የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

March 3, 2023

የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲ኛ ዓመት በዓሉ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ሥነሥርዓት ተከብሮ ውሏል።በበዓሉ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ቴጉሃን ታጋይ ታደለ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያና የድርጅትኃላፊዎች፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚሁ ጊዜ ” ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው “(ዮሐ17፥11)የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል መነሻ በማድረግ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

አያይዘውም መለያየት አንዱን ወገን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም በእኩል ይጎዳል ሲሉ ገልጸዋል።

በቤተክርስቲያን የሚፈጠር መለያየት ከሌላው ሁሉ በባሰ ሁኔታ የማኅበረሰብን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወት በእጅጉ እንደሚጎዳ ጠቅሰዋል።

እግዚአብሔር አምላክ ከምንም በላይ መለያየትን ይጠላል፤ እንዲህ ባይሆን ኖሮስ ለምእመናን አንድነት ሲል ሰው ሆኖ ደሙን ባላፈሰሰ ነበር ብለዋል።

ከዚህ አኳያ በኅብረትና በአንድነት መኖር ለፍጡራን የውዴታ ሳይሆን የግዴታ ሆኖ እንዲቀጥል የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ትልቁ የችግር መፍትሔ ትዕግሥት፣ ውይይትና መቻቻል እንጂ ግጭት አይደለም ሲሉም መክረዋል።

ቤተክርስቲያን ያጋጠማትን ችግር በቀላሉ ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ በንስሐ፣ በሰላምና በውይይት መፍታት የሚያስገኘውን መንፈሳዊ ጥቅም በመረዳት እንጂ የተፈጸመው ሕገ ወጥ ድርጊት ቀላል ስለሆነ አይደለም ብለዋል።

በሐዋርያት እግር ተተክተን የምንገኘው ሁላችንም ሊቃነ ጳጳሳት በጎቹን ለመበታተንና አለያይተን ለማፋጀት ሳይሆን ለማሰባሰብና አንድ ለማድረግ እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም ሲሉ መክረዋል።

ይህንን የማናስከብር ከሆነ በዓለ ሢመትን ማክበር ሥልጣነ ክህነትም አለኝ ማለት ምን ፋይዳ አለው? ስለዚህ አሁንም ሰከን ብለን እናስብና ወደ ልባችን እንመለስ በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የተከሰተው ችግር ለጊዜው መልክ ቢይዝም ቀጣይ ሥራ እንዳለን ግን ከሁኔታው አይተናል፤ ጉዳዩን በጥልቀት አይተን ዘላቂ መፍትሔን ማበጀት አሁንም ከእኛ ይጠበቃል በማለትጠቅሰዋል።

የቤተክርስቲያንን አንድነትና ህልውና ከሚያስቀጥለው ሐዋርያዊ ተልእኮ ባሻገር የቤተክርስቲያንን የሥራ አፈጻጸም ከአባካኝነት፣ ከአድልዎ፣ ከዘረኝነትና ከፖለቲከኝነት ለማጽዳት በቁርጠኝነት መሥራት አለብን፤ እሰከመቼ በዚህ ስንታማ እንኖራለን ከእንግዲህ ወዲህ በቃ ማስተካከል አለብን ሲሉ መክረዋል።በመጨረሻም

“……የቤተክርስቲያንን አንድነትና ህልውና ከሚያስቀጥለው ሐዋርያዊ ተልእኮ ባሻገር የቤተ ክርስቲያንን የሥራ አፈጻጸም ከአባካኝነት፣ ከአድልዎ፣ ከዘረኝነትና ከፓለቲከኝነት ለማጽዳት በቁርጠኝነት መሥራት አለብን።እስከ መቼ በዚህ ስንታማ እንኖራለን፤ ከእንግዲህ ወዲህ በቃ፤ ማስተካከል አለብን፤
ማስተካከል አለብን፤ማስተካከል አለብን።ብለዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቅዱስነታቸውን ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት የተዘጋጀው “ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መጻህፍት በዛሬው ዕለት ተመረቀ። Link to: የቅዱስነታቸውን ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት የተዘጋጀው “ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መጻህፍት በዛሬው ዕለት ተመረቀ። የቅዱስነታቸውን ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት... Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ። Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛው የኢትዮጵያ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top