የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።

March 10, 2023

የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሕገወጥና ኢቀኖናዊ ድርጊት ምክንያት በሕግ አግባብ የሚፈቱ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ መብት እና የአማኞችን ሁለንተናዊ መብት እንደከበር ያስችል ዘንድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች የጠበቆች ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮችን በሕግ አግባብ እንዲፈቱ እየጠየቀችና እየተከታተለች እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ መሠረት የጠበቆች ቡድኑ ዛሬ የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ/ም በዋለ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ችሎት የሰጠውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በጥልቅ ማብራሪ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፍርድቤቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሕጋዊ ጥያቄ በሕግ አግባብ መልካም ውሳኔ የሰጠበት መሆኑን ግልጽና ጥልቅ በሆነው ገለጻው ተጠቁሟል።

የጠበቆች ቡድኑ በመግጫው ሕገወጦቹ ያቀረቦቻው የመቃወሚያ ጉዳዮች እንደነበሩ አብራርቶ ፍርድቤቱ በውሳኔ ውድ አድርጓቸዋል ብሏል።
ፍርድቤቱ ውድቅ ካደረጋቸው መቃወሚያ መከራከሪያ ነጥቦች መካከል

፩. ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት ያላት በመሆኑ የመክሰስና የመከሰስ መብት የለት መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ክስ መመስረት እንደምትችል።

፪. ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የመብት ጥሰት የንብረት ባለቤትነት ያለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት የሚችል መሆኑ በመጥቀስ የሕገወጡ ቡን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድ አድርጓል።
በአጠቃላይ በሕገወጡ ቡድን የቀረቡ መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጡ ሹመት ላይ በተሳተፉ ፳፮ቱ ግለሰቦች ላይ ክስ እንድትመሠርት ውሳኔ ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በጠየቀችው የሦስት ወር እግድ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቱ ፵፭ ቀናት ከሦስቱ “አባቶች” በስተቀር ፳፮ (26)ቱም ግለሰቦች
ከዚህ ቀደም የገቡበትን መንበረ ጵጵስና እና አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ “የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏትን ይዞታዎች፣ አህጉረ ስብከት፣ገዳማት እና አድባራት፤ አብያተ ክርስቲያናት ንብረቶቿን፤ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ መገልገያ እንዳይጠቀሙ፣ ወደ ቅጥሯ እንዳይገቡ፤ ንብረቶቿን እንዳይወስዱ፣ እንዳይገለገሉ፣ ዓርማዋንና ስሟን እንዳይጠቀሙ ይህ ጊዜያዊ የዕግድ ትዕዛዝ ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀናት ብቻ (ከየካቲት ፫/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ብቻ ተሰጥቷል”።
መባሉን የጠበቆች ቡድን በመግጫው አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር የኦርዶክሳውያን የእስር ሁኔታ የተነሳ ሲሆን በአብዛኛው እየተፈቱ መሆናቸውን ጠቅሶ በሻሸመኔና በአርሲ ነገሌ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን እስረኞ ለመጋቢት ፯፳፻፲፭ ዓ/ም ፍርድ ቤት እንደተቀጠሩም ተጠቅሷል።

በዚህ ረገድ የሕግ ተርጓሚ አካላት ላይ የሚታየው ፍትሕን የማስፈን ተጠቃሽ ሥራዎችን በመመዘርዘር በፍርድ ቤቶች የሚስተዋለው ፍትሕን የማስፈን መንገድ የሚበረታታና የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሰው የጠበቆች ቡድኑ በአስፈጻሚ አካላት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የታየው የፍረድ ቤቶችን ውሳኔ ያለማስፈጸም ሁኔታዎች በእጅጉ ሊታረሙ እንደሚገባም ገልጿል።

በሌላ በኩል “በፓስተር ዮናታን” እና “በፓስተር ኢዩ ጩፋ” የቀረበው ክስ ምን ላይ ደረስ? ለሚለውም በምላሹ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን እያስኬደው እንደሆነ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም የጠበቆች ቡድኑ የሕጉን መንገድ ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መብትና ማስጠበቅ ሁነኛ ግቡ መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን ይሁን እንጂ የትኛውም መንገድ ይሁን ድርጊት ከቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ከአባቶች ቃል የማይቀድምና የማይበጥል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የምትከተላቸውን የይቅርታና የስምምነት አቅጣጫዎችን በማክበረ እንደሚቀጥል ገልጿል።

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-03-10 12:24:262023-03-10 12:24:26ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ ተመደበ፤ Link to: በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ ተመደበ፤ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ... Link to: ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ የሕይወት ታሪክ Link to: ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ የሕይወት ታሪክ ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top