የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሠራሯን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አጠናቃ ተግባራዊ ልታደርግ መሆኑን ተገለጸ።

August 13, 2026
​
ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
​የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአሠራር ሥርዓቷን ከወረቀት ንክኪ ነፃ ወደ ሆነ የዲጂታል አሠራር ለማሸጋገር የሚረዱ የመሠረተ ልማት እና የሶፍትዌር ፕሮጀክቶችን አጠናቃ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ልትሸጋገር መሆኑ ተገለጸ።
በዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ​ውይይት መድረክ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያ ኃላፊዎች እና በዘርፉ በኩል የተዋቀሩ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል።
​የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የአይሲቲ እና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ ዮሐንስ ተስፋዬ፣ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ የፀደቁትና አቅጣጫ የሚያሳዩት ሰነዶች በቀጥታ ወደ ተግባራዊ ሥራ የሚመሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
​የአማካሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ለጊዜው ተጠናቀው የተዘጋጁ የተለያዩ ሲስተሞችን በውይይት መድረኩ ላይ አቅርበዋል። እነዚህም፦
  1. ​በቤተ ክርስቲያኗ መምሪያዎችና አህጉረ ስብከት የሚካሄዱ በርካታ ድረ-ገጾችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾችን ጠቅልሎ እንደ ዋና መግቢያ በር የሚያገለግል ዋና የመረጃ መግቢያ ድረ-ገጽ (Web Portal) ተገንብቷል። ይህ ፖርታል የቤተ ክርስቲያኗን ስያሜ፣ ማንነትና ታሪክ የሚያሳይ ሲሆን፣ በውስጡም የሰነድ ማደራጃ (Documentation)፣ የእውቀት ማኔጅመንት (Knowledge Management) እና የአርካይቭ ሥርዓቶችን ያካተተ ነው።
  2. የሰበካ ጉባኤ ምዕመናን መመዝገቢያ የዲጂታል ሥርዓት ሲሆን የምዕመናን፣ የጥምቀት፣ የጋብቻ እና የዕረፍተ ሥጋ (ሞት) መረጃዎች በማዕከል ደረጃ የሚመዘገቡበት ሥርዓት ነው። መረጃው በአድባራቱ ደረጃ የሚመዘገብ ቢሆንም፣ አደረጃጀቱ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ በአህጉረ ስብከት፣ በወረዳና በክፍለ ከተማ እስከ ደብር ድረስ ወርዶ የበላይ ኃላፊዎችና አባቶች ሙሉ መረጃውን በቀላሉ ማየትና መከታተል የሚያስችላቸው ነው።
  3. የሰው ኃይል አስተዳደር ሥርዓት (HR System) ሲሆን በቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር በሁሉም ደረጃ የሚገኙ አገልጋዮችና ሠራተኞች የሚመዘገቡበት ነው። ጊዜና ቦታ ሳይገድበው ባለሙያዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አማካይነት መረጃዎችን ማስገባትና በአንድ ማዕከል ማየት የሚያስችልም ነው ብለዋል።
​በተጨማሪም የሀብት አስተዳደር የኢአርፒ (ERP) ሲስተሞች፣ የዲጂታል ላይብረሪ እና የቅርስ ጥበቃ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን፤ የዲጂታል ሽግግሩ ዋና መርሕ ቴክኖሎጂን ለመግዛት ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ተልዕኮን ለማሳካትና አሠራርን ለማዘመን እንደሆነ ተጠቅሷል።
​ቀሲስ ዮሐንስ አክለውም ሥራው ቢጀመርም ወደ ዲጂታሉ ዓለም ለመውሰድ የታቀዱ በርካታ ተግባራት የሚቀሩ በመሆኑ፣ በዘርፉ ዕውቀቱና አቅሙ ያላቸው የቤተ ክርስቲያኗ ልጆች ባሉበት ሆነው የቴክኖሎጂ ዕድገቷን እንዲደግፉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል።
​በመድረኩ የመምሪያ ኃላፊዎች ለዘርፉ ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህ ተግባር የቤተ ክርስቲያኗን ጥንታዊነትና ልዕልና ለዓለም የሚያስተዋውቅ፣ ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት የሚያጎለብትና ገጽታዋን የሚቀይር በመሆኑ በፍጥነት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ ደብር መዋቅሩ ተዘርግቶ መሬት ላይ ወርዶ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
​እንዲሁም ሥራውን ወደ ተግባር ለማውረድ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ትብብርና ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።
​የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከልማት ሥራዎች ሁሉ በላይ ሆኖ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል። “ቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ናት፤ አሁን ላይ ከቴክኖሎጂ አንጻር ወደ ኋላ ቀርተናል” ያሉት ብፁዕነታቸው፣ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም፣ የቤተ ክርስቲያኗን ክብርና ልዕልና ጠብቆ ከዓለም እና ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ማቀራረብና አብሮ መፍጠን እንደሚገባ ገልጸዋል።
​ቤተ ክርስቲያን የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን የሚመራ ክፍል በመምሪያ ደረጃ አዋቅራ እየተንቀሳቀሰች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከሀገረ ስብከት ጀምሮ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ መዋቅሩ እንዲዘረጋ መመሪያ የወረደ መሆኑ ተገልጿል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000063.jpg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-13 18:19:202026-08-14 08:45:43የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሠራሯን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አጠናቃ ተግባራዊ ልታደርግ መሆኑን ተገለጸ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለ272 አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።
  • የደብረ ታቦር በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
  • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በባሕታዊ አባ ተስፋ ማርያም ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ኅዘን በመግለጽ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የብፁዕነታቸው አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል::
  • ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 14ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡ አስታወቀ። Link to: የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡ አስታወቀ። የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት... Link to: 14ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ Link to: 14ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ 14ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top