የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጠፋንበት አገኘችን” ትውልደ አሜሪካዊው ካህን

October 18, 2023

የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ የአኅጉረ ስብከቶችን ሪፖርት በማዳመጥ ላይ ይገኛል።

በዛሬው የሪፖርት ቀን ከሀገር ውስጥ አኅጉረ ስብከቶች በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ አኅጉረ ስብከቶች ሪፖርታቸውን ማቅረብ ጀምረዋል። በጉባኤው ላይ ከቀረቡት ሪፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሪፖርት ሲሆን ያቀረቡት ትውልደ አሜሪካዊው መልአከ ገነት ተስፋ ኢየሱስ ናቸው።

መልአከ ገነት ተስፋ ኢየሱስ በ1975 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ አማካኝነት በሀገረ አሜሪካ ተጠምቀው የቤተ ክርስቲያን ልጅነትን ያገኙ ሲሆን በ1988 ዓ.ም ደግሞ ቅስናን ተቀብለዋል።

ባላቸው የአገልግሎት ትጋት እና የቤተ ክርስቲያን ፍቅር አማካኝነት በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልአከ ገነት ተብለው በሀገረ አሜሪካ የደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተሹመዋል።

በአሁኑ ወቅት በደብሩ ውስጥ በቅስና የሚያገለግሉት እርሳቸው ብቻ ሲሆኑ ሁለት ዲያቆናት አብረዋቸው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው የአጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት የሀገረ ስብከቱን ሪፖርት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡ ሲሆን በጉባኤው ላይ በመገኘታቸው ትልቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

“እኛ ምዕራባውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፈልጋ እስክታገኘን ድረስ ጠፍተን ነበር አሁን ግን ከጠፋንበት አግኝታናለች” በማለት ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት ገልጸዋል።

ጉባኤውም ትልቅ አድናቆት እና ክብር ሰጥቷቸዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/photo_2023-10-18_18-06-51-cover.jpg 372 350 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-10-18 16:50:152023-10-18 16:50:15“የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጠፋንበት አገኘችን” ትውልደ አሜሪካዊው ካህን
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: በራያና አካባቢው የሚገኙ ስድስት ወረዳዎችን እንዲያስተባብር የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት በ፵፪ኛው ዓለምአቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቀረበ። Link to: በራያና አካባቢው የሚገኙ ስድስት ወረዳዎችን እንዲያስተባብር የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት በ፵፪ኛው ዓለምአቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቀረበ። በራያና አካባቢው የሚገኙ ስድስት ወረዳዎችን እንዲያስተባብር... Link to: ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) ማረሚያ ቤት እንዲወርድ ታዘዘ Link to: ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) ማረሚያ ቤት እንዲወርድ ታዘዘ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) ማረሚያ ቤት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top