐ ግብር እንደሚኖር በአቀባበል መርሐ ግብሩ ተጠቁሟል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000065.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-15 11:49:252026-08-15 11:50:45የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
Search Search

Recent Posts

  • የደብረ ታቦር በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
  • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በባሕታዊ አባ ተስፋ ማርያም ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ኅዘን በመግለጽ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የብፁዕነታቸው አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል::
  • ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 14ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።
  • ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት... Link to: ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ Link to: ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ስምከ ሕያው ዘኢመውት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top